Wednesday, February 23, 2022 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና አበባየሁ ተዘራ የሰ.መ.ቁ 198703 ጉዳዩ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፡፡ አመልካች በተጠሪ ላይ በሥር ፍ/ቤት አቅርቦአቸው የነበሩት ክሶች ሁለት ሲሆኑ ይዘታቸውም፡- 1ኛ ክስ፡- ተጠሪ የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 543(3) እና ደንብ ቁጥር 208/2003 አንቀጽ 26 ድንጋጌዎች በመተላለፍ የሌላውን ሰው ሕይወት፣ ጤንነት እና ደሕንነት የመጠበቅ የሙያ ግዴታ እያለባት ባለመወጣት በቀን 23/07/2010 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 1፡30 ሠዓት ሲሆን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2-57534 አ.አ የሆነ ተሸከርካሪ እያሽከረከረች ከስድስት ኪሎ ወደ መገናኛ አቅጣጫ ስትጓዝ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ቦታው ኮከበ ፅባሕ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ስትደርስ ለእግረኛ ቅድሚያ በመከልከል በእግረኛ ማቋረጫ መንገድ ላይ ስታቋጥ የነበረችውን ሟች አስምረት ንጉሴን በመኪናው የፊት ለፊት አካል ገጭታ በጭንቅላቷ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ራሷን ስታ ወድያውኑ ሕይወቷ እንዲያልፍ በማድረግ በፈጸመችው በቸልተኝነት ሰውን መግደል ወንጀል ተከሳለች የሚል ነው፡፡………. Previous Article መሀመድ አባ ቡልጉ እና የጌምቤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የሰ.መ.ቁ 198400 Next Article የደነባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት እና አቶ ጥላሁን ይስማ ሰ/መ/ቁጥር 201201 Print 15120 Documents to download 198703(.pdf, 830.74 KB) - 1318 download(s)