እነ ወ/ሮ ማርታ በቀለ እና አቶ ሚልኪያስ መንገሻ የሰበርመ.ቁ.-213330

እነ ወ/ሮ ማርታ በቀለ እና አቶ ሚልኪያስ መንገሻ የሰበርመ.ቁ.-213330

መዝገቡ ተከፍቶ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለው አመልካች /ቾች/ ነሐሴ 21 ቀን /2013 ዓ.ም በተፃፈ  ማመልከቻ በ ፌደራል ጠቅላይ  /ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.199317 በ ግንቦት 25 ቀን 2013 ዓ.ም የተሰጠ ውሳኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት አለበት በመግለፅ በሰበር ታይቶ እንዲታረምላቸው በሚል የቀረበ ነው፡፡ በመሆኑም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡…….

እነ አበበ ጨዶ እና አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ አስ/ፅ/ቤት የሰበር መ.ቁ 212620

እነ አበበ ጨዶ እና አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ አስ/ፅ/ቤት የሰበር መ.ቁ 212620

መዝገቡ ለዚህ ችሎት 10/12/2013 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ ደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ  ችሎት በመ/ቁ 35305 በ ግንቦት 18 ቀን 2013 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን ገልፆ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ባቀረበው ማመልከቻ መነሻነት  ነው፡፡ በዚህ መሰረት መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩን ትአዛዝ ሰጥተናል፡፡………….

አቶ አንዱዓለም ፈረደ እና እነ አለም ረዳ ወልዱ የሰ/መ/ቁ፡-208809

አቶ አንዱዓለም ፈረደ እና እነ አለም ረዳ ወልዱ የሰ/መ/ቁ፡-208809

ጉዳዩ የመፋለም ክርክርን የሚመለከት ሆኖ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጀመረው ክርክር ተጠሪዎች ከሣሽ አመልካች ሁለተኛ ተከሣሽ አቶ ፈንታው ሰይድ አንደኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪዎች ታሕሳስ 4ቀን 2011ዓ/ም በተፃፈ ክሳቸው ዜግነታቸው ኤርትራዊያን የሆኑ ባልና ሚስት መሆናቸውን ከገለፁ በኋላ በአንደኛ ተጠሪ ስም የተመዘገበ ኮምቦልቻ ከተማ ቀበሌ 05 መለያ ቁጥሩ 117 የሆነውንና በ218.5 ካሬ ሜትር ላይ የተሰራውንና ግምቱ 100 ሽኅ ብር የሚያወጣውን ቤት በ1990 ዓ/ም ሁለተኛ ተጠሪ በሰራ ምክንያት ወደ ሌላ ቦታ ሲዛወሩ ቤታቸውን እንዲያስተዳድርላቸው 2ኛ ተጠሪ ለአመልካች ውክልና ሰጥተው ከቆዩ በኋላ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በተደረሰው ስምምነት ተጠሪዎች ከኤርትራ ሲመለሱ የቤታቸውን ስመ-ንብረት ወደ አንደኛ ተከሣሽ (አቶ ፈንታው ሰይድ) መዞሩን አመልካች የገለፁላቸው መሆኑን በመዘርዘር ከ1991ዓ/ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 2010 ዓ/ም በየወሩ 400 ብር በሚታሰብ ኪራይ በድምሩ 96 ሽህ ብር እንዲከፍላቸው፣ ቤቱንም እንዲያስክቧቸው ጠይቀዋል፡፡…………….    

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አስ/ፅ/ቤት እና አቶ ሰለሞን ወዳጆ የሰ/መ/ቁ 208603

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አስ/ፅ/ቤት እና አቶ ሰለሞን ወዳጆ የሰ/መ/ቁ 208603

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 261471 ግንቦት 17ቀን 2013 ዓ/ም የአመልካቾችን ይግባኝ አቤቱታ ከመረመረ በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት መሰረዙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብሎ እንዲታረምላቸው አመልካቾች በመጠየቃቸው ነው፡፡ ጉዳዩ የመፋለም ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ በተጀመረበት የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ አመልካች 1ኛ ተከሣሽ፣ ወ/ሮ አሰገደች ዝናቡ 2ኛ ተከሣሽ፣ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ጣልቃ ገቦች ተጠሪ ደግሞ ከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

ተጠሪ ጥቅምት 28 ቀን 2011 ዓ/ም በተፃፈ የተሻሻለ ክሱ በመምህርነት ሲያገለግል ከነበረበት ወለጋ ሲመልስ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የቤት ቁጥር 889 የሆነና በደብተር ቁጥር 5/25444 የተመዘገበውን ቤቱን  የያዘበትን 1ኛ አመልካች ቤቱን እንዲያስረክበው ሲጠይቀው ፈቃደኛ ባለመሆኑ አቤቱታውን ለጠቅላይ ዐ/ሕጉ አቅርቦ አንደኛ አመልካች ሰኔ 12ቀን 1982ዓ/ም በተፃፈ ለጠቅላይ ዐ/ሕግ በሰጠው መልሱ ቤቱን ለተጠሪ ለማስረከብ ከ50 በላይ ጠያቂዎች በመኖራቸው እንዲሁም ሁለተኛ ተከሣሽ በቤቱ ከ14 ቤተሰቦች በላይ የሚያስዳድሩበት መሆኑን በመግለፅ በቅደም ተከተል እንደሚያስተናግደው ከገለፀ በኋላ እስካሁን ድረስ ቤቱን ያልመለሰለት መሆኑን በመዘርዘር ምንም መብት ሣይኖራቸው የያዙበትን ቤት ለቀው እንዲያስረክቡት የተሰበሰበው ኪራይና ክሱ ከቀረበበት ጊዜጀምሮ 2ኛ ተከሣሽ ኪራይ እንዲከፍሉት እንዲወሰንባቸው ጠይቋል፡፡……………….

የአቶ ተመስገን ተሻገር እና አቶ ሞላ ታረቀኝ ሰ/መ/ቁ፡-207003

የአቶ ተመስገን ተሻገር እና አቶ ሞላ ታረቀኝ ሰ/መ/ቁ፡-207003

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 267605 ሚያዚያ 15 ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ተበሎ እንዲታረምለት አመልካች ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሣሽ አመልካች አንደኛ ተከሣሽ በዚህ ሰበር ክርክር ያልተጠሩት ወ/ሮ ፅጌ ወ/ጊዮርጊስ ሁለተኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

ተጠሪ ጥር 23 ቀን 2011ዓ/ም ፅፈው ባቀረቡት ክስ በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የቤት ቁጥር አደስ ተበሎ የሚታወቀው ቤትና ይዞታቸውን አመልካች በሰሜን አቅጣጫ 60 ሣ.ሜትር  ሁለተኛ ተከሣሽ የነበሩት በደቡብ አቅጣጫ 30 ሣ.ሜትር ገፍተው አጥረው የያዘቡባቸው ከመሆናቸውም በላይ የአጥርና የፍሣሽ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ለመስራት የግንበታ ፈቃድ ለማውጣት የመጣው ባለሙያን ይዞታውን አላስለካም ያሉ መሆኑን በመዘርዘር እያንዳንዳቸው ገፍተው የያዙትን ይዞታ እንዲለቁላቸው እንዲወሰንባቸው ጠይቀው አመልካች ይዞታቸውን ከ1983ዓ/ም ጀምረው አጥረው ይዘው ከሚገለገሉ በስተቀር የተጠሪን ይዞታ አለማጠራቸውን ተከራክረዋል፡፡………………

First7891012141516Last