አቶ ተስፋዬ አማረ እና የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ህይወት አክስዬን ማህበር የሰ/መ/ቁ 213553

አቶ ተስፋዬ አማረ እና የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ህይወት አክስዬን ማህበር የሰ/መ/ቁ 213553

ጉዳዩ የቀረበው አመልካች ከማህበሩ አባልነት እንዲሰናበቱ የተወሰነበትን አግባብነት ከመተዳደሪያ ደንባቸውና አግባብነት ካላቸው የንግድ ህጉ ድንጋጌዎች አንፃር ለመመርመር ሲባል ነው፡፡የሚል ነው መልካም ንባብ……..

የሶረታ መካነሔዋን መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን እና መሐመድ ሁሴን የሰ/መ/ቁጥር 213492

የሶረታ መካነሔዋን መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን እና መሐመድ ሁሴን የሰ/መ/ቁጥር 213492

ክርከሩ በተጀመረው በነቀምቴ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ከሣሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሣሽ ነበሩ፡፡ አመልካች ጥር 4ቀን 2013 ዓ/ም በተፃፈ ክሷ በነቀምቴ ከተማ 25 ሄክታር ስፋት ያለው መሬትን ከ1972ዓ/ም ጀምሮ ይዛ እየተጠቀመች መሆኑን ተጠሪው በምስራቅ ስለሚዋስናት በ2010ዓ/ም ከይዞታዋ ላይ 1600 ካሬ ሜትሩን በመውሰድ ስለያዘባት ክስ አቅርባ ክሣችሁን አላረጋጣችሁም ተብሎ መዝገቡ መዘጋቱ ለራሱ እንደተወሰነለት በማስመሰል እንደገና ህዳር 20 ቀን 2013ዓ/ም  500 ካሬ ሜትር ጨምሮ በጥቅሉ 2100 ካሬ ሜትር መሬት በመያዝ በመሬቱ ላይ የነበረውን 200 ባርዛፍ ቆርጦ የወሰደባት መሆኑን በመዘርዘር ያጠረውን አጥር አፍርሶ ይዞታውን እንዲለቅላት የንብረት ግምት እንድታቀርብ መብቷ እንዲጠበቅላት ጠይቃለች፡፡መልካም ንባብ……              

ወ/ሮ ወይንሸት ወርቁ ጅማ እና አቶ ፈይሳ ኃይሌ ሮቢ የሰ.መ.ቁ 213041

ወ/ሮ ወይንሸት ወርቁ ጅማ እና አቶ ፈይሳ ኃይሌ ሮቢ የሰ.መ.ቁ 213041

የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የሲናና ወረዳ ፍ/ቤት 2ኛ ከሳሽ ሆነው፤ አሁን ሰበር ክርክሩ ላይ የሌሉት ፈቃዱ ስሜ(የስር 1ኛ ከሳሽ)፤ ብርሃኑ ኃይሌ(ስር 3ኛ ከሳሽ) ሆነው በተጠሪ(ስር 2ኛ ተከሳሽ) እና አሁን ሰበር ክርክሩ ላይ በሌሉት ወ/ሮ ደሚቱ ሮቢ(ስር 1ኛ ተከሳሽ) ላይ ባቀረቡት ክስ ለስር 1ኛ ተከሳሽ አያታችን ወ/ሮ ኡርጎ ጂማ አክስቷ ሲሆኑ፤ ተጠሪ(ስር 2ኛ ተከሳሽ) ደግሞ የአያታችን የልጅ ልጅ ሲሆን አያታችን ወ/ሮ ኡርጎ ጂማ በ24/1/10ዓ.ም ሞታለች፡፡ ሟች አያታችን ያላት ልጆች 4 ይኀውም የስር 1ኛ ተከሳሽ አባት፤ ኃይሌ ሮቢ፤ የስር 1ኛ ከሳሽ አባት ስሜ መርጋ፤ የአመልካች(ስር 2ኛ ከሳሽ) እናት ሙሉ ሮቢ እና የስር 3ኛ ከሳሽ እናት ዘውዲቱ ሮቢ ናቸው፡፡ የአያታችን ልጆች አራቱም በህይወት ስለሌሉ የአያታችን ወራሾች መሆናችን ተረጋግጦ አከራካሪውን በተጠሪ(ስር 2ኛተከሳሽ) እጅ የሚገኝ በሮቤ ከተማ በኦዳ ሮቤ ቀበሌ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት እንዲሁም በክሱ ከተራ ቁጥር 2ኛ-6ኛ ስፋቱና አዋሳኙ የተገለጸው የእርሻ መሬት እንዲሁም በተጠሪ እና በስር 1ኛ ተከሳሽ እጅ የሚገኝ ኦንሾ በሚባል አካባቢ የሚገኝ ስፋቱ 16 ጥማድ የሚሆን እና አንድ ሺህ እግር ባህርዛፍ የሚገኝበትን  በማለት እንዲሁም ሌሎች የእርሻ መሬት እና መኖሪያ ቤት በመዘርዘር አያታችን ከተከሳሾች ጋር ስትጠቀምበት ቆይታ ለወራሾቹ የሚገባውን እና ስር ከሳሾች በቤተሰባችን ምትክ አያታችንን መውረስ እንድንችል እንዲረጋገጥልን እና ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ሀብትና ይዞታ ከመሰረቱ የአያታችን መሆኑ እንዲወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ……    

