Friday, March 4, 2022 / Categories: CASSATION, Cassation የጎንደር ከተማ ቂርቆስ ቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት ወ/ሮ ስመኝ አለሙ እና የሰ/መ/ቁ፡-206636 ጉዳዩ የቤት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ጎንደር መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው፡፡ በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪዎች ከሳሾች፤ የአሁን አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን ተጠሪዎች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- በጎንደር ከተማ ጭርቆስ ክፍለከተማ አካባቢ 07 ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ እና አዋሳኙ በክሱ የተገለጸ 30.50 ካ.ሜ የሆነ ቤት እና ቦታ በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሠረት ያልተወረሰ እና የሟች አባታቸው የምርጫ ቤት መሆኑን፤ ከዚሁ ይዞታ ውስጥ 6.5 ካ.ሜ ላይ ያረፈውን ቤት አመልካች ያለአግባብ የያዘባቸው መሆኑን በመግለጽ ለቆ እንዲያስረክባቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡……… Print 12370 Documents to download 206636(.pdf, 932.1 KB) - 884 download(s)