Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation የፌደራል ዐቃቤ ህግ እና አቶ አበበ ወንድሙ ኤጋ የሰ/መ/ቁጥር 251759 አመልካች በስር ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ተጠሪ የወ/ህ/ቁ.539(1)(ሀ) ን ተላልፈው ሰው ለመግደል አስቀድሞ በነበረው ሀሳብ ጨካኝነቱንና ነውረኝነቱን በሚያሳይ ሁኔታ ወንድሙን ሟች ጀንበሩ ወንድሙን ከአሁን በፊት ሰድቦኛል እንዲሁም በሚያሽከረክረው መኪና ሊገጨኝ ሞክሯል በማለት በቂም በቀል በመነሳት ሽጉጥ ተኩሶ ማጅራቱን ሲመታው ሲወድቅ በተደጋጋሚ ሶስት ጊዜ ተኩሶ ግንባሩን በቀኝ በኩል አንገቱንና በግራ በኩል አንገቱን በመምታት የጥይት እርሳስ ጉዳት በራስ ቅሉ የኋለኛው ክፍል፤የክብ ቅርፅ ያለው ጥይት እርሳስ የገባበት ቁስል በራስ ቅሉ የኋለኛው ክፍል፤ሳተላይት ቅርጽ ያለው የጥይት እርሳስ የወጣበት ቁስል፤በግራ ግንባሩ የፊተኛው ክፍል ላይ የአጥንት መሰበር ጉዳት፤በራስ ቅሉ ፊተኛው የታችኛው ክፍል ላይ እንዲደርስበት፤የመበሳት ጉዳት በአንገቱ ላይ እንዲደርስበት ፤በአንጎሉ የላይኛው ሽፋን ክፍል የተሰራጨ የደም መፍሰስ እንዲሁም የአየር ባንቧው የመበለዝ ጉዳት እና በዙሪያው ከፍተኛ ደረጃ ያለው የውስጥ ደም መፍሰስ ጉዳት እንዲደርሰበት እና ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓ በዚህም ከባድ የሆነ የሰው ግድያ ወንጀል ፈፅሟል በማለት ከሷል፡፡መልካም ንባብ…. Print 1898 Documents to download 251759(.docx, 142.83 KB) - 266 download(s)