የእነ ወ/ሮ እቴነሽ አሰፋ ወኪል መኮንን በቀለ እና ወ/ሮ በላይነሽ አሰፋ የሰ/መ/ቁ 208950 የእነ ወ/ሮ እቴነሽ አሰፋ ወኪል መኮንን በቀለ እና ወ/ሮ በላይነሽ አሰፋ የሰ/መ/ቁ 208950 ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው ከሳሾች በቀን 03/11/2010 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ ሟች ወ/ሮ ቦጋለች ሺበሺ አያታችን ሲሆኑ በመ/ቁ 67546 በቀን 05/03/2010 ዓ.ም የሟች አባታችን መላኩ ወ/ሰማንያ ተተኪ ወራሽነታችንን አረጋግጠናል፡፡ 2ኛ ተከሳሽ (የአሁን 1ኛ አመልካቸ) ደግሞ የሟች እናታቸው ልጅና ወራሽ ናቸው፡፡ ሟች ወ/ሮ ቦጋለች ሺበሺ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ቀበሌ 16 የቤ/ቁ 325 የተመዘገበ ቤት ነበራቸው፡፡ ከሳሾች በጋራ 25% ለእያንዳንዳችን ከሳሾች ደግሞ 1/24ኛ ድርሻ፤ እንዲሁም 2ኛ ተከሳሽ 25% ድርሻ አለን፡፡ 1ኛ ተከሳሽ ሟች በቀን 11/08/1996 ዓ.ም ኑዛዜ አድርገዋል በማለት በመ/ቁ 07365 በቀን 07/03/2010 ዓ.ም ኑዛዜ ማረጋገጣቸውን በ02/11/2010 ዓ.ም ተረድተናል፡፡ በኑዛዜው ላይ ያለው ፊርማ የሟች ወ/ሮ ቦጋለች ሺበሺ ካለመሆኑም በላይ ኑዛዜው በህግ የተቀመጠውን ፎርማሊቲ በተለይ በፍ/ህ/ቁ 880 እስከ 897 የተጠቀሱትን ድንጋጌዎች አሟልቶ የተዘጋጀ ስላልሆነ በፍ/ህ/ቁ 2008 መሰረት የፊርማ ምርመራ ሊደረግ ይገባል፡፡መልካም ንባብ……
አቶ ኃይለ ስላሴ ዮሐንስ (ሸካ ኖርዲክ ማርና ሰም ልማት) እና አልፋ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 1 የጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር የሰ/መ/ቁጥር 207336 አቶ ኃይለ ስላሴ ዮሐንስ (ሸካ ኖርዲክ ማርና ሰም ልማት) እና አልፋ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 1 የጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር የሰ/መ/ቁጥር 207336 አመልካች ሚያዝያ 17 ቀን 2008 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው ክስ ከተጠሪ ጋር ህዳር 25 ቀን 2008 ዓ.ም በተደረገ የጭነት ማጓጓዝ ውል ለአውሮፓ ኤክስፖርት የተዘጋጀ 20.88 ሜትሪክ ቶን ማር ወደ ጅቡቲ ወደብ ለማጓጓዝ ተስማምቶ ንብረትነቱ የስር 2ኛ ተከሳሽ የሰሌዳ ቁጥሩ 37607-07420 የሆነን ተሽከርካሪ በመመደብ ሲያጓጉዝ አሽከርካሪው በፍጥነት በማሽከርከሩ በደረሰ አደጋ ወደብ ላይ ሳይደርስ በጅቡቲ ክልል አባይ በሚባል ቦታ መኪናው ወድቆ ማሩ ፈሶ በመበላሸቱ ለውጪ ገበያ እንዲቀርብ ሳይደረግ ቀርቷል፡፡ ተጠሪ የማሩን ዋጋ ከግምት ውስጥ ሳያስገባ በገባው የጉዞ መድን ውል አመልካች ከደረሰው ጉዳት ጋር የማይመጣጠን ብር 524,843.71 ብቻ ተቀብሏል፡፡ አመልካች ከማሩ ማግኘት ይገባው የነበረው ገንዘብ፣ ማሩን ለማስመርመር ለኤስዲኤስ የተከፈለ ገንዘብ፣ የምርቱን ናሙና ለመላክ፣ ለማስመርመር እና ለመጋዘን ኪራይ የተከፈለ ገንዘብ ብር 1,975,635.52 ሲሆን በተጠሪ ትዕዛዝ ናይል ኢንሹራንስ የከፈለው ገንዘብ ተቀናሽ ተደርጎ የሚቀረውን ብር 1,449,694.90 አደጋው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዲሁም አደጋው ከደረሰበት ቀን ናይል ኢንሹራንስ ብር 524,843.71 እስከከፈለበት መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ ያለውን ወለድ ተከሳሾች በአንድነት እና በነጠላ እንዲከፍሉ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነተ ጠይቋል፡፡ መልካም ንባብ…….
