ዲቢኤል ኢንዳስትሪስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና እነ አቶ ኣረጋዊ ስዩም(5ሰዎች) የሰ.መ.ቁ 255892 ዲቢኤል ኢንዳስትሪስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና እነ አቶ ኣረጋዊ ስዩም(5ሰዎች) የሰ.መ.ቁ 255892 የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪዎች በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመቐለ ዞን ፍርድቤት የኵሓ ክፍለከተማ ፍርድቤት በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት ተቀጥረን 1ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 5750 እየተከፈለኝ በፕሮዳከሽን ቲም ሊደር የስራ መደብ፤ 2ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 7000 እየተከፈለኝ በጥገና የስራ መደብ፤ 3ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 6500 እየተከፈለኝ በፕሮዳክሽን የስራ መደብ፤ 4ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 6900 እየተከፈለኝ በኳሊቲ የስራ መደብ፤፤ 5ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 7000 እየተከፈለኝ በወርክ ስተዲ የስራ መደብ፤ 6ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 2500 እየተከፈለኝ በኳሊቲ የስራ መደብ፤ 7ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 6700 እየተከፈለኝ በከቲንግ የስራ መደብ፤ 8ኛ ተጠሪ የወር ብር 7000 እየተከፈለኝ በካድ የስራ መደብ፤ 9ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 7000 እየተከፈለኝ በፕሮዳክሽን የስራ መደብ፤ 10ኛ ተጠሪ የወር ደመወዝ ብር 6000 እየተከፈለኝ በፕሮዳክሽን የስራ መደብ ስንሰራ ቆይተን በትግራይ ክልል ባጋጠመ ጦርነት ምክንያት አመልካች ስራ ሊያቆም ችሏል፡፡ ከዚህ በኋላ አመልካች ስራዬን እያቆምኩኝ ስለሆነ ውል ስለማቋርጥ የሚገባችሁን ጥቅማ ጥቅም እንድሰጣችሁ ወኪል ወክላችሁ ወደ አዲስአበባ ላኩ ያለን ቢሆንም በነበረው ጦርነት ንግግሩ ቆሟል፡፡ ከፕሪቶሪያ ውል በኋላ ደግሞ አመልካች የሰራተኞች ደመወዝ እከፍላለሁ በሚል ምክንያት የድርጅቱን ንብረት በጨረታ ሸጦ ገቢ ሰብስቦ ውዝፍ ደመወዛችንን እንዲከፍለን ብንጠይቀውም ሊከፍለን አልቻለም፡፡ ስለሆነም አመልካች ከህዳር ወር 2013ዓ.ም እስከ ነሃሴ 2013ዓ.ም የ9 ወር ውዝፍ ደመወዝ የ1ኛ ተጠሪ ብር 51‚750፤ የ2ኛ ተጠሪ ብር 63‚000፤ የ3ኛ ተጠሪ ብር 58‚500፤፤ የ4ኛ ተጠሪ ብር 62‚100፤ የ5ኛ ተጠሪ ብር 63‚000፤ የ6ኛ ተጠሪ ብር 22‚500፤ የ7ኛ ተጠሪ ብር 60‚300፤፤ የ8ኛ ተጠሪ ብር 63‚000፤ የ9ኛ ተጠሪ ብር 63‚000፤ የ10ኛ ተጠሪ ብር 54‚000 በድምሩ ብር 561‚150 እንዲከፍለን እንዲወሰንልን፤ የ2014ዓ.ም ሙሉ የ12 ወር ደመወዝ በድምሩ ብር 676‚200 እንዲከፍለን፤ የ2015ዓ.ም ክስ እስከተመሰረተበት ቀን ድረስ የ8 ወር ደመወዝ ብር 498‚000 አመልካች ከፍሎ ወደስራ እንዲመልሰን፤ ተጠሪዎች የ3 አመት ያልተጠቀምንበትን የአመት እረፍት ብር 87‚999.99 ፤ ክፍያ ለዘገየበት የ3 ወር ደመወዝ በድምሩ ብር 204‚750 በአጠቃላይ ብር 1‚949‚699.99 አመልካች እንዲከፍለን እንዲወሰንልን፡፡ የስራ ልምድ ማስረጃ፤ የስነምግባር ማስረጃ፤ ክሊራንስ፤ ከደመወዛችን ግብር እየተቆረጠ ስለመሆኑ የድጋፍ ደብዳቤ አመልካች እንዲሰጠን፤ አመልካች በ2013ዓ.ም የ9 ወር ደመወዝ እከፍላችኋለሁ በማለት የገባልንን የተስፋ ቃል እና በትግራይ ክልል ግዜያዊ መንግስት ክፈሏቸው ተብሎ መግባባት ላይ የተደረሰው የ3 ወር ደመወዝም እንዲከፍለን እንዲወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ማስረጃዎችንም አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…
የቻይና ኮሚኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒየ እና እነ ወ/ሮ ለምለም ተሾመ (4ሰዎች)ሰ/መ/ቁ 256185 የቻይና ኮሚኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒየ እና እነ ወ/ሮ ለምለም ተሾመ (4ሰዎች)ሰ/መ/ቁ 256185 ጉዳዩ የጉዳት ካሳን የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ በተጀመረው የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ፣2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ እንደዚሁም አመልካች፣3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች ጣ/ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡1ኛ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት የክስ ይዘት በአጭሩ 2ኛ ተጠሪ በራያ ቆቦ ወረዳ 01 ቀበሌ የሚገኘውን ይዞታዬን የባቡር መንገድ ድልድይ ሲሰራ መሬቴንሙሉ በሙሉ በጎርፍ በማስወሰድ ዘላቂ ጉዳት ያደረሰብኝ በመሆኑ የ1ዓመት አላባ 28‚800 ሲሆን የ10 ዓመት አላባ 288‚000 (ሁለት መቶ ሰማኒያ ስምንት ሺህ) እንዲሁም መሬት ሙሉ በሙሉ የተጎዳ በመሆኑ ምትክ መሬት እንