Friday, May 30, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ዲቢኤል ኢንዳስትሪስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና እነ አቶ ኣረጋዊ ስዩም(5ሰዎች) የሰ.መ.ቁ 255892 የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪዎች በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመቐለ ዞን ፍርድቤት የኵሓ ክፍለከተማ ፍርድቤት በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት ተቀጥረን 1ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 5750 እየተከፈለኝ በፕሮዳከሽን ቲም ሊደር የስራ መደብ፤ 2ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 7000 እየተከፈለኝ በጥገና የስራ መደብ፤ 3ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 6500 እየተከፈለኝ በፕሮዳክሽን የስራ መደብ፤ 4ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 6900 እየተከፈለኝ በኳሊቲ የስራ መደብ፤፤ 5ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 7000 እየተከፈለኝ በወርክ ስተዲ የስራ መደብ፤ 6ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 2500 እየተከፈለኝ በኳሊቲ የስራ መደብ፤ 7ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 6700 እየተከፈለኝ በከቲንግ የስራ መደብ፤ 8ኛ ተጠሪ የወር ብር 7000 እየተከፈለኝ በካድ የስራ መደብ፤ 9ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 7000 እየተከፈለኝ በፕሮዳክሽን የስራ መደብ፤ 10ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 6000 እየተከፈለኝ በፕሮዳክሽን የስራ መደብ ስንሰራ ቆይተን በትግራይ ክልል ባጋጠመ ጦርነት ምክንያት አመልካች ስራ ሊያቆም ችሏል፡፡ ከዚህ በኋላ አመልካች ስራዬን እያቆምኩኝ ስለሆነ ውል ስለማቋርጥ የሚገባችሁን ጥቅማ ጥቅም እንድሰጣችሁ ወኪል ወክላችሁ ወደ አዲስአበባ ላኩ ያለን ቢሆንም በነበረው ጦርነት ንግግሩ ቆሟል፡፡ ከፕሪቶሪያ ውል በኋላ ደግሞ አመልካች የሰራተኞች ደመወዝ እከፍላለሁ በሚል ምክንያት የድርጅቱን ንብረት በጨረታ ሸጦ ገቢ ሰብስቦ ውዝፍ ደመወዛችንን እንዲከፍለን ብንጠይቀውም ሊከፍለን አልቻለም፡፡ ስለሆነም አመልካች ከህዳር ወር 2013ዓ.ም እስከ ነሃሴ 2013ዓ.ም የ9 ወር ውዝፍ ደመወዝ የ1ኛ ተጠሪ ብር 51‚750፤ የ2ኛ ተጠሪ ብር 63‚000፤ የ3ኛ ተጠሪ ብር 58‚500፤፤ የ4ኛ ተጠሪ ብር 62‚100፤ የ5ኛ ተጠሪ ብር 63‚000፤ የ6ኛ ተጠሪ ብር 22‚500፤ የ7ኛ ተጠሪ ብር 60‚300፤፤ የ8ኛ ተጠሪ ብር 63‚000፤ የ9ኛ ተጠሪ ብር 63‚000፤ የ10ኛ ተጠሪ ብር 54‚000 በድምሩ ብር 561‚150 እንዲከፍለን እንዲወሰንልን፤ የ2014ዓ.ም ሙሉ የ12 ወር ደመወዝ በድምሩ ብር 676‚200 እንዲከፍለን፤ የ2015ዓ.ም ክስ እስከተመሰረተበት ቀን ድረስ የ8 ወር ደመወዝ ብር 498‚000 አመልካች ከፍሎ ወደስራ እንዲመልሰን፤ ተጠሪዎች የ3 አመት ያልተጠቀምንበትን የአመት እረፍት ብር 87‚999.99 ፤ ክፍያ ለዘገየበት የ3 ወር ደመወዝ በድምሩ ብር 204‚750 በአጠቃላይ ብር 1‚949‚699.99 አመልካች እንዲከፍለን እንዲወሰንልን፡፡ የስራ ልምድ ማስረጃ፤ የስነምግባር ማስረጃ፤ ክሊራንስ፤ ከደመወዛችን ግብር እየተቆረጠ ስለመሆኑ የድጋፍ ደብዳቤ አመልካች እንዲሰጠን፤ አመልካች በ2013ዓ.ም የ9 ወር ደመወዝ እከፍላችኋለሁ በማለት የገባልንን የተስፋ ቃል እና በትግራይ ክልል ግዜያዊ መንግስት ክፈሏቸው ተብሎ መግባባት ላይ የተደረሰው የ3 ወር ደመወዝም እንዲከፍለን እንዲወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ማስረጃዎችንም አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ… Print 3701 Documents to download 255892(.pdf, 884.13 KB) - 476 download(s)