/ Categories: CASSATION, Cassation

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አቶ መጣልኝ መላኩ የሰ.መ.ቁ.252953

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበዉ የክስ አቤቱታ፡ ከሳሽ በ2005 ዓ.ም የ40/60 የመኖሪያ ቤት መርሃ ግብር ተመዝግቤ በአሁኑ ወቅቱ ባጠቃላይ 430000 ማለትም መቶ ፐርሰንት የቆጠብኩኝ በመሆኑ በዉሉና በመመሪያዉ መሰረት ቅድሚያ ዕጣ እንዲወጣልኝ መደረግ ሲገባዉ ከመመሪያዉ ዉጭ አርባ ፐርሰንት የቆጠቡ ሰዎች ተካተዉ እጣ እንዲወጣ በመደረጉ መብቴን አጣቧል፡፡ ከሳሽ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር ባደረግነዉ ዉል ቤቱን ሊያስገኝ የሚያስችል ዉል የተዋዋልንና ግዴታዬን የተወጣሁ ቢሆንም ሌሎች ተከሳሾችም በመመሪያ ቁጥር 21/2005 መሰረት የሚጠበቅባቸዉን አስተዳደራዊ ኃላፊነታቸዉን በመወጣት ቤቱን ሊያስረክቡኝ አልቻሉም፡፡ 1ኛ ተከሳሽ ከ3ኛ ተከሳሽ ጋር ባደረገዉ ሰነድ መሰረት ተገንብተዉ የተጠናቀቁትን ቤቶች ከቢሮዉ ተረክቦ በዉሉ መሰረት ቅድሚያ ማስረከብ ሲገባዉ ይህን ያላደረገ በመሆኑ፣ ሌሎች ተከሳሾችም ኃላፊነታቸዉን ያልተወጡ በመሆናቸዉ፣ በመመሪያዉና በዉሉ መሰረት ተገንብተዉ ከተጠናቀቁ ቤቶች ላይ ከአንዱ ሳይት እንዲወስድ ተከሳሾች በአንድነትና በነጠላ ኃላፊነት አለባቸዉ ተብሎ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ….

Print
5084

Documents to download

  • 252953(.pdf, 861.73 KB) - 565 download(s)