Tuesday, February 22, 2022 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ-ክርስቲያን ኮሚሽን እና አቶ መስፍን አዱኛ የሰ/መ/ቁ. 211260 ጉዳዩ የግል የስራ ቅጥር ዉልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በጀመረበት በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ በቀን 30/06/2013 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከጥር 23 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ በፕሮጀክት ኦፊሰርነት በወር ብር 10,095.00 እየተከፈለኝ ሳገለግል የቆየሁ ቢሆንም አመልካች ምንም አይነት ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠኝ፣ በማላውቀው እና በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም የስራ ውሌን ያቋረጠው በመሆኑ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ተብሎ ወደ ስራዬ እንድመለስ፤ ወደ ስራ የማልመለስ ከሆነ ደግሞ ያልተጠቀምኩበት የ58 ቀን የዓመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ፣ ካሳ፣ የሶስት ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ ክፍያ ለዘገየበት የሶስት ወር ደመወዝ ቅጣት እንዲከፍል እና የስራ ልምድ እንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቀዉን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ እንደሚከተለው ቀርቧል………… Previous Article የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል ገቢዎች ቢሮ እና አቶ አዕምሮ ዘሪሁን የሰ/መ/ቁ.210727 Next Article ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር እና እነ አቶ ታምሩ ደብሩ ሰ/መ/ቁ፡-191430 Print 13771 Documents to download 211260(.pdf, 825.29 KB) - 1069 download(s)