የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና አቶ አሰድ አህመድ ሁሴን የሰበር መ/ቁ/ 224485 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና አቶ አሰድ አህመድ ሁሴን የሰበር መ/ቁ/ 224485 ከስር ክርክሩ አመጣጥ ሲታይ በ6ኛዉ ሀገር አቀፍ ምርጫ በሶማሌ ክልል መስከረም 20 ቀን 2014ዓ.ም በተካሄደዉ ምርጫ በመዩ ሙሉቄ ምርጫ ክልል የተደረገው ምርጫ ጊዜያዊ ውጤት ከተገለጸ በኋላ የብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ወ/ሮ አያን አብዲ ባቀረቡት ቅሬታ በድምጽ መስጫ ዕለት መራጮች የፈለጉትን ፓርቲ ወይም ግለሰብ በነፃነት እንዳይመርጡ መከልከላቸውን፣ የምርጫ አስፈፃሚዮች ጫና እንደነበረ፣ የድምፅ አሰጣጥ ስርዓት ህግን ያልተከተለ፣መስፈርት የማያሟሉ መራጮች እንዲመርጡ መደረጉ፣በመራጮች ላይ ዛቻና መስፈራሪያ እንደነበር፣የካቢኔና የሚሊሻ አባላት ዛቻና ማስፈራራት በመጠቀም መራጮች ለቅሬታ አቅራቢዋ የሰጧቸውን ድምጽ ከድምጽ ምርጫ ሳጥን ውስጥ እንዲወጣ በማድረግ የማጭበርበር ተግባር የተፈፀመባቸው መሆኑን በመግለጽ በዚህ ምርጫ ክልል የተካሄደው ምርጫ ውጤት ተሰርዞ ድጋሚ ምርጫ እንዲከናወን በሚል አቤቱታ ማቅረባቸዉን መዝገቡ ያሳያል፡፡ መልካም ንባብ……….
አጋር የጥበቃ አገልግሎት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና እነ አቶ ተሰማ ዳንጉሪ የሰ/መ/ቁጥር 221210 አጋር የጥበቃ አገልግሎት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና እነ አቶ ተሰማ ዳንጉሪ የሰ/መ/ቁጥር 221210 ከክርክሩ ሒደት መገንዘብ እንደቻልነው ተጠሪዎች ጥቅምት 09 ቀን 2014 ዓ.ም ባቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ በጥበቃ ሰራተኝነት ሲያገለግሉ መቆየታቸውን፣ በሀገሪቱ ውስጥ ከተከሰተው ወቅታዊ ችግር ጋር በተያያዘ ከህዳር 2013 ዓ.ም እገዳ ከተጣለበት ጊዜ ጀምሮ የአመት እረፍት እና የአገልግሎት ተሰልቶ እንዲከፍለን ብንጠይቀውም ፍቃደኛ ስላልሆነ ያልተጠቀምንበት የዓመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ፣ የስራ ስንብት ክፍያ፣ካሳ፣ዉሳኔ እስከሚሰጥበት ድራስ ያልተጠቀምንበት ደመወዛችን፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣የዘገየ ክፍያ እንዲሁም የስራ መፈለጊያ እንዲከፈለን ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋ መልካም ንባብ……….
ወ/ሮ ዮዲት ብርሃኑ እና አቶ ሳምሶን አምባዬየሰ/መ/ቁጥር 221154 ወ/ሮ ዮዲት ብርሃኑ እና አቶ ሳምሶን አምባዬየሰ/መ/ቁጥር 221154 ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች የካቲት 9 ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 275237 ጥር 5 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 256800 ሚያዝያ 18 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታዋን በማቅረቧ ነው፡፡ ቅሬታዋም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የምትቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልኝ ይገባል የምትለውን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ ቀለብ ሰጪ ለራሱ ማድረግ የማይችለውን አቅም ሳይኖረው ቀለብ እንድሰጥ ልገደድ አይገባም፡፡ ቀለብ ሲወሰን የቀለብ ሰጪውን የገንዘብ አቅም እና የተቀባዩ ችግር ግምት ውስጥ ሊያስገባ ይገባል፡፡ የአሁን ተጠሪ በየወሩ ከ10,000 ብር በላይ እያገኘ፣ ኮንዶሚኒየም ቤቱ የማይከራይ ሲሆን፣ እኔ በልብስ ቤት ተቀጥሬ በወር ከማገኘው 1000 ብር የማይበልጥ ገቢ 4000 ብር ቀለብ በወር እንድከፍል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው፡፡ መልካም ንባብ……….
