/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

የየጉለሌ ክ/ከ/ወረዳ 2 የመ/ቤቶች ጽ/ቤት እና ወ/ሪት ፍቅርተ ከተማ ሰ.መ.ቁ 204992

የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 22 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታው የሚያከራክረው የመንግሥት ቤትን አስመልክቶ የስር ፍ/ቤት ተጠሪ መብት አላት ብሎ መወሰኑ እና የበላይ ፍ/ቤቶችም የስር ፍ/ቤት በውሣኔው የፈፀመውን ስህተት ሳያርሙ ማለፋቸው  መሠረታዊ የሕግ ስሕተት  በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው፡፡

ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ላየው የአዲስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪ አቅርባው የነበረው ክስ ከሚያከራክረው ቤት ተከራይ ከነበሩት አቶ አስፋው ቢራቱ ጋር በቤት ቁጥር 167 ውስጥ እንደልጅ ማደጓን፣ በቤቱ ውስጥ ያደገችው ከህፃንነቷ ጀምሮ መሆኑን እና እናቷም በህይወት የሌለች መሆኑን፣ ነገር ግን አመልካች ከቤቱ በህገወጥ መንገድ ስላስወጣት በቤቱ የመኖር መብት አላት ተብሎ እንዲወሰንላት ዳኝነት ጠይቃለች፡፡………

 

Previous Article በደሴ ከተማ የሆጤ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እና የወ/ሮ ማሚቴ ሁሴን ወራሾች እነ አያል አብርሃ የሰ/መ/ቁ፡-204074
Next Article አቶ መለሰ ዘርጋው እና የፌዴራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ የሰ/መ/ቁጥር 185932
Print
11940

Documents to download