ወ/ሮ ፋንቱ ዘነበ (2ሰዎች) እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የእንጦጦ ስብሐት ቅድስት ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን መ.ቁ 246386 ወ/ሮ ፋንቱ ዘነበ (2ሰዎች) እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የእንጦጦ ስብሐት ቅድስት ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን መ.ቁ 246386 የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ በመሆን አመልካቾች 1ኛ እና 4ኛ ተከሳሽ በመሆን እንዲሁም በዚህ ክርክር ተካፋይ ያልሆኑት እነ ሳልሳይ ኤፍሬም ጌታቸው 4 ሰዎች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ፣ 3ኛ፣ 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል፡፡ተጠሪ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረበችው የተሻሻለ ክስ የአባ ኃይለስላሴ መገኖ ርስት እና ንብረት የሆነው አንድ ጋሻ ይዞታ ሰኔ 17 ቀን 1948 ዓ.ም በተደረገ ግልጽ ኑዛዜ የተሰጣት መሆኑን ኑዛዜው በከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 169/55 ግንቦት 13 ቀን 1955 ዓ.ም መጽደቁን እና ከሳሽ ይዞታውን ተረክባ ስታስተዳድር የቆየች መሆኑን፤ ከአንድ ጋሻ መሬት ላይ 1192 ካ.ሜ ይዞታ ቀንሳ ለአገልጋይ ካህናት ደመወዝ መክፈያ ይሆን ዘንድ የ1ኛ አመልካች ባለቤት ለነበሩት ለአቶ ኤፍሬም ጌታነህ በወር ብር 30 (ሰላሳ) ሂሳብ ለአምስት ዓመታት አከራይታ የኪራይ ውሉ እስከ 1967 ዓ.ም እየተራዘመ መቆየቱን፤ ይዞታው ያልተወረሰ እና የግል ቤቴ ነው በማለት አቶ ኤፍሬም ጌታነህ በ2004 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ እንደ ቅደም ተከተላቸው የስር 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች የነበሩት ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር እና ጉለሌ ክ/ከተማ መሬት አስተዳደር የቤት ቁጥር 815(ለ) በሚል በአቶ ኤፍሬም ጌታነህ ስም ተመዝግቦ ስም እንዲዞር ማድረጋቸውን፤ ይህንኑ ይዞታ የአቶ ኤፍሬም ጌታነህ ወኪልና የስር 4ኛ ተከሳሽ(2ኛ አመልካች) የቦርድ ሰብሳቢ በሆኑት አቶ መኮንን አያሌው እና የተጠሪ ፀሀፊ ዲያቆን ተስፋሚካኤል ታደሰ አመልካችነት ይዞታው ወደ አቶ ኤፍሬም ጌታነህ እንዲተላለፍ በመጠየቁ ህዳር 17 ቀን 2005ዓ.ም ቁጥሩ 22/69/28322/00 የሆነ ካርታ በአቶ ኤፍሬም ጌታነህ ስም ተዘጋጅቶ ተሰጥቷል፡፡ ነሐሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም በተደረገ በሽያጭ ውል ለ2ኛ አመልካች(ስር 4ኛ ተከሳሽ) ተላልፏል፡፡ የተጠሪ ይዞታ ከህግ ውጪ የተላለፈ በመሆኑ የስር 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች የይዞታውን ባለቤት በአግባቡ ሳያጣሩ በአቶ ኤፍሬም ጌታነህ ስም በ17/3/2005ዓ.ም አዘጋጅተው የሰጡትን ካርታ እንዲሰርዙ፤ በሟች አቶ ኤፍሬም ጌታነህ እና በስር 4ኛ ተከሳሽ(2ኛ አመልካች) መካከል የተደረገው በ15/12/2005ዓ.ም የተደረገው ውል እንዲሰረዝ፤ የስር 5ኛ ተከሳሽ አለአግባብ በሰጠው መረጃ መሰረት ለስር 4ኛ ተከሳሽ(2ኛ አመልካች) የተሰጠው ካርታ እንዲሰረዝ፤ በምትኩ የስር 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች ለይዞታው ለተጠሪ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲሰጡ፤ በይዞታው ላይ ያለን ንብረት 2ኛ አመልካች አንስቶ ይዞታውን ለተጠሪ እንዲያስረክብ እንዲወሰን በማለት ዳኝነት ጠይቃለች፡፡ ማስረጃዎችንም አያይዛለች፡፡ነው፡፡መልካም ንባብ…
ሲቀላ ክፍለ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና ወ/ሮ አረግዋ ጠብቀው የሰበር መዝገብ ቁጥር - 247036 ሲቀላ ክፍለ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና ወ/ሮ አረግዋ ጠብቀው የሰበር መዝገብ ቁጥር - 247036 ጉዳዩ የተጀመረው በቀድሞ ደቡብ ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልል መንግስት የአርባምንጭ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የስር ከሳሽ በአመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ ዝርዝር ይዘቱ በአጭሩ ባለቤታቸው የ ፶ አለቃ እንግዳ ንጉሴ በህይወት በነበረበት ጊዜ በመለያ ቁጥር 207 የሚታወቅ 625 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ይዞታ ከወ/ሮ ተፈሪ ወልደጊዮርጊስ የገዙ መሆኑን በመሬቱ ላይ ግብር እስከ 2007 አ.