Wednesday, September 18, 2024 / Categories: CASSATION, Cassation የጦሳ ነጋዴዎች አጠቃላይ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማኅበር እና የኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር የሰ/መ/ቁጥር 237423 የጉዳዩ አመጣጥ አጠር ባለ መልኩ ሲታይ፡- ክርክሩ የተጀመረዉ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሆኖ የአሁን ተጠሪ ተወካይ የነበረዉ የአማራ ብሔራዊ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአሁን አመልካችና የአመልካች ሥራ አስኪያጅ እና ሠራተኛ በሆኑት ላይ ሁለት ክሶችን መስርቷል፡፡ የመጀመርያው ክስ የመሰረተው በአመልካች ድርጅት ሥራ አስኪያጅ እና የጥበቃ ሠራተኛ ላይ ሲሆን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1/ሀ) እና በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120/1 ላይ የተደነገገዉን በመተላለፍ ያለደረሰኝ ግብይት በማከናወናቸው ያለደረሰኝ ግብይት በመፈጸም ወንጀል ተከሰዋል የሚል ክስ መስርቶባቸዋል፡፡ ሁለተኛው ክስ የመሰረተው አመልካች በሆነው ድርጅት ላይ ሲሆን የክሱ ይዘትም አመልካች በወንጀል ሕግ አንቀጽ 34/1 እና በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120/1 ስር የተደነገገዉን በመተላለፍ ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ እንዳለበት እያወቀ በቀን 10/03/2013 ዓ/ም ከምሽቱ በግምት 1፡00 ሰዓት በደሴ ከተማ ሆጤ ክፍለ ከተማ መናኸሪያ አካባቢ በሚገኘዉ ጦሳ ቁጥር 1 መኝታ ቤት ደንበኛ የሆኑት ግለሰብ ለተከራዩት አልጋ ደረሰኝ ባለመስጠቱ በፈጸመዉ ያለደረሰኝ ግብይት በመፈጸም ወንጀል ተከሷል የሚሉ ናቸው፡፡ መልካም ንባብ Print 1703 Documents to download 237423(.pdf, 1.26 MB) - 532 download(s)