Friday, July 22, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ግሩም ሆስፒታል ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ዶ/ር ተስፋዬ አልማው የሰ/መ/ቁ. 219386 ጉዳዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ጽፈው ባቀረቡት ክስ በአመልካች ሆስፒታል ውስጥ በኤክስፐርት ሜዲካል ስፔሻሊስት (ሰርጀሪ) የስራ መደብ ላይ በወር ብር 49,000.00፣ ሃርድሺፕ አሎዋንስ 19,124.00፣ እንዲሁም ለእያንዳንዱ የቀዶ ጥገና ህክምና ብር 1,000.00 እየተከፈላቸዉ ከቀን ግንቦት 07 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ አመልካች የካቲት 19 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ የሁለት ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ በመስጠት ከስራ ከህግ ውጪ ከስራ ያሰናበታቸዉ መሆኑን ጠቅሰዉ የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፈላቸዉ ይወሰንላቸዉ ዘንድ የጠየቁትን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡መልካም ንባብ…… Print 13685 Documents to download 219386(.pdf, 1.04 MB) - 1195 download(s)