Tuesday, May 20, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation የአፋር ክልል የኤትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና እነ እንድሪስ ሰይድ የሰበር መዝገብ ቁጥር - 253719 ጉዳዩ የተጀመረው በአፋር ክልል የአሩሲረሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በስር ፍርድ ቤት አመልካች 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው ኢትዮ ቴሌኮም 1ኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የስር ከሳሽ በስር ተከሳሾች ላይ ያቀረበው ክስ ይዘት ከሳሽ በአናጢነት ስራ የሚተዳደር መሆኑን ከስራው በቀን ብር 500.00 ገቢ የሚያገኝ መሆኑን ንብረትነቱ የ 1ኛ ተከሳሽ የሆነው ቢሮ ጣራ በብር 1,500.00 ለመስራት ከ 1ኛ ተከሳሽ ጋር ውል መግባቱን ስራውን በመስራት ላይ እያለ በጣራ ላይ በተዘረጋው የኤሌክትሪክ ገመድ በመያዙ ወደ መሬት በመውደቁ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ ህክምና ሲከታተል ቆይቶ የሀኪሞች ቦርድ 5% የአካል ጉዳት የደረሰበት መሆኑን በማረጋገጥ ማስረጃ የሰጠ በመሆኑ የከሳሽ እድሜ 35 አመት ስለሆነ ወደፊት 65 አመት ስለምኖር የ 30 አመት የአካል ጉዳት ምክንያት የተቋረጠብኝ ገቢ ካሳ ብር 270,000.00 ተከሳሾች በአንድነትና ነጠላ እንዲከፍሉ የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ …. Print 558 Documents to download 253719(.pdf, 1.03 MB) - 61 download(s)