Thursday, July 21, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አቶ ተከስተ ካሴ የሰ/መ/ቁ. 212603 ጉዳዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተጠሪ ባቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ እ.አ.አ. ከቀን 22/04/2020 ዓ.ም ጀምሮ በወር ብር 42,863.37 እየተከፈለኝ በአውሮፕላን ጥገና አሰልጣኝነት ሳገለግል ቆይቻለሁ፡፡ ከመስከረም 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በድርጅቱ ውስጥ በተቋቋመው የሰራተኛ ማህበር ውስጥ ምክትል ፀኃፊ በመሆን እያለገልኩ ቆይቻለሁ፡፡ ይሁን እንጂ አመልካች ስለእኔ እውነት ያልሆነ መረጃ በማስተላለፍ ስም እና ዝናዬን አጥፍተሃል፣ ከሌሎች ሰራተኞች ጋር በስራ ቦታ መተባበር እና ሰላማዊ የስራ ግንኙነት እንዳይኖር አድርገሃል በማለት የስራ ውሌን አቋርጦታል፡፡ ከስራ ስሰናበት በህብረት ስምምነቱ መሠረት በተቋቋመው ኮሚቴው ውስጥ የሰራተኛ ማህበር ተወካይ አልነበረም፡፡ ስለሆነም ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ተብሎ ያልተከፈለኝ ደሞዝ ተከፍሎኝ ወደ ስራዬ እንድመለስ ይወሰንልኝ፤ ወደ ስራ ልመለስ የማልችልበት አግባብ ካለ ደግሞ የስራ ስንብት ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ የሚያዝያ ወር ሙሉ ደሞዝ፣ እ.አ.አ. የ2020 ዓ.ም የዓመት እረፍት ክፍያ እንዲከፍለኝ እና የስራ ልምድ እንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቁትን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡መልካም ንባብ…….. Print 15590 Documents to download 212603(.pdf, 1.05 MB) - 1168 download(s)