Tuesday, June 7, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ዳሽን ባንክ አ.ማ እናየአማራ ክልል ነጋዴ ሰቶች ማኅበር የሠ/መ/ቁጥር 204348 ጉዳዩ ባንክ በቼክ ክፍያ ሲፈጽም መከተል የሚገባዉን አሠራር የሚመለከት ነዉ፡፡የአሁን ተጠሪ በባህር ዳር ከተማ እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በስር 1ኛ ተከሳሽ ደረጀ ሀይማኖት እና በአመልካች ላይ በመሰረተዉ ክስ በአመልካች ዘንድ በቼክ በሚያንቀሳቅሰዉ ሂሳብ በቼክ ክፍያ ሲፈጸም መፈረም ያለባቸዉ አቶ ጥላሁን አያሌዉ፣ ወ/ሮ አለም ሞገስ ወይም በማኅበሩ ም/ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ንግስት አለማየሁ እንደሆኑ በመግለጽና የፊርማ ናሙናቸዉን በመስጠት ተጠሪ ሂሳቡን ሲያንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ሆኖም የስር 1ኛ ተከሳሽ በማኅበሩ ዉስጥ የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ ሆነዉ ሲሰሩ በሥራዉ አጋጣሚ በእጃቸዉ በገቡ ቼኮች ላይ ፈራሚዎቹ እንደፈረሙ በማስመሰል በተጭበረበረ መንገድ ፈርመዉ ለክፍያ ሲያቀርቡ አመልካች በቼኮቹ ላይ የተፈረሙ ፊርማዎች የትክክለኛ ፈራሚዎች ፊርማ መሆኑን በባንኩ ዉስጥ ካለዉ ናሙና ጋር ማገናዘብ ሲገባዉ ተገቢዉን ጥንቃቄ ሳያደርግ በተጭበረበረ መንገድ በተፈረሙ ቼኮች ለስር 1ኛ ተከሳሽ ከተጠሪ ሂሳብ ላይ ቀንሶ የከፈለዉን ብር 103,530.00 ከ9% ሕጋዊ ወለድ ጋር ከስር 1ኛ ተከሳሽ ጋር እንዲከፍሉ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ መልካም ንባብ…… Print 9661