Friday, March 4, 2022 / Categories: 2013, Cassation ዶ/ር ሙሉጌታ በካሎ እና እነ አቶ አማኑኤል ዮካሞ የሰ/መ/ቁ፡210525 የጉዳዩ አመጣጥ እንዲህ ነው፡-አመልካችና 1ኛ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት እያደረጉ ያሉትን የአፈፃፀም ክርክር አስመልክቶ አመልካች ለፍርዱ ማስፈፀሚያ እንዲሆን የ1ኛ ተጠሪ ንብረት እንደሆነ በመግለፅ ያቀረቡትን በአለታ ጩኮ ወረዳ 01 ቀበሌ የሚገኘውን በ1ኛ ተጠሪ ስም የሚታወቀውን ቤት ማዘጋጃ ቤቱ የቤቱን ግምት አውጥቶ እንዲልክ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቶ ግምቱን ልኮ ግራ ቀኙ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን በዚህ እለትም በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.418 አቤቱታ 3ኛ ተጠሪ የሟች ጋዲሶ ቃቂዮ ሚስት 4ኛ ተጠሪ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ መሆናቸውን እንዳረጋገጡ ገልፀው አከራካሪውን ቤት ግንቦት 07 ቀን 1985 ዓም በተደረገ ውል ከአቶ አማሎ ሄክሶ እና ወ/ሮ አስቴር አረፋይኔ ገዝተው ቤቱን እየኖሩ እንዲጠብቁ ለ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ሰጥተዋቸው እያለ በድብቅ ስም ለማዞር ሙከራ እያደረጉ መሆኑንና በስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለአፈጻጸም ሂደቱ መገመቱን እንደሰሙ ማዘጋጃ ቤቱን ጨምሮ በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ላይ ክስ አቅርበው በክርክር ላይ መሆናቸውን ገልፀው በቤቱ ላይ የወጣው የሃራጅ ሽያጭ ሂደት እንዲታገድ ብፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.418(4) እንዲሁም በቤቱ ላይ የተሰጠው የመያዢያ ትዕዛዝ እንዲነሳ ጠይቀዋል፡፡……… Print 13096 Documents to download 210525(.pdf, 928.05 KB) - 944 download(s)