ወ/ሮ መሰለች ገ/ህይወት እና ወ/ሮ ትዕግስት ድጋፌ የሰ.መ.ቁ 220962 ወ/ሮ መሰለች ገ/ህይወት እና ወ/ሮ ትዕግስት ድጋፌ የሰ.መ.ቁ 220962 ጉዳዩ የይግባኝ ማስፈቀጃን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁን አመልካች የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ 103666 ሐምሌ 22 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሠጠውን ውሳኔ በመቃወም ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሬጅስትራር መስከረም 18 ቀን 2014 ዓ.ም የተጻፈ የይግባኝ አቤቱታ ያቀረቡ መሆኑን፣ በዚሁ ቀን የስር ፍ/ቤት መዝገብ እንዲላክ የተመራላቸውና የስር ፍ/ቤትም መስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም የመዝገቡን ግልባጭ አዘጋጅቶ የሰጣቸው መሆኑን፣ በዕለቱ የአመልካች ጠበቃ በደረሰበት ድንገተኛ ሕመም ሐኪም ቤት ገብቶ እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ሕክምና ላይ ቆይቶ እንደተሻለው ይግባኙን ለከፍተኛው ፍ/ቤት ሬጅስትራር ቢያቀርቡም የመዝገቡ ግልባጭ በአመልካች እጅ የቆየ በመሆኑ ለችሎቱ እንዲያቀረቡ የነገራቸው መሆኑን በመግለጽ ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም የተጻፈ የይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታ ከሕክምና ማስረጃ ጋር አያይዘው ይግባኙ እንዲፈቀድላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ……….
ናፊሳ ዱቄት ፋብሪካ እና ቄስ ሰለሞን ዓለማየሁ የሰ/መ/ቁ. 220133 ናፊሳ ዱቄት ፋብሪካ እና ቄስ ሰለሞን ዓለማየሁ የሰ/መ/ቁ. 220133 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ተከሳሽ፤ ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ፡፡ ተጠሪ ጥር 25 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ ያቀረቡት ክስ ከአመልካች ጋር በነበረን የሥራ ግንኙነት የፋብሪካውን የምርት ውጤት እያጓጓዝኩ በተለያየ ቦታ ለመሸጥ እና የድካም ዋጋ ሊከፈለኝ ተስማምተን ከ2005 እስከ 2009 ዓ/ም ድረስ ምርቱን እየሸጥኩ ገንዘቡን ለአመልካች ገቢ አድርጊያለሁ፡፡ አመልካች የድካም ዋጋዬን ለመክፈል እምቢተኛ በመሆኑ አመልካች የእርቅ ሽማግሌዎች መርጦ በእኛ መካከል ያለውን ያለመግባባት ከተመለከቱ በኋላ ብር 706,788.00 እንዲከፍለኝ አስታርቀውናል፡፡ በእርቅ የተስማማነውን ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ ስላልሆነ ገንዘቡን አመልካች እንዲከፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ አመልካች ባቀረበው መልስ በፍርድ ቤት የተረጋገጠ የእርቅ ውል ስላልሆነ ልከሰስ አይገባም፣ ተጠሪ ጋር የቀረብንን ገንዘብ በሽምግልና ጠየቅን እንጂ ከተጠሪ ጋር ሕዳር 02 ቀን 2010 ዓ/ም ያደረግነው እርቅ ውል የለም በማለት ተከራክሯል፡፡ መልካም ንባብ……….