Friday, July 15, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ፊዳ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበርየሰበር እና አቶ ፋሲካ መርሻ መዝገብ ቁጥር 215158 ጉዳዩ ተጠሪ ከአመልካች ማኀበር ለመውጣት ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ በዚሁ አግባብ ተውስኖ ከማህበሩ ሲወጡ የሚከፈላቸውን ድርሻ ለማጣራ የሂሳብ አጣሪ ተሹሞ ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ/ም የቀረበው ሪፖርት ስህተት አለበት ተብሎ እንደገና ተስተካክሎ በቀረበው ሪፖርት ላይ ግራቀኙ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን አመልካች በአስተያየታቸው ተከፈለ የተባው የማኀበሩ ዕዳ በተጠሪ የተከፈለውን እንጅ በአመልካች የተወሰደው የብድር ገንዘብ በሪፖርቱ አለመካተቱንና ብድሩን ለመውሰድ የተያዘውን ቃለ ጉባኤ ተጠሪ ወስድው ያልመለሱ ሲሆን መውሰዳቸውን ያመኑበት ቃለ ጉባኤ ቀርቦ ሳይጣራ ሂሳቡ መሰራቱ ፍትሐዊ አይደለም በማለት ተቃውሞ አቅርበዋል፡፡ የሂሳብ አጣሪው በቀረበው ቅሬታ ላይ በሰጠው ማብራሪያ በአመልካች የቀረበው ሰነድ በአመልካች ብቻ የተፈረመ ፣ ተጠሪ ያልፈረሙበት የተሟላ ሕጋዊ ሰነድ ባለመሆኑ በሂሳብ ማጣራቱ አለመካተቱን አስረድተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም በአመልካች ለሂሳብ አጣሪው የቀረበው ሰነድ በግራቀኙ ያልተረጋገጡ በመሆኑ ሂሳቡን ለመሥራት እንደህጋዊ ሰነድ ሊያቀርቡ የማይችሉ በሂሳብ አሰራር ደንብ ተቀባይነት የሌላቸው ሰነዶች በመሆናቸው በሂሳብ አጣሪው ተቀባይነት ማጣቱ አግባብ ነው በማለት የአመልካችን ቅሬታ ውድቅ በማድረግ የቀረበው የሂሳብ ማጣራት ሪፖርት በማጽደቅ ተጣርቶ በቀረበው ሪፖርት መሠረት የተጠሪ ድርሻ ብር 42,788.5(አርባ ሁለት ሺ ሰባት መቶ ሰማኒያ ስምንት ብር ከ5/100) እንዲከፈላቸው የወሰነ ሲሆን ፣ አመልካች በውሳኔው ባለመስማማት ያቀረቡት ይግባኝ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረዙ በፍርዱ መግቢያ ላይ የተመለከተውን የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ Print 10450 Documents to download 215158(.pdf, 825.48 KB) - 793 download(s)