/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

የእነ ወ/ሮ እቴነሽ አሰፋ ወኪል መኮንን በቀለ እና ወ/ሮ በላይነሽ አሰፋ የሰ/መ/ቁ 208950

ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው ከሳሾች በቀን 03/11/2010 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ ሟች ወ/ሮ ቦጋለች ሺበሺ አያታችን ሲሆኑ በመ/ቁ 67546 በቀን 05/03/2010 ዓ.ም የሟች አባታችን መላኩ ወ/ሰማንያ ተተኪ ወራሽነታችንን አረጋግጠናል፡፡ 2ኛ ተከሳሽ (የአሁን 1ኛ አመልካቸ) ደግሞ የሟች እናታቸው ልጅና ወራሽ ናቸው፡፡ ሟች ወ/ሮ ቦጋለች ሺበሺ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ቀበሌ 16 የቤ/ቁ 325 የተመዘገበ ቤት ነበራቸው፡፡ ከሳሾች በጋራ 25% ለእያንዳንዳችን ከሳሾች ደግሞ 1/24ኛ ድርሻ፤ እንዲሁም 2ኛ ተከሳሽ 25% ድርሻ አለን፡፡ 1ኛ ተከሳሽ ሟች በቀን 11/08/1996 ዓ.ም ኑዛዜ አድርገዋል በማለት በመ/ቁ 07365 በቀን 07/03/2010 ዓ.ም ኑዛዜ ማረጋገጣቸውን በ02/11/2010 ዓ.ም ተረድተናል፡፡ በኑዛዜው ላይ ያለው ፊርማ የሟች ወ/ሮ ቦጋለች ሺበሺ ካለመሆኑም በላይ ኑዛዜው በህግ የተቀመጠውን ፎርማሊቲ በተለይ በፍ/ህ/ቁ 880 እስከ 897 የተጠቀሱትን ድንጋጌዎች አሟልቶ የተዘጋጀ ስላልሆነ በፍ/ህ/ቁ 2008 መሰረት የፊርማ ምርመራ ሊደረግ ይገባል፡፡መልካም ንባብ……           

Print
12150

Documents to download

  • 208950(.pdf, 1.03 MB) - 992 download(s)