ወ/ሮ ጎበኔ ጉዬ እናአቶ ሁሴን ሶራ የሰበር መዝገብ ቁጥር 249911 ወ/ሮ ጎበኔ ጉዬ እናአቶ ሁሴን ሶራ የሰበር መዝገብ ቁጥር 249911 ጉዳዩ የንብረት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በሻሸመኔ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ሲጀምር ተጠሪ ከሳሽ ፣አመልካች 2ኛ ተከሳሽ፣ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው ጀማል ከድር 1ኛ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡ የሰበር አቤቱታለዚህ ችሎት የቀረበው የሻሸመኔ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/14689 በቀን25/01/2015 ዓም የሰጠውን ውሳኔ የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 45377 በቀን 15/02/2015 ዓ/ም ቅሬታውን ባለመቀበል ትዕዛዝ በመስጠቱ፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 407521 በቀን 18/05/2015 ዓ/ም እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በመ/ቁ/ 421547 በቀን 24/08/2015 ዓ/ም የሥር ፍረድ ቤቶች ውሳኔ በማጽናት የሰጡትን ውሰኔ በመቃወም አመልካች ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ/ም የተጻፈ ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።መልካም ንባብ…
የአቶ ከበደ ተክለማርያም ወራሾች፡-እነ አቶ ደረጀ ከበደ.(4ሰዎች)እና እነ አቶ ደረጀ ተስፋዬየሰ/መ/ቁ253101 የአቶ ከበደ ተክለማርያም ወራሾች፡-እነ አቶ ደረጀ ከበደ.(4ሰዎች)እና እነ አቶ ደረጀ ተስፋዬየሰ/መ/ቁ253101 ጉዳዩ የውርስ ማጣራትን ተከትሎ የቀረበ የሚስት የንብረት ድርሻን የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን የአመልካቾች አዉራሽ ሟች አቶ ከበደ ተክለማሪያም አመልካች፣የአሁኑ ተጠሪዎች በሌላ በኩል ተጠሪዎች በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአመልካቾች አውራሽ በስር ፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ይዘት በአጭሩ ልጃቸው ሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ ልጅ ሳይወልዱ በመሞታቸው ከባለቤታቸው አስር አለቃ ተስፋዬ ደስታ ጋር ያፈሩት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የቤት ቁጥር 682 የሆነው ንብረት እና ከቤቱ የተሰበሰበው የኪራይ ሀብት በውርስ አጣሪ ተጣርቶ የድርሻዬ እንዲለይ በሚል ያቀረቡ ሲሆን የሟቿ አባት የሆኑት አቶ ከበደ ተክለማሪያም በመሞታቸው አመልካቾች በተተኪ ወራሽነት ወደ ክርክሩ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ተጠሪዎችም በቀረበው አቤቱታ ላይ መልስ በመስጠት የአቤቱታው መነሻ የሆነው የውርስ ሀብቱም ተጣርቶ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡በውርስ አጣሪው ተጣርቶ የቀረበው ርፖርት ይዘትም የአስር አለቃ ተስፋዬ ደስታ በመ/ቁ 158482 ህዳር 03 ቀን 2013 ዓ.ም የውርስ ሀብት ተጣርቶ በጸደቀው የውርስ ሀብት ሪፖርት አስር አለቃ ተስፋዬ ደስታ ሰኔ 09 ቀን 1995 ዓ.