Monday, July 18, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ፋል ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ እና አቶ አለማየሁ ገረመው የሰበር መ/ቁ/220193 ጉዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ የስራ ግንኙነት የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን በአሁኑ አመልካች ላይ ባቀረበው ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከህዳር 03/2011 ዓ.ም ጀምሮ በከባድ መኪና ሹፌርነት የስራ መደብ በወር ብር 4000 እየተከፈለኝ ሲሰራ ቆይቼ በስራ ላይ እያለሁ በደረሰዉ አደጋ ምክንያት ለተጎዳዉ ንብረትት እንደ ጥፋተኛ በመቁጠር በህገ-ወጥ መንገድ ከስራ ያሰናበተኝ በመሆኑ ስንብቱ ህገወጥ ነዉ ተብሎ ከህገወጥ የስራ ስንብት ጋር የተያያዙ ክፍያዎች እንዲከፈለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡አመልካች በበኩሉ በሰጠው መልስ ተጠሪ ከስራ የተሰናበተው በከባድ ቸልተኝነት በፍጥነት በማሽከርከር ላይ ሳለ ከመስመር ወጥቶ በመገልበጥ አደጋ በማድረሱ በትራፊክ ሪፖርት እና በተያዘው ቃል ጉባኤ መሰረት በአዋጅ 1156/2011 አንቀጽ 27(ሸ) መሰረት በጥፋቱ የተሰናበተ በመሆኑ ስንብቱ ህጋዊ ነው፣ ስለዚህ የሚከፈለው ክፍያ የለም በማለት መከራከሩን መዝገቡ ያሣያል፡፡መልካም ንባብ……. Print 12380