ሐጂ ይማም መሀመድ እና አቶ በላቸው /አብዱልሰመድ/ አደም የሰበር መ/ቁ/211987

ሐጂ ይማም መሀመድ እና አቶ በላቸው /አብዱልሰመድ/ አደም የሰበር መ/ቁ/211987

ጉዳዩ የዋሰትና ዉል የሚመለከት ነዉ፡፡የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ክርክሩ የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን በአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ተጠሪ ዋስ ጠርቶኝ ብር 278,000 እቁብ ገንዘብ ወስዶ ብር 153,000 ሳይከፍል በማቋረጡ በገባሁት የዋስትና ግዴታ መሰረት ተጠሪ ያልከፈለውን ገንዘብ የከፈልኩኝ ስለሆነ ተጠሪ ዋናውን ገንዘብ ብር 153,000 ፣የ6ዓመት ከ7 ወር ህጋዊ ወለድ ብር 92,259 እና ኪሳራ ብር 164,583 በድምሩ ብር 409,842 እንዲከፈለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ……           

እነ ተማሪ የውብዳር ጫካ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሰበር መ/ቁ/210256

እነ ተማሪ የውብዳር ጫካ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሰበር መ/ቁ/210256

ጉዳዩ የሥራ ላይ ጉዳት ካሳ ክፍያ ጥያቄ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካቾች ከሳሽ በመሆን በአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ወላጅ አባታችን ሟች አቶ ጫካ ሰቦቃ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ የዶዘር ኦፕሬተር ሆነው በማገልገል በስራ ላይ እያሉ ህይወቱ በቀን 30/01/2001 ዓ.ም ያለፈ በመሆኑ በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 110(3)(ለ) መሰረት የጉዳት ካሳና ለቀብር ማስፈፀሚያ የወጣ ወጪ ጨምሮ በድምሩ ብር 130,000.00 እንዲከፈላቸው ዳኝነት ጠይቋል፡፡ተጠሪ በበኩሉ በሰጠው መልስ የአመልካቾች አባት የሞቱት በተጠሪ መ/ቤት ስራ ላይ እያለ ሳይሆን ሲሰሩበት የነበረው ዶዘር በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ካምፕ ውስጥ አቁመው ውቤ በሚባል ወንዝ ውስጥ ነው፤የአመልካቾች አባት የሞቱት በስራ ላይ እያሉ ነው ቢባል እንኳን የሟች ደመወዝ 2000 ብር ሳይሆን ብር 1273 መሆኑን ሊከፈላቸው የሚገባ ካሳ በአንቀጽ110(3)(ለ) መሰረት በ10% መጠን ለእያንዳንዳቸው ብር 7,650 ሲሆን ለቀብር ማስፈፀሚያ የሁለት ወር ደመወዝ ብቻ ነው በማለት መከራከሩን መዝገቡ ያሣያል፡፡መልካም ንባብ……            

First678911131415Last