ም ድረስ የተከፈለ ቢሆንም የይዞታ ባለቤትነት ወደ አመልካች እና ሌሎች ወራሾች ስም እንዲዞርላቸው ያቀረብነው ጥያቄ ተከሳሽ ፍቃደኛ ባለመሆኑ የባለቤትነት ስም ወደ ከሳሽ ስም እንዲያዞር እንዲወሰን የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ ዓቃቤ ሀግ እና ወ/ሮ መዓዛ በልስቲየሠ/መ/ቁጥር 248735 የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ ዓቃቤ ሀግ እና ወ/ሮ መዓዛ በልስቲየሠ/መ/ቁጥር 248735 ጉዳዩ ያለደረሰኝ ግብይት የማከናወን የወንጀል ክስን የሚመለከት ሆኖ ክሱ የቀረበው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደጀን ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን በአመልካች እና በሰበር ክርክሩ የሌሉት ሁለት ግለሰቦች ላይ ቀርቦ የነበረው ክስ፡- የክልሉን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 241/2008 አንቀጽ 131/1 እና 119/1 ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር 0052005902 ፤ በንግድ ምዝገባ ቁጥር AM/EG/DEJEN/1/0001230/2010 በተጠሪ ስም የተመዘገበ በደጀን ከተማ 01 ቀበሌ በሚገኘው ሆቴልና ሉካንዳ ቤት የንግድ ሥራ በደረጃ “ለ” ግብር ከፋይነት ተሰማርተው የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅና ባለቤት ሁነው እየሰሩ እያለ ሚያዝያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 5:50 ሰዓት ላይ ደርብ አበጀና አፀደ ከተማው የተባሉ ደንበኞች አንድ በየአይነቱ ምግብ እና አንድ ሊትር የታሸገ ውሃ ተጠቅመው ደርብ አበጀ የተባለው ለተጠቀሙበት ክፍያ ብር 200.00(ሁለት መቶ) ለአስተናጋጅ ሲሰጥ የብር 135.00 (አንድ መቶ ሰላሳ አምስት) ሽያጭ ያለደረሰኝ ፈጽመዋል የሚል ነው፡፡ ተጠሪም የእምነት ክህደት ቃላቸውን ተጠይቀው ከአዲስ አበባ የሂክምና ቀጠሮ ስለነበራቸው ወንጀሉ ተፈጽሟል በተባለበት ቦታ ያልነበሩ መሆኑን፤ያለደረሰኝ ግብይት ይፈፀም አይፈፀም እንደማያውቁ፤ የድርጅቱን ሥራ በአግባቡ እንዲሰሩ ለሥር ለሥር 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች እንዳሳወቁ ገልጸው ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ተከራክረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ-ሕግ ምስክሮች የሰጡትን የምስክርነት ቃል ሰምቶ ወንጀሉ ተፈጽሟ በተባለት ቀንና ሰዓት ተጠሪ በድርጅቱ ውስጥ አለመኖራቸው በቃቤ-ሕግ ምስክሮች መነገሩን ጠቅሶ አመልካች የሥር 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በተመደቡበት የስራ ኃላፊነት ብቁ ሠራተኞች መሆናቸውን በማመን ወደ ህክምና የሄዱ መሆኑ ተረጋግጧል በሚል በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 141 መሠረት በነፃ ያሰናበተ ሲሆን፤አመልካች ተጠሪ ከክሱ በብይን በነፃ መሰናበታቸውን በመቃወም ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 መሠረት መሰረዙን ተከትሎ አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩ የፌደራል በመሆኑ ለክልል ሰበር ሰሚ ችሎት ሊቀርብ አይገባም በሚል ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ የሰበር ቅሬታ የቀረበው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩ የፌዴራል ነው በሚል የሰበር አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ ባለመቀበል የሰጠውን ፍርድ በመቃወም ሆኖ የሰበር ቅሬታው በአጭሩ፡- ተጠሪ በደጀን ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት በሆቴልና ሉካንዳ ቤት ንግድ ዘርፍ በደረጃ “ለ” በክልል ግብር ከፋይነት ተመዝግበው ሲሰሩ በክልሉ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 240/2008 አንቀፅ 79/2 እንዲሁም በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 241/2008 አንቀፅ 19/3 የተመለከተውን ደረሰኝ የመስጠት ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 241/2008 አንቀፅ 131/1 እና 119/1 የተመለከተውን በመተላለፍ በፈፀሙት ወንጀል በደጀን ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦባቸው ክርክር ተደርጎ የወረዳው ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣኑ ክርክሩን አይቶ የሰጠውን ውሳኔ የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በይግባኝ ሰሚነቱ የተመለከተውን የመጨረሻ ውሳኔ ያገኘን የክልል ጉዳይ ተጠሪ በክልሉ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋይ እንጅ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ባልሆኑበት በክልል ግብር ከፋይነታቸው ለፈፀሙት የወንጀል ጥፋት ተጠያቂ የሚሆኑት በክልል የታክስ አስተዳደር አዋጅ መሆኑ እየታወቀ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር አጣሪው ችሎት ጉዳዩን የማየት የሥረ-ነገር ሥልጣን የለኝም በማለት አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አለመቀበሉ የአማራ ብሔራዊ ክልል ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ ቁጥር 223/2007 አንቀፅ 17/1 ፤ እንዲሁም የክልሉን ፍርድ ቤቶች ለማቋቋም ተሻሽሎ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 281/2014 አንቀፅ 24 ድንጋጌዎችን የሚቃረን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት በሰበር ሰሚ ችሎቱ እንዲታረምላቸው ጠይቃዋል፡፡መልካም ንባብ…
አቶ ተገኝ ደምሴ ወንድአፍራሽ እና ወ/ሮ አየለች ደሳለኝ እንዳሻው የሰበር መ/ቁጥር 248810 አቶ ተገኝ ደምሴ ወንድአፍራሽ እና ወ/ሮ አየለች ደሳለኝ እንዳሻው የሰበር መ/ቁጥር 248810 ጉዳዩ የንብረት መፋለም ክስን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.13375 በቀን 18/11/2011 ዓ/ም የሰጠውን ውሳኔ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችሎት በመ/ቁ. 04927 በቀን 01/04/2012 ዓ/ም የቀረበውን ይግባኝ ቅሬታ ባለመቀበል የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በትዕዛዝ በማጽናት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል አመልካች ሰኔ 09 ቀን 2015ዓ/ም በተጻፈ አቤቱታ ቅሬታ በማቅረባቸው ነው፡፡ ከሥር ፍርድ ቤቶች የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ በ23/03/2008ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰው የቤት ቁጥር 144 የሆነ በ 2921 ካ.ሜ የመሬት ይዞታ ላይ ያረፈ ሰባት ክፍሎች ያሉት ፎቅ ቤትና ሰርቪስ ቤት ሟች እህታችን በግዥ አግኝተው ሲጠቀሙበት ቆይተው በ1962 ዓ/ም በነበረው የሶማሊያ ጦርነት ወጥተው ስላልተመለሱ ተጠሪ ከወንድሜ ሻምቤል ፈለቀ ደሳለኝ ጋር በመሆን የእህታችንን መጥፋት እና ወራሽነት በ1972 ዓ/ም አሳውጀውን ቤቱ በውርስ ለተጠሪ እና ወንድሜ ከተላለፈ በኃላ፤ የተጠሪ ወንድም በ1988 ዓ/ም በውርስ ያገኙትን የአከራካሪውን ቤት ድርሻ በስጦታ ያስተላለፉልኝን ጨምሮ ከጠቅላላ ይዞታ ውስጥ በ1394 ካ/ሜ ላይ ካርታ በስሜ 11/09/1996 ዓ/ም የተሰራልኝ ሲሆን ቀሪው 1527 ካ/ሜ ይዞታ እና ፎቅ ቤት ወደ ፊት ይሰራልሻል ተብዬ ነበር፤ከዚያ በኋላ ሟች እህቴ ያከራየቻቸው የተከሳሽ ቤተሰቦችከ1969 ዓ/ም ጀምሮ በቤት ውስጥ መኖር ቀጠሉ፤ አመልካች ምንም መብት ሳይኖረው በምዕራብ አቅጣጫ የሚገኙትን አምስት ክፍል ቤቶችን ይዞ በማከራየት፤ ከ2001 ዓ/ም እስከ 2004 ዓ/ም ተለጣፊ ቤቶችን በመስራት እየተጠቀሙ በመሆኑና ቤቱንም ለማስረከብ ፈቃደኛ ስላልሆኑ በሕገ-ወጥ መንገድ የሠሩትን ቤት አፍርሰው የቤት ቁጥር 144 እና ይዞታውን ለቀው እንዲያስረክቡ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…
ቁአቶ ጌታቸው ጎነሞ እና አቶ ፍሰሀ ታምራትየሰ/መ/ቁ249348 ቁአቶ ጌታቸው ጎነሞ እና አቶ ፍሰሀ ታምራትየሰ/መ/ቁ249348 የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ የአመልካችን ክርክር ውድቅ በማረግ ቦታውን ለቀው እንዲወጡ ወሰነ፡፡በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር ተሰኝተው ለሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርበው ፤ ፍርድ ቤቱ አመልካች የሰሩት ተጠሪ ሳይቃወሙ ነው በማለት የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመሻር ለአመልካች ወሰነ፡፡ ተጠሪ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ቅሬታ ቢያቀርቡም የከፍተኛውን ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጸና፡፡ተጠሪ ለደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታ አቅርበው የሰበር ችሎቱ የከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎቶችን ውሳኔ በመሻር የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክል ነው በማለት ለተጠሪ ወስኗል፡፡ ይህ የሰበር ቅሬታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው፡፡መልካም ንባብ…