አቶ አብዲ አህመድ ጃማ እና እአ ምባሳደር ፒተር ገብርኤል የሰ/መ/ቁጥር 214179 አቶ አብዲ አህመድ ጃማ እና እአ ምባሳደር ፒተር ገብርኤል የሰ/መ/ቁጥር 214179 የጉዳዩን አመጣጥ ስንመለከተው ተጠሪዎችና የስር ከሳሾች በአመልካች ላይ በፋፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ በጅጅጋ ከተማ ቀበሌ 05 የሚገኘውን 13838 ካሜ ይዞታ አላግባብ የያዘባቸው መሆኑን ገልፀው ይዞታውንና ቤቱን ለቆ እንዲያስረክባቸው ላቀረቡት ክስ አመልካች ባቀረቡት መልስ የአመልካቾች የዳኝነት ጥያቄ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን ጠቅሶ ያቀረበውን መቃወሚያ ተቀብሎ ክሱ በይርጋ የሚታገድ ነው በማለት በብይን የዘጋውና ይህ ብይን በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች የፀና ቢሆንም ይህንን ብይን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ.162536 መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ፍርድ በመሻር የፋፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክርክር ያስነሳውን መሬት በተመለከተ በአሁን አመልካች እጅ ያለው ምን ያህል ነው? መሬቱ በአሁን አመልካች እጅ ሊገባ የቻለው በምን ሁኔታ ነው? የአሁን አመልካች የገዙት ቤት ነው? ወይስ ባዶ መሬት ነው? ሽያጩ በባዶ ቦታ ከሆነ በይርጋ ክርክር ላይ የሚያስከትለው ሕጋዊ ውጤት የሚለውንና መሬቱ ወደ አሁን አመልካች ያስተላለፉት ግለሰቦችም ወደ ክርክሩ በማስገባት መሬቱን እንዴት ሊያገኙ እንደቻሉ እንደዚሁም ይዞታው የሚገኝበት የጅጅጋ ከተማ ቀበሌ 05 አስተዳደር በጉዳዪ ላይ አስተያየት እንዲሰራ በማድረግና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችንም ጭምር በማጣራት እንዲወስን በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.341(1) መሰረት መዝገቡን ወደ ስር ፍርድ ቤት መልሶታል፡፡መልካም ንባብ…….
እነ አቶ ደለሳ ጅማ እና ኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክስዮን ማህበር የሰ.መ.ቁ.214136 እነ አቶ ደለሳ ጅማ እና ኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክስዮን ማህበር የሰ.መ.ቁ.214136 የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ በሥር ፍ/ቤት ባቀረበዉ ክስ ተከሳሾች የከሳሽ ማህበር አባላት ሁኖ የሚጠበቅባቸዉን ክፍያዎችን ባለመፈጸማቸዉ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ሰኔ 19 ቀን 2008 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ ከማህበሩ እንዲሰናበቱ የወሰነ ሲሆን፣ ተከሳሾች ይህን ዉሳኔ ለማሰረዝ ክስ አቅርበዉ ዉድቅ የሆነባቸዉ ሲሆን፣ በዚህ ዉሳኔ መሰረት ለማስፈጸም ሰኔ 10 ቀን 2010 ዓ.ም በተደረገዉ ጠቅላላ ጉባኤ ክፍያ ያልከፈሉ አባላት ክፍያዉንና ቅጣቱን በሁለት ወራት ዉስጥ እንዲከፍሉ፣ ይህ ካልሆነ ሱቆቻቸዉ ወደ ማህበሩ በማስገባት ክፍያዉ ተሳስቦ እንዲከፈላቸዉ የተወሰነ በመሆኑ፣ ተከሳሾች ዉሳኔዉን ለማሰረዝ ክስ አቅርበዉ ዉድቅ የሆነቸዉ ስለሆነ፣ ተከሳሾች አልከፈሏቸዉም ያለዉን ክፍያዎች በመዘርዘር፣ በጠቅላላ ጉባኤዉ ዉሳኔ መሰረት ከማህበሩ አባልነት እንዲወጡ ወይም እንዲሰረዙ እንዲወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ መልካም ንባብ…….
