Thursday, May 29, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation የአቶ ፍስሃ ወ/ገሪማ እና የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሰ/መ/ቁ. 253575 አመልካች በመስከረም 22 ቀን 2016 ዓ/ም በተጻፈ ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይህን ውሳኔ በመቃወም የቀረበ ሲሆን ይዘቱም የሥር ፍርድ ቤት ጉዳዩ በእርቅ ያለቀ ነው በማለት በብይን ክሱን ለመዝጋት መሠረት ያደረገው በ11/08/2013 ዓ/ም በአመልካችና 1ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገው ስምምነት ለአመልካች ተነቦላቸው ፈርመዋል በሚል በህግ ፊት የሚጸና የመጨረሻ የጉዳት ካሳ ክፍያ ስምምነት ተፈጽሟል በሚል ነው፡፡ ይሁን እንጂ መሀይማንና ማየት የተሳናቸው ሰዎች የሚያደርጉት ውል በዳኛ ወይም በአዋዋይ ፊት መደረግ እንዳለበት በህግ ተደንግጎ እያለ ስምምነቱ በዚህ ሁኔታ መደረጉ ሳይረጋገጥ በውሉ ላይ ፈረሙ የተባሉት የ2ኛ ው ተጠሪ የራሱ ሠራተኞች በመሆናቸው ምስክርነታቸው እምነት የሚጣልበት ባለመሆኑና የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1730 በሚጠይቀው መሠረት ተስማሚ ወገኖች ፈቃዳችንን በመስጠት ስምምነቱን የፈጸምን መሆኑን የሚያሳይ ባለመሆኑና፣ የእርቅ ስምምነቱ ላይ 2ኛው ተጠሪ ያልፈረመ ከመሆኑም ሌላ በስምምነቱ ላይ ፈቃዱን ያልሰጠው 1ኛው ተጠሪ ላይ ስምምነቱ ተፈጻሚ እንዲሆን በማድረግ የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ የግራ ቀኙ ጉዳይ በስምምነት አልቋል በማለት የተሰጠው ብይንና ተሽሮ የሥር ፍርድ ቤት በፍሬ ጉዳዩ ላይ አከራክሮ ውሳኔ እንዲሰጥ ይወሰንልን የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ… Print 1698 Documents to download 253575(.pdf, 840.67 KB) - 211 download(s)