Thursday, May 29, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation የወ/ሮ በላይነሽ ወንድማገኘሁ ወራሾች አቶ በሻዳ ወርቁ ደፈሩአቶ ደበበ ወርቁ ደፈሩ እና አቶ ደበበ ቱሉ (3ሰዎች)ሰ.መ.ቁ:- 257723 የይዞታ ክርክር የሚመለከት ሲሆን ተጠሪዎች በአመልካቾች አውራሽ ላይ ክርክሩ በጀመረበት የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘቱ ሲታይ፡- አመልካቾች በአዲስአበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ሰርቲ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ከነበራቸው ቦታ በምስራቅ መንገድ፣ በምእራብ የአቶ ደቻሳ መኖሪያ ቤት በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ ኤሌክስቴራዞና እምነበረድ ፋብሪካ የሚያዋስኑት ስፋቱ 5057 ካሬ ሜትር ህዳር 1 ቀን 1984 ዓ.ም በተፃፈ የስጦታ ውል ለተጠሪዎች ያስተላለፉ መሆኑን፤ ተጠሪዎችም ለ30 ዓመት በ3ኛ ተጠሪ ስም ግብር በመገበር በእጃችን አድርገን አትክልቶችን በመትከልና በመዝራት የምናስተዳድረውን ይዞታ የአመልካቾች አውራሽ የሆኑት (ወ/ሮ በላይነሽ ወንድማገኝ)(ስር ተከሳሽ) መብትና ጥቅም ሳይኖራቸው ህጋዊ ይዞታችንን በጉልበት ነጥቀው የያዙ በመሆኑ ለቀው እንዲወጡ እንዲወሰንልን የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ… Print 5030 Documents to download 257723(.pdf, 879.45 KB) - 696 download(s)