/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

ፌደራል ስነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና ወ/ሮ ፍሬህይወት ተረፈ የሰ/መ/ቁ፡- 209987

ጉዳዩ ተጠሪ በአመልካች ኮሚሽን አለአግባብ ከደረጃና ከደመወዝ ዝቅ ተደርጌያለሁ በማለት ለፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ መነሻ የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ተብሎ የቀረበዉን የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ ተጠሪ በአመልካች ላይ በአስተዳደር ፍርድ ቤት ዘንድ ባቀረቡት ይግባኝ ከንብረት አወጋገድ፣ከሂሳብ አዘጋግ፣ በኦዲት ግኝት ለይ የተሰጠዉን ምክረ ሀሳብ ተግባራዊ ከማድረግ እና ሥራዎቼን በወቅቱ ከመፈጸም አንጻር የፈጸምኩት ጥፋት ሳይኖር አለአግባብ ከነበርኩበት ሥራ መደብ አንድ ደረጃ ዝቅ አድርጎ መድቦኛል፡፡ በመሆኑም አመልካች የሰጠኝ የዲሲፕሊን ውሳኔ አግባብ አይደለም ተብሎ ወደ ቀድሞ የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ደረጃ -15 ስራ መደብ ላይ እንዲመልሰኝ እንዲሁም በእግድ ምክንያት ያልተከፈለኝን የሐምሌ እና የነሐሴ ወር 2012 ዓ/ም ደመወዝ ብር 20,300.00 አመልካች እንዲከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡………..

Previous Article እነ አቶ ከበደ ደሴ እና ወ/ሮ እልፍነሽ አብደላ የሰ/መ/ቁ.209757
Next Article የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል ገቢዎች ቢሮ እና አቶ አዕምሮ ዘሪሁን የሰ/መ/ቁ.210727
Print
13156

Documents to download

  • 209987(.pdf, 832.43 KB) - 1139 download(s)