አቶ ናሆም ተወልደ እና እነ ወ/ሮ ንግስቲ ገዛኽኝ የሰ/መ/ቁ 217149

አቶ ናሆም ተወልደ እና እነ ወ/ሮ ንግስቲ ገዛኽኝ የሰ/መ/ቁ 217149

መዝገቡ ዛሬ በችሎት የቀረበው 6ኛ ፣7ኛ 8ኛ ተጠሪዎች በግልና በጋራ ባቀረቡት የተሰጠ የዕግድ ይነሣልንና ወደ አከራካሪው ቤት እንድገባ ትዕዛዝ ይሰጥልኝ አቤቱታ የሚመለከታቸው አካላት ደርሷቸው አስተያየት እንዲያቀርቡ በዚህ ችሎት መታዘዙን ተከትሎ፤ 7ኛ እና 8ኛ ተጠሪዎች አመልካችን ማግኘት አለመቻላቸውን በመግለፅ ትአዛዙ ለአመልካች የሚደርስበት አማራጭ በመዘርዘር ባቀረቡት አቤቱታና 6ኛ ተጠሪ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ አስተዳደሩ አስተያየት መስጠቱን ተከትሎ ትዕዛዝ እንዲሰጥበት በማስፈለጉ ነው፡፡በዚህ መሰረት ጉዳዩን መርምረን ተከታዩን ትዕዛዝ ሰጥተናል…………

የእነ ኦሜጋ የወርቅ ግብይት ማህበር እና አቦቦ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት ሰበር መ.ቁ 216709

የእነ ኦሜጋ የወርቅ ግብይት ማህበር እና አቦቦ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት ሰበር መ.ቁ 216709

መዝገቡ ከቀነ ቀጠሮ በፊት ሊቀርብ የቻለው አመልካች 30/3/2014 ዓ.ም በተፃፈ ቃለ መሃላ አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡ ለዚህ ችሎት 16/3/2014 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የጋምቤላ ብ/ክ/መ/ጠ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 01080/2014 በ 16/3 /2014 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን ገልፆ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ባቀረበው ማመልከቻ መነሻነት ነው፡፡ በዚህ መሰረት መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩን ትአዛዝ ሰጥተናል፡፡…………….

ወ/ሮ ገነት ቶላ እና እነ አቶ ብርሃኑ ቶላ ሰ/መ/ቁ 214108

ወ/ሮ ገነት ቶላ እና እነ አቶ ብርሃኑ ቶላ ሰ/መ/ቁ 214108

መዝገቡ ለችሎት የቀረው 2ኛ ተጠሪ ወ/ሮ ኤልሳቤት አንበርብር ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ በዚህ ሰበር ችሎት በክርከር ላይ የምንገኘው በጋራዥ ቤቱ ላይ ሆኖ እያለ በመኖሪያ ቤት ላይ ጨምሮ እግድ የተሰጠበት በመሆኑ ከመኖሪያ ቤቱ ላይ እግድ እንዲነሳልት ስትል አመልክታለች፡፡ የአሁን አመልካቾችም መልስ እንዲሰጡበት ተደርጎ ታህሳስ 6 ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ መልስ የአፈፃፀም እግድ የተሰጠው በሚያከራክረን ንብረት ላይ በመሆኑ እግዱ ሊነሳ አይገባም ብለዋል በዚሁ መሰረት ተከታዩ ትእዛዝ ተሰጥቷል፡፡……………

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና እነ ወ/ሮ የጆቴወርቅ ኪዳኔ የሰ/መ/ቁ. 200564

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና እነ ወ/ሮ የጆቴወርቅ ኪዳኔ የሰ/መ/ቁ. 200564

ጉዳዩ የውል አለመፈጸምና የኪሣራ አከፋፈልን የተመለከተ ክርክር ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች ከሳሽ ሲሆን ተጠሪዎች ተከሳሾች ነበሩ፡፡ አመልካች ግንቦት 04 ቀን 2009 ዓ/ም በተጻፈ የክስ ማመልከቻ ያቀረበው ክስ የ1ኛ ተጠሪ ባለቤትና ከ2ኛ-8ኛ ተጠሪዎች አባት የሆኑት አቶ ቅጣው መሸሻ ከአመልካች ጋር በተደረገ የንግድ ቤት ኪራይ ውል በአዲስ አበባ ከተማ  በቀድሞ ወረዳ 05 ቀበሌ 12 የቤት ቁጥሩ 1165 የሆነ የንግድ ቤት በወር ብር 212.50 እየከፈሉ ከ1969 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ/ም ድረስ እየከፈሉ ሲጠቀሙበት ቆይተው የተከራዩትን ቤት ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ከአከራዩ ዕውቅና ውጪ ለሦስተኛ ወገን አከራይተው የማይገባ ጥቅም በማግኘታቸው ምክንያት አመልካች የኪራይ ተመኑን በማስተካከል በወር ብር 31,479.00 እንዲከፍሉ አድርጓል፡፡ አቶ ቅጣው ቅሬታ ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በዚህ መካከል አቶ ቅጣው መሸሻ ውል ሳያድሱ ሕዳር 13 ቀን 2005 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ ውል ያላደስነው ባለቤቴ ሕመም ላይ ስለቆየና ሞግዚትነትና ወራሽነት እስከምናረጋገጥ ድረስ ስለሆነ ጊዜ እንዲሰጠን በማለት በጽሁፍ አመልክተዋል፤ ውዝፍ ዕዳውን በተመለከተ የአንድ ዓመት የመክፈያ ጊዜ እንዲሰጣቸው ጠይቀው ከአመልካች ጋር የውል ሥምምነት አድርገዋል፡፡ በሥምምነቱ መሠረት ዕዳውን መክፈል ጀምረው ያቋረጡ ሲሆን እስከ ታህሳስ 17 ቀን 2009 ዓ/ም ድረስም ሲገለገሉበት ቆይተዋል፡፡ ስለሆነም የኪራይ ገንዘብ ብር 2,311,503.59 ተጠሪዎች ከወለድ ጋር እንዲከፍሉ ሲል ዳኝነት ጠይቋል፡፡……………….. 

 

አቶ መሐመድ አበራ እና አቶ ታጁ ጌታዬ የሰ/መ/ቁ፡-200555

አቶ መሐመድ አበራ እና አቶ ታጁ ጌታዬ የሰ/መ/ቁ፡-200555

ጉዳዩ የገጠር እርሻ መሬት ተጠቃሚነት መብት የሚመለከት ነዉ፡፡በስር በወግድ ወረዳ ፍርድ ቤት ተዋበች አስናቀዉ ከሳሽ የአሁን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ በዚህ መዝገብ ላይ በተከራካሪነት ያልተሰየሙት ካሳዉ መንግስቱ 2ኛ ተከሳሽ የአሁን ጣልቃ ገቦች ከሌሎች ስድስት ጣልቃ ገቦች ጋር በመሆን በጣልቃ ገብነት ተከራክረዋል፡፡ የክሱም ይዘት በወረዳዉ 02 ቀበሌ ዉስጥ በክሱ በተጠቀሱት አዋሳኞች የሚታወቅ  በ1983ዓ/ም የተመራሁበትንና በደብተር ያስመዘገብኩትን 4 ገመድ የእርሻ መሬት አመልካች ይዞብኝ ለስር 2ኛ ተከሳሽ በመሸጡና 2ኛ ተከሳሽ ቤት ሊገነባ ስለሆነ የያዙብኝን መሬት እንዲለቁልኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡………………..

First678911131415Last