/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

ዳሽን ባንክ አክስዬን ማህበር እና የኢትዬጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፤የኢትዬጵያ ብሔራዊ ባንክ የሰ/መ/ቁ 217557

ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው ከሳሽ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ ተከሳሽ በቀን 19/02/2012 ዓ/ም እና በቀን 04/02/2013 ዓ.ም የሰጠው አስተዳደራዊ ውሳኔ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በአዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 48 መሰረት ውሳኔው እንዲከለስ በማለት ጠይቋል፡፡ተከሳሽ በሰጠው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችንና የፍሬ ነገር ክርክሩን አቅርቧል፡፡ ባቀረበው መቃወሚያ ተከሳሽ ለጣ/ገብ በ04/02/2013 ዓ.ም የጻፈው ደብዳቤ ተከሳሽ በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በጉዳዩ ላይ ቋሚ መመሪያ እስኪወጣ ድረስ በማለት የሰጠውን መመሪያ ለማብራራት የተጻፈ ደብዳቤ እንጂ አስተዳደራዊ ውሳኔ አይደለም፡፡ በቀን 19/02/2012 ዓ.ም የወጣው መመሪያ አዋጅ ቁጥር 1183/12 ከመውጣቱ በፊት የወጣ ስለሆነ አዋጁ በመመሪያው ላይ ተፈጻሚ ሊሆን አይገባም፡፡ ፍ/ቤቱም ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለውም፡፡ በተጨማሪም ከሳሽ ተከሳሽ በሰጠው ውሳኔ ቅሬታውን በአዋጅ ቁጥር 1183/12 አንቀጽ 51 መሰረት ለተከሳሽ ተቋም የቅሬታ ማስተናገጃ አካል ያላቀረበ ስለሆነ ከሳሽ የተከሳሽን አስተዳደራዊ መፍትሄዎች አሟጦ ያልጨረሰ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለውም በማለት ተከራክሯል፡፡መልካም ንባብ……..

Print
13250

Documents to download

  • 217557(.pdf, 1.02 MB) - 1201 download(s)