/ Categories: CASSATION, Cassation

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤሕግ እና እያሱ ያየህ ባየህ የሰ/መ/ቁ፡-205297

ጉዳዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው፡፡ የአሁን አመልካች በአሁን ተጠሪ ላይ በስር ፍርድ ቤት አቅርቦት የነበረው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- ተጠሪ የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 543/2 ድንጋጌን በመተላለፍ በቀን 24/09/2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡45 ሰዓት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-01771 ኢት የሆነ ተሸከርካሪ ይዞ ከሳህሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ወደ ጃክሮስ አቅጣጫ በሚያሽከረክርበት ወቅት ሳህሊተ ምህረት ቤተክርስቲን አካባቢ ሲደርስ የመንገዱን እና የእግረኞቹን ሁኔታ በማየት ጥንቃቄ አድርጎ ማሽከርከረ ሲገባው ይህን ባለማድረግ መንገዱን ከግራ ወደ ቀኝ ሲያቋርጥ የነበረውን ሟች ማቴዎስ ሀናቆ የተባለውን ግለሰብ በተሸከርካሪው የፊት ለፊት የግራ አካል በመግጨት ጥሎት ሟችም በግጭቱ ምክንያት በጭንቅላቱ ላይ በደረሰ ጉዳት ሕይወቱ ያለፈ በመሆኑ በፈጸመው በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡………………

Print
11759

Documents to download

  • 205297(.pdf, 1.16 MB) - 1496 download(s)