Tuesday, May 27, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ እና ታደሰ ከበበ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የሰበር መ/ቁ247851 በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዳይ የግንባታ ውልን የሚመለከት ነው፡፡ ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ ባቀረበው ክስ ነው፡፡ ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው ተጠሪ ባቀረበው ክስ የጀሞ ጤና ጣቢያ ጂ + 5 ህንጻ ለማስራት ከአመልካች ጋር ግንቦት 29 ቀን 2009 ዓ.ም ውል የገባን ቢሆንም አመልካች በውሉ መሰረት የተሟላ ዲዛይን እና የግንባታ ፍቃድ በወቅቱ ባለመስጠቱ እንዲሁም ግንባታ የሚከናወንበትን ቦታ አጽድቶ ባለማስረከቡ ምክንያት ስራው በመጓተቱ በአመልካች ጥፋት ውሉ ሰኔ 03 ቀን 2011ዓ.ም ተቋረጧል፡፡ በመሆኑም በሳይት ላይ ለተቀጠሩ ሰራተኞች ሳይሰሩ የተከፈላቸው ደመወዝ የኮንስትራክሽን ማሽን ስራ የፈቱበት ኪሳራ ግንባታው በመዘግየቱ ምክንያት የተፈጠረ ኦቨር ሄድ ወጪ ስራው እስከ መጨረሻው ቢሰራ ኖሮ ከስራው የሚገኘው ትርፍ የተሰራ ስራ በባለሞያ የተረጋገጠ ግምት በግንባታ ቦታ የገባው የግንባታ ማቴሪያል ግምት ላይ ለከሳሽ ቅድሚያ የተከፈለው ተቀንሶ ልዩነቱን በድምሩ 25,201,775.23(ሃያ አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሰባ አምስት ብር ከ23/100) ከወለድ ጋር እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል፡፡መልካም ንባብ… Print 2002 Documents to download 247851(.pdf, 856.81 KB) - 265 download(s)