ም ባደረጉት ኑዛዜ መሰረት የክርክር መነሻ በሆነው ቤት እና ይዞታ ላይ የሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ ድርሻ 1/4ኛ ነው የሚል ውሳኔ የተሰጠ በመሆኑ አመልካቾች የሟቿን ድርሻ የቤቱን እንደዚሁም ከኪራይ የሚገኘውን ገቢ 1/4ኛ ድርሻ እንዲካፈሉ የሚል ነው፡፡ግራ ቀኙም በቀረበው የውርስ አጣሪ ሪፖርት ላይ ያላቸውን አስተያየት የሰጡ ሲሆን ፍ/ቤቱም የሟች አስር አለቃ ተስፋዬ ደስታ የውርስ ሀብት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 158482 ላይ ተጣርቶ የፀደቀ ሲሆን በዚህ የጸደቀው የውርስ አጣሪ ሪፖርት ላይ የውርስ ሀብት የሆነውን ቤት ሟች አስር አለቃ ተስፋዬ ደስታ በሰኔ 09 ቀን 1995 ዓ.ም ባደረጉት ኑዛዜ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የቤት ቁጥር 682 ከሆነው ቤት እና ይዞታ ላይ የሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ ድርሻ 1/4ኛ መሆኑን ፍ/ቤቱ የቀረበው በውርስ አጣሪ ሪፖርት ተረጋግጧል፣አመልካቾችም ይህን ውሳኔ አላሻሩም፣ከቤት ቁጥር 682 ላይ የሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ የሚስትነት ድርሻ ግማሽ ድርሻ እንደሆነ የሚገልጽ ውሳኔ አላቀረቡም፣አመልካቾች ይህ ውሳኔ ስለመሻሩም ያቀረቡት ማስረጃ የለም፣ ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ የሟች አስር አለቃ ተስፋዬ ደስታ ሚስት ስለመሆኗ እና ቤት እና ይዞታውን በጋራ አፍርተዋል በሚል የተሰጠ ውሳኔ አልቀረበም፣ ሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ ከሟች አስር አለቃ ተስፋዬ ደስታ ጋር በመሆን ያፈሩ በመሆኑ ግማሹ የሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ የሚስትነት ድርሻ ሊሆን ይገባል የሚል ክርክር ሊቀርብ የሚገባው በቤተሰብ ችሎት እንጂ በዚህ በተያዘው ችሎት ባለመሆኑ የሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ ድርሻ ከሆነው 1/4ኛ ድርሻ ላይ አመልካቾች እያንዳንዳቸው 1/4ኛ ድርሻ አላቸው።የቤት ኪራይን ገቢን በተመለከተ የተሰበሰበው ገቢ በአጠቃላይ ብር 444,400 ስለሆነ ከዚህ ገንዘብ ላይ ሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ ድርሻ ብር 111,100 በመሆኑ ሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ ድርሻ ላይ አመልካቾች እያንዳንዳቸው 1/4ኛ ማለትም ብር 27,775 ብር የሚደርሳቸው ሆኖ ለተለያዩ ጉዳዮች የወጣው ወጪ ብር 108,259.11 በመሆኑ የሟች ወ/ሮ ጥሩዓለም ከበደ ድርሻ ብር 27,064.78 ስለሆነ ከዚህ ላይ አመልካቾች እያንዳንዳቸው ብር 6943.75 የሚለከፍሉት ውርስ ሃብት ዕዳ ይሆናል በማለት በውርስ አጣሪ የቀረበውን ሪፖርት አጽድቆታል፡፡መልካም ንባብ…
የሰበሶራ ሴኪዩሪቲ ኃ/የተ/የግ/ማ እና ታቦር ሴራሚክስ ውጤቶች አ/ማህበር የሰ/መዝገብ ቁጥር -253253 የሰበሶራ ሴኪዩሪቲ ኃ/የተ/የግ/ማ እና ታቦር ሴራሚክስ ውጤቶች አ/ማህበር የሰ/መዝገብ ቁጥር -253253 ጉዳዩ የተጀመረው በሲዳማ ብሄራዊ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የስር ከሳሽ በተከሳሽ ላይ ያቀረበው ክስ ይዘቱ በአጭሩ የፋብሪካውን ደህንነት ለማስጠበቅ የጥበቃ ውል ከተከሳሽ ጋር በ02/05/2014 ዓ.