Friday, July 15, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ፓስተር ሚሊዮን ጎንጤ እና አቶ አብዱልቃድር አብዱራህማን የሰ/መ/ቁ. 104131 በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዳይ የንብረት ክርክርን የተመለከተ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ በፊንፌኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ነው፡፡ የክሱ ይዘት ባጭሩ በሰበታ ከተማ ቀበሌ 04 የሚገኝ በካርታ ቁጥር ሰ/23802/2001 የሚታወቅ አዋሳኙ በሰሜን መንገድ፣ በሌሎች አቅጣጫዎች ምሪት ከሆነ 500 ካ.ሜ ይዞታቸው ላይ አቶ ሸምሱ አወል ከወኪላቸው አቶ ሀሰን አህመድ ጋር በ16/02/02 በተደረገ ውል ሽጠውልኝ በስሜ አዙሬ በእጅ አስገብቼ ስጠቀምበት የነበረውን ቤት ተከሳሽ በቤቱ ካስቀመጥኩት አቶ ሀሽም ሁሴን ላይ በኃይል የቤቱን ቁልፍ ተቀብሎ ገብቶ ይዞት ስለሚገኝ ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት ቀን ድረስ በወር ብር 300.00 ኪራይ ታስቦ የአስራ ሰባት ወራት ኪራይ ብር 5700.00 ከፍለው ቤቱን እንዲለቁ እንዲወሰን ዳኝነት የተጠየቀበት ነው፡፡ መልካም ንባብ……. Print 13792 Documents to download 104131 (.pdf, 832.99 KB) - 949 download(s)