አቶ ገብረመድህን ግዛቸው እና እነ ወ/ሮ መሰረት መኮንን ሰ/መ/ቁ. 105332 አቶ ገብረመድህን ግዛቸው እና እነ ወ/ሮ መሰረት መኮንን ሰ/መ/ቁ. 105332 የክርክር መነሻ አመልካች ኪንግ ማክሬል ካሬና ሬስቶራንት በሚል መጠሪያ በሚታወቀው የንግድ ድርጅት ውስጥ እንዲሰራ ሁለተኛ ተከሳሽ /ሁለተኛ ተጠሪ/ ያቀረበውና ሰኔ 24 ቀን 2005 ዓ.ም ሁለተኛ ተከሳሽ ከስራ ያባረረው መሆኑን ገልፆ፣ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ መሰረት መብቱ እንዲከበርለት ሀምሌ 29 ቀን 2005 ዓ.ም የተፃፈ ክስ አቅርቧል፡፡ ሁለተኛ ተከሳሽ ከከሳሽ ጋር የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት የለኝም፡፡ የኪንግማክሬል ካፌና ሬስቶራንት ባለቤት አይደለሁም የከሳሽም አሰሪ አይደለሁም የሚል የክስ መቃወሚያ በማቅረቡ ከሳሽ /አመልካች/ የካቲት 21 ቀን 2006 ዓ.ም ክሱን በማሻሻል በሁለቱ ተጠሪዎች ላይ ክሱን በማቅረብ ፍርድ ቤቱ ከሁለቱ ሰዎች ማንኛቸው ለስራ ውሉ ከህግ አግባብ ውጭ መቋረጥ ኃላፊ እንደሆኑ ለይቶ እንዲወሰንለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡ መልካም ንባብ…….
ፓስተር ሚሊዮን ጎንጤ እና አቶ አብዱልቃድር አብዱራህማን የሰ/መ/ቁ. 104131 ፓስተር ሚሊዮን ጎንጤ እና አቶ አብዱልቃድር አብዱራህማን የሰ/መ/ቁ. 104131 በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዳይ የንብረት ክርክርን የተመለከተ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ በፊንፌኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ነው፡፡ የክሱ ይዘት ባጭሩ በሰበታ ከተማ ቀበሌ 04 የሚገኝ በካርታ ቁጥር ሰ/23802/2001 የሚታወቅ አዋሳኙ በሰሜን መንገድ፣ በሌሎች አቅጣጫዎች ምሪት ከሆነ 500 ካ.ሜ ይዞታቸው ላይ አቶ ሸምሱ አወል ከወኪላቸው አቶ ሀሰን አህመድ ጋር በ16/02/02 በተደረገ ውል ሽጠውልኝ በስሜ አዙሬ በእጅ አስገብቼ ስጠቀምበት የነበረውን ቤት ተከሳሽ በቤቱ ካስቀመጥኩት አቶ ሀሽም ሁሴን ላይ በኃይል የቤቱን ቁልፍ ተቀብሎ ገብቶ ይዞት ስለሚገኝ ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት ቀን ድረስ በወር ብር 300.00 ኪራይ ታስቦ የአስራ ሰባት ወራት ኪራይ ብር 5700.00 ከፍለው ቤቱን እንዲለቁ እንዲወሰን ዳኝነት የተጠየቀበት ነው፡፡ መልካም ንባብ…….
አቶ ኪዳኔ ኃይለማርያም ገብረስላሴ እና እነ ወ/ሮ ሳራ ወልደገሪማ ነ የሰ/መ/ቁጥር 210037 አቶ ኪዳኔ ኃይለማርያም ገብረስላሴ እና እነ ወ/ሮ ሳራ ወልደገሪማ ነ የሰ/መ/ቁጥር 210037 ክርክሩ የብድር ውልን መነሻ ያደረገ ሲሆን ጉዳዩ በተጀመረበት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ተጠሪ ከሳሽ፣ አመልካች 1ኛ ተከሳሽ እንዲሁም 1ኛ ተጠሪ 2ኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡መልካም ንባብ……….