እነ ወ/ት ሰንሰለት ወንድይራድ እና እነ አቶ አዳነ ተ/ሃይማኖት የሰ.መ.ቁ 213758 እነ ወ/ት ሰንሰለት ወንድይራድ እና እነ አቶ አዳነ ተ/ሃይማኖት የሰ.መ.ቁ 213758 የጉዳዩ አመጣጥ 1ኛ አመልካች በስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በተጠሪዎች እና በ4ኛ አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ሟች እማሆይ ጥሩነሽ ድንበሩ አያቴ ሲሆኑ በአዲስ አበባ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የቤ.ቁ 008፤ 008/09 እና 029 ቤት የነበረ ሲሆን አያቴ ከሞቱ በኋላ የውርስ ሀብት በሆኑት ቤቶች ውስጥ እስከ 21/4/06ዓ.ም ድረስ የቆየሁ ሲሆን ከዚህ ግዜ በኋላ ተጠሪዎች እና 4ኛ አመልካች(ስር ተከሳሾች) ለብቻቸው በመያዝ ክስ እስከቀረበበት ግዜ ድረስ ብር 258,000.00 የውርስ ገንዘብ ሰብስበዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ የ1ኛ አመልካች ድርሻ ብር 12,900.00 እና ወደፊት በቤቱ ላይ ድርሻዬን እስከማገኝ ድረስ የሚኖረው ክፍያ ታስቦ እንዲከፈለኝ፤ ሟች አያታችን የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ የሆኑ አራት ልጆች ያሏቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የ1ኛ አመልካች አባት አቶ ወንድይራድ አለማየሁ አምስት ልጆች ያላቸው በመሆኑ የአባቴን ድርሻ 1/5ኛ ከቤ.ቁ 008፤ 008/09 እና 029 ድርሻ እንዲያካፍሉኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ……
ኤምቲጂዲ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር እና ኤምቲጂዲ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር. የሰ/መ/ቁ. 213747 ኤምቲጂዲ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር እና ኤምቲጂዲ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር. የሰ/መ/ቁ. 213747 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ፤ ተጠሪ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ አመልካች ያቀረበው ክስ ውልን መሠረት በማድረግ ተጠሪ ብር 10,386,376.43 እንዲከፍለው ዳኝነት ጠይቋል፡፡ መልካም ንባብ……
እነ አቶ ንጉሴ ወ/ማሪያም ወ/ሮ አሰለፈች ንጋቱ እና የሰ.መ.ቁ.213738 እነ አቶ ንጉሴ ወ/ማሪያም ወ/ሮ አሰለፈች ንጋቱ እና የሰ.መ.ቁ.213738 ጉዳዩ የቤት እና ይዞታ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካቾች ከሳሾች፤ የአሁን ተጠሪዎች ተከሳሾች፤ በዚህ የሰበር ክርክር የሌለው የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቤቶች አስተዳደር ደግሞ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የቤት ቁጥር 511 ቤት ግቢ በስተጀርባ ከደቡብ በኩል የተወረሰ እና 1ኛ ተጠሪ የምትኖበርበት የቤ.ቁ 510 የሆነ ቤት አለ፤ አመልካቾች እና 1ኛ ተጠሪ በጋራ የምንጠቀምበትን መጸዳጃ ቤት 1ኛ ተጠሪ ያለአመልካቾች ፈቃድ በማፍረስ ሰርቪስ ቤት በመስራት እንዳንጠቀምበት አድርጋለች፤ 1ኛ ተጠሪ ማንም ሳይፈቅድላት ከምንኖርበት ቤት በስተሰሜን በኩል ከአመልካቾች ቤት ግድግዳ በማስጠጋት በግምት 100 ካ.ሜ አስፋፍታ ያጠረችውን አጥር እንድታፈርስ በተደጋጋሚ ተጠይቃ ፍቃደኛ አልሆነችም፤ 2ኛ ተጠሪም ከፕላን ውጪ ያለፈቃድ የተሰራውን እንዲያፈርስልን እንዲሁም የ1ኛ ተጠሪን ሕገወጥ ግንባታ አስቁሞ በሽንት ቤት የምናገኘውን አገልግሎት ወደ ነበረበት እንዲያስመልስን፣ 1ኛ ተጠሪ ወደ ይዞታችን ገብታ ያላግባብ ያጠረችውን አጥር እንድታፈርስ ጠይቀነው ለማስፈጸም ፍቃደኛ አይደለም፤ ስለሆነም 1ኛ ተጠሪ የተገነባውን ሰርቪስ ቤት እንድታፈርስ እና መጸዳጃ ቤቱን ወደ ነበረበት እንድትመልስ አስፋፍታ ያጠረችውን አጥር በተሰጠው የፕሮፖርሽን ካርታ መሰረት እንድታፈርስ፤ 2ኛ ተጠሪም የተሰራውን ግንባታ አስፈርሶ የጋራ መጸዳጃ ቤት በ1ኛ ተጠሪ ወጪ ተሰርቶ አገልግሎት ላይ እንዲውል እንዲያደረግ አጥሩንም እንዲያስፈርስ ይወሰንልን ሲሉ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡መልም ንባብ ……..