ም መፈፀሙን ተከሳሽ ግዴታውን ባለመወጣት በተለያዩ ጊዜ የከሳሽ ንብረት የተሰረቀ በመሆኑ የንብረቱ ግምት ብር 4,825,295.00 (አራት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሃያ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና አምስት ብር) ጉዳት ያደረሰ በመሆኑ በፍ/ብ/ህ አንቀፅ 2028 መሰረት እንዲከፍል የሚል ነው፡፡ ከተከሳሽ በኩል ለክሱ የተሰጠው መልስ ይዘቱ በአጭሩ ከሳሽ ተሰረቀብኝ ብሎ ያቀረበው 38 ዕቃ በውላችን መሰረት ተቆጥሮ ያልተሰጠ ንብረት በመሆኑ በተከሳሽ ጥፋት ጉዳት አልደረሰበትም፡፡ ጠፉ ከተባሉት ንብረቶች ውስጥ በውላችን አንቀፅ 4.2 መሰረት ያልተረከብኩትና የማላውቀው ነው፡፡ ተሰረቀ ከማለት ውጪ ከየትኛው መጋዘን እንደተሰረቀ እና የትኛው እቃ እንደተሰረቀ በስማቸው ዘርዝሮ አለማቅረቡ እቃዎቹ አለመሰረቃቸውን የሚያሳይ ከመሆኑ በተጨማሪ በተለያዩ ቦታ ላይ እርስ በርስ የሚጋጭ የዋጋ ዝርዝር አቅርቧል፡፡ የጠቀሳቸው እቃዎች ለመያዝ ፍቃድ የለውም፡፡ በስርቆት ጥርጣሬ በተደረገ ቆጠራ የከሳሽ ሰራተኞች በኦዲት ይጠየቃሉ እንጂ ከውጪ እየጠበቁ ያሉ ጥበቃዎች ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉበት አግባብ ስለሌለ ተከሳሽ ለከሳሽ የሚከፍለው ገንዘብ የለም ተብሎ እንዲወሰን የሚል መልስ ከሰጡ በኃላ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርቧል፡፡ ዝርዝሩ በአጭር ከሳሽ ጠፍቶብኛል በሚል ምክንያት በመካከላችን ያለውን ውል በ28/01/2014 ዓ.ም አቋርጦ ያለበትን ውዝፍ ደመወዝ የ 10 ወር 834,652.21 (ስምንት መቶ ሰላሳ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ሁለት ብር ከሃያ አንድ ሳንቲም) በተጨማሪ ለተመደቡ ለአራት ጥበቃዎች የ 6 ወር ብር 55,643.47 (ሃምሳ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አርባ ሶስት ብር ከአርባ ሰባት ሳንቲም) በውላችን መሰረት ያለማስጠንቀቂያ ውሉን በማቋረጡ ብር 92,739.12 ውል ለማፍረሱ ቅጣት 5,000.00 ብር በአጠቃላይ ብር 990,816.23 (ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሺህ ስምንት መቶ አስራ ስድስት ብር ከሃያ ሶስት ሳንቲም) ከሳሽ ለተከሳሽ እንዲከፍል የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…
የአቶ ጂወይድ ሰይድ ሳሊም እና አቶ አብዱልዋሲ አህመድ ኢብራሂም(2ሰዎች) ሰ/መ/ቁ. 253517 የአቶ ጂወይድ ሰይድ ሳሊም እና አቶ አብዱልዋሲ አህመድ ኢብራሂም(2ሰዎች) ሰ/መ/ቁ. 253517 ጉዳይ የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረቡትን ክስ መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡ አመልካች ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት ክስ ይዘትም በአጭሩ ታህሳስ 10 ቀን 2008 ዓ.ም በተደረገ የሊዝ ዉል መሠረት የፕላስቲክ ፋብሪካ እና የአስተዳደር ሕንፃዎችን በአጠቃላይ በ10,000,000.00 ብር የሚገመት ግንባታ አጠናቅቄ የፕላስቲክ ባግ ማምረቻ ማሽኖችን ወደ አገር ለማስገባት ስሞክር መንግስት በሚከተለዉ አረንጓዴ ፖሊሲ ልማት ምክንያት በመከልከሌ ህንፃዉን ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ሳከራየሁ ቆይቻለሁ፤ በዚህም መሠረት ለ1ኛ ተጠሪ ከነሐሴ 11 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም በወር 20,000.00 ኪራይ እየከፈሉ ሲሰሩበት ቆይተዋል፡፡ ይሁንና 2ኛ ተጠሪ ከመመሪያ ዉጪ ፋብሪካዉን አልከፍትም በሚል ያለማስጠንቀቂያ ካርታዬን በመሰረዝ ያለምንም ጨረታ ለ1ኛ ተጠሪ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የሰጠዉ በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ ከመስከረም 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያለዉን የኪራይ ገንዘብ እንዲከፍሉ እና ይዞታዉን እንዲያስረክቡኝ እንዲሁም ካርታዉ እንዲመክን ወይም ይህ ቢታለፍ የህንፃዉ ግምት በባለሙያ ተገምቶ የሚመጣዉን ብር 10,000,000.00 እንዲከፈለኝ ይወሰንልኝ የሚል ነዉ፡፡ ይህ ጉዳይ የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረቡትን ክስ መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡ አመልካች ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት ክስ ይዘትም በአጭሩ ታህሳስ 10 ቀን 2008 ዓ.