Friday, December 31, 2021 / Categories: CASSATION, Judgement, Cassation የየካ ክ/ከተማ ዐቃቤ ህግ ፅ/ቤት እና እነአቶ ብሩክ ወንድሙሰ/መ/ቁ፡-204866 ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ ሊቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካችን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 የቀረበን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሰጠውን ውሳኔ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከውጤት አንፃር ማፅናቱ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይኸው እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረበውን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ሲሆን አመልካች በስር ፍርድ ቤት የመ/አመልካች የነበረ ሲሆን ተጠሪዎች የመ/ተጠሪዎች ነበሩ፡፡አመልካች በስር ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 መሰረት ባቀረበው አቤቱታም አመልካች በአዋጅ ቁጥር 64/2011 መሰረት የአስተዳደሩን እና የነዋሪዎችን መብት እና ጥቅም በማስከበር በማናቸውም የዳኝነት አካል ዘንድ የመቃወም አቤቱታ የማቅረብ መብት እንዳለው በመግለፅ በመቃወም ተጠሪዎች እና በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ፅ/ቤት መካከል በተደረገው ክርክር ላይ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ውሳኔ መብቴን የሚነካ በመሆኑ ሊሰረዝ ይገባል በማለት አመልክቷል፡፡…………………. Previous Article ኮ/ል ተክለብርሃን ገ/መድህን እና የደ/ዕዝ ወታደራዊ ዓ/ህግ የሰ/መ/ቁ፡- 204813እና206556 Next Article የአቶ ተመስገን ተሻገር እና አቶ ሞላ ታረቀኝ ሰ/መ/ቁ፡-207003 Print 14292 Documents to download 204866(.pdf, 717.73 KB) - 1466 download(s)