Friday, March 4, 2022 / Categories: CASSATION, Cassation ደሴ ከተማ ሆጤ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት -ዓ/ህግ ማዘንጊያ ደምሴ እና አዋድ ኢብራሂም የሰ/መ/ቁ፡-201746 ጉዳዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት የቀረበን የመቃወም አቤቱታን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ ነክ ጉዳዮች የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው፡፡ በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች የመቃወም አመልካች፤ የአሁን ተጠሪ እና በዚህ የሰበር ክርክር የሌለ ሆጤ ክፍለከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት ደግሞ የመቃወም ተጠሪዎች በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ያቀረበው የመቃወም አቤቱታ ይዘት በአጭሩ፡- የአከራካሪው የንግድ እና መኖሪያ ቤት ካርታ በቅይጥ የተሰራ ቢሆንም ሽያጭ በተከናወነበት ጊዜ የንግድ እንቅስቃሴው ያልቆመ እና የንግድ ፈቃዱም ያልተመለሰ በመሆኑ የሽያጭ ውሉን መሠረት በማድረግ በመኖሪያ ቤት ስም እንዲዛወርላቸው የተሰጠው ውሳኔ የመንግስትን መብት እና ጥቅም የሚጎዳ በመሆኑ ሊሰረዝ ይገባል የሚል ነው፡፡……. Print 11713 Documents to download 201746(.pdf, 820.25 KB) - 863 download(s)