ም በተደረገ የሊዝ ዉል መሠረት የፕላስቲክ ፋብሪካ እና የአስተዳደር ሕንፃዎችን በአጠቃላይ በ10,000,000.00 ብር የሚገመት ግንባታ አጠናቅቄ የፕላስቲክ ባግ ማምረቻ ማሽኖችን ወደ አገር ለማስገባት ስሞክር መንግስት በሚከተለዉ አረንጓዴ ፖሊሲ ልማት ምክንያት በመከልከሌ ህንፃዉን ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ሳከራየሁ ቆይቻለሁ፤ በዚህም መሠረት ለ1ኛ ተጠሪ ከነሐሴ 11 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም በወር 20,000.00 ኪራይ እየከፈሉ ሲሰሩበት ቆይተዋል፡፡ ይሁንና 2ኛ ተጠሪ ከመመሪያ ዉጪ ፋብሪካዉን አልከፍትም በሚል ያለማስጠንቀቂያ ካርታዬን በመሰረዝ ያለምንም ጨረታ ለ1ኛ ተጠሪ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የሰጠዉ በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ ከመስከረም 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያለዉን የኪራይ ገንዘብ እንዲከፍሉ እና ይዞታዉን እንዲያስረክቡኝ እንዲሁም ካርታዉ እንዲመክን ወይም ይህ ቢታለፍ የህንፃዉ ግምት በባለሙያ ተገምቶ የሚመጣዉን ብር 10,000,000.00 እንዲከፈለኝ ይወሰንልኝ የሚል ነዉ፡፡መልካም ንባብ…
ቻይና ሬል ወይስ ሰቨንዝ ግሩፕ ኦሞ ወንዝ ታርጫ መንገድ ስራ ድርጅት እና አቶ ደረሰ ደሳለኝ -የሰ/ መ/ ቁ 254490 ቻይና ሬል ወይስ ሰቨንዝ ግሩፕ ኦሞ ወንዝ ታርጫ መንገድ ስራ ድርጅት እና አቶ ደረሰ ደሳለኝ -የሰ/ መ/ ቁ 254490 ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁን አመልካች ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 18418 ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በቀን 05/12/2015 አ.ም ይግባኙ አያስቀርብም በማለት ሰርዞታል፡፡ የአሁን አመልካች በነዚህ ውሳኔዎች ላይ ቅር በመሰኘት ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት በቀን 23/02/2016 አ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ ይዘቱም ተጠሪ በክሳቸው እንዲወሰንላቸው የጠየቁት የዳኝነት መጠን ብር 800,800 (ስምንት መቶ ሺህ ስምንት መቶ ብር) ካሣ ሆኖ እያለ ህጉን ባልተከተለ መንገድ፣ ገለልተኛ ባልሆኑ ሰዎችና ቦታው ላይ እንዳልገኝ ተደርጎ ከቅን ልቦና ውጪ ከሳሽ ከጠየቀው ዳኝነት በላይ የተሰራዉ የባለሞያ ማጣሪያ አመልካችን እጅግ የሚጎዳ በመሆኑና የሞያው ባለቤት በሆነው በከርሰ ምድር ባለሞያ እንዲጣራ ተደርጎ የተጎዳ ንብረት ካለ በግራ ቀኙ ገማች ኮሚቴ አባላት ተመርጠው እንዲገምቱ ተደርጎ ውሳኔ እንዲሰጠኝ በስር ፍርድ ቤት ጠይቄ እያለ ይህ ሳይደረግ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ተሸሮ ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዲወሰንልኝ በማለት የሰበር አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡ መልካም ንባብ…