Monday, June 6, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ጉምሩክ ኮምሽን እና ማራቶን ሞተርስ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሰ/መ/ቁጥር 204549 ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች መጋቢት 3 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 194905 ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ፣ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 247070 ሐምሌ 27 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ አና የኢፌዴሪ ታክስ ይግባኝ ኮምሽን በመ/ቁጥር ከመ-982 መስከረም 28 ቀን 2012 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታውን በማቅረቡ ነው፡፡ ቅሬታውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የሚቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልኝ ይገባል የሚለውን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የአሁን ተጠሪ የ2012 እና የ2014 ሞዴል የሆኑ ቱስኮን ix35 ተሽከሪካሪዎች በኢንቮይስ ዋጋ ዩ ኤስ ዲ 15,722/ዩኒት (USD 15,722/unit) እና ዩ ኤስ ዲ 16030/ዩኒት (USD 16,030/unit) ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ ሲሆን ተመሳሳይ ከሆኑ ከዋጋ መረጃ ቋት ውስጥ ከሚገኘው የ2010 ሞዴል ቱስኮን ix35 ተሽከሪካሪ መነሻ ዋጋ ዩ ኤስ ዲ 17,621/ዩኒት (USD 17,621.50/unit) ጋር ስነጻጸር ለምን የ2012 ዓ/ም እና የ2014 ዓ/ም ስሪት ተሽከሪካሪ ዋጋ እንደቀነሰ ተጠይቆ የ2010 ዓ/ም ስሪት ተሽከሪካሪው በወቅቱ ሀገር ውስጥ ያስገባቸው በልዩ ትእዛዝ (ስፔሻል ስፔስፍኬሽን) ኖሯቸው የገቡ ስለሆነ እና የ2012 እና የ2014 ዘመን ስሪት የሆኑት ተመሳሳይ ሞዴል ተሽከርካሪዎች ያነሰ አገልግሎት(less optional spedification) ስለሆነ ዋጋቸው አንሷል ያለ ሲሆን የ2010 ምርት ዘመን ተሽከርካሪው በወቅቱ ወደ ሀገር ውስጥ ስያስገባ በልዩ ትእዛዝ የገባ ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ ሳይኖር እና የቀረበው የግብይት ዋጋ በቤዚክ ቫይክል ሆኖ እያለ አሁን የሚያነሳው ክርክር ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ መልካም ንባብ…….. Print 11181 Documents to download 204549(.pdf, 1.04 MB) - 863 download(s)