/ Categories: CASSATION, Cassation

ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230

የአሁን አመልካች በምዕራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ/መ/ቁ 47863 እና በመ/ቁ በመ/ቁ 47862 በሁለቱም መዝገቦች ላይ 2ኛ ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው የክስ ይዘትም አመልካች የኢትዮጵያ የፌዴራል ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ግምቢ ቅርንጫፍ የቡና ላኪ ሸኚ ስምሪት ጣቢያ ላይ ቋሚ ሰራተኛ ሆኖ በባለሙያነት ተቀጥሮ እየሰራ እያለ በቡና ንግድ ውስጥ የማጭበርበር ድርጊት በመፈጸም ለራሱ የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ከተማ ቀበሌ 05 በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ግምቢ ቅርንጫፍ ግቢ ውስጥ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም  ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርብ የተቀሸረ ቡና ዓይነቱ እና የሰሌዳ ቁጥሩ 3-A02958 A.A በሆነ ኤፍ.ኤስ፣አር መኪና ከነጆ ከተማ ተጭኖ በፕሎምፕ ታሽጎ የቡናው ፕሎምፕ ቁጥር GM-7 በሚባል የታሸገውን በሚልክበት ጊዜ የቡናውን መጠን አጣርቶ መላክ እያለበት የተቀሸረ 129 ኩንታል ተጭኖ እያለ 100 ኩንታል በሚል እንዲሁም ከአይራ ወረዳ  በሲኖ ትራክ 210 ኩንታል ቡና የተጫነ ነዉ ተብሎ የተላከዉን ተቀብሎ በቡናው የይለፍ ወረቀት ላይ ይህንኑ መጠን በማረጋገጥ የይለፍ ወረቀት ከሰጠ በኋላ በዚሁ ቀን የተጠቀሱት መኪናዎች  በጊምቢ ከተማ ልዩ ስሙ ሰርጤ ኬላ ቦታ ላይ በቁጥጥር ስር ውለዉ ሲፈተሹ 29 እና 70 ኩንታል ቡና እንደቅደም ተከተላቸዉ  ከህግ ውጭ ጥራት በሌለው የማዳበሪያ ከረጢት ተጨምሮ እሱ በይለፍ ወረቀት ላይ ጽፎ ከሰጠው በላይ በተጨማሪ ተጭኖ ስለተገኘ የአዋጅ 1051/2009 አንቀጽ 19/5/ የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 433/2007 አንቀጽ 41(1)(ቀ) በመተላለፍ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት አስቦ በቡና ንግድ ውስጥ የማጭበርበር ወንጀል ድርጊት ፈጽሟል የሚል ነው፡፡ መልካም ምንባብ…

Print
2601

Documents to download

  • 267231(.pdf, 1.08 MB) - 850 download(s)