/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

የደቡብ ክልል ዐ/ሕግ እና እነ በረከት በየነ የሰ/መ/ቁጥር 211689

ጉዳዩ የሰው መግደል ወንጀል የሚመለከት ክስን  የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነበር፡፡ የአሁን አመልካች ጳጉሜ 4ቀን 2011ዓ/ም በተፃፈ ክሱ 1ኛ ተጠሪን 3ኛ ተከሣሽ 2ኛ ተጠሪን ደግሞ 5ኛ ተከሣሽ በማድረግ ተጠሪዎች ከሌሎች ተከሣሾች ጋር ሆነው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1)(ሀ) እና 540 የሚደነግገውን ተላልፈው የካቲት 24ቀን 2011ዓ/ም ከምሽቱ በ2ሰዓት አረካ ከተማ ቀበሌ 04 ትምህርት ቤቶች ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሟች አዲሱ በለጠን 4ኛ ተከሣሽ ስሙን ጠርቶ እንዲቆም አድርጎ ለስላምታ የሟችን እጅ ጨብጦ እንደያዘው፤ 1ኛ ከሣሽ ከኋላ በኩል በፌሮ ብረት የኋላ ጭንቅላቱን 2 ጊዜ ሲመታው፤ 2ኛ ተከሣሽ በጌጠኛ ድንጋይ (ኮብል ስቶን) የግራ ጭንቅላቱን 3ኛ ተከሣሽ(1ኛ ተጠሪ ) የሟችን ጀርባ በክራንች ሁለት ጊዜ፤   5ኛ ተከሣሽ(ሁለተኛ ተጠሪ) ሟቹ እንደወደቀ ጉረሮውን እና ሆዱን ከረገጠው በኋላ ሮጠው ማምለጣቸውን ሟች በድብደባው ስለደከመ በዱቦ ሆስፒታል ሲታከም ቆይቶ መጋቢት 5ቀን 2011ዓ/ም መሞቱን በመዘርዘር የሰው መግደል ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ክስ አቅርቦባቸዋል፡፡መልካም ንባብ………….

Print
14029

Documents to download

  • 211689 (.pdf, 1.05 MB) - 1000 download(s)