/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

የእነ አምሳሉ አበራ እና አሻግሬ አበራ የሰ-መ-ቁ195361

.   የእነ አምሳሉ አበራ  እና አሻግሬ አበራ የሰ-መ-ቁ195361 ጉዳዩ የገጠር መሬት ዉርስ ይመለከታል፡፡ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በእስቴ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን በአሁኑ ተጠሪ ላይ ያቀረበው ክስ ሲሆን ይዘቱም በፍ/ቤቱ በመ/ቁ 0482874 በቀን 06/10/2010 ዓ/ም የሟች አያቶቼ አቶ አበረ ፋንቴ እና እማሆይ ፀሓይ ካሳ ወራሽነት አረጋግጨ እያለ ተጠሪም የልጅ ልጆች ሁነን እያለ የሟች መሬቶችን ብቻውን ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በመያዝ አላካፍልም ስላለኝ የሟች አያቶቼን የይዞታ መሬት ድርሻዬን እንዲካፈለኝ ውሳኔ ይሰጥልኝ በማለት ዳኝነት የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ የሰጠው መልስ ባጭሩ አመልካች የአያታችን መሬት መጠየቅ የሚችለው ወላጆቹ ሙተው ከሆነ ነው፤አባቱ እያለ ተተኪ ወራሽ ሊሆን ስለማይገባ እና የቤተሰብ አባል ያልሆነና በውርስ ላይም ያልጠየቀ እንዲሁም ሟች አቶ አበረ ፈንቴ የሞተዉ በ1995 ዓ.ም ስለሆነ አመልካች መብት የጠየቀዉ በ2010 ዓ.ም ስለሆነ ይህ ጊዜ ሲቆጠር 15 ዓመት በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1000(1) መሰረት በ3 ዓመት ይርጋ መብቱ ቀሪ ሆኗል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን በአማራጭ አመልካች የቤተሰብ አባል አይደለም ከአያታቸው ጋር አላደገም በማለት ክሱ ዉድቅ እንዲደረግ መከራከሩን መዝገቡ ያሳያል፡፡……

Previous Article እነ ሻለቃ ሰብሪ ቶፊቅ መሐመድ እና ሌ/ኮ/ል አለሙ ጌትነት አባተ የሰ-መ-ቁ 183941
Next Article እነ አቶ ሳሙኤል ገዛኸኝ፣ አቶ መኩሪያ ታረቀኝ እና አቶ ፍሰሃ እርቅይሁን የሰ-መ-ቁ-191141
Print
14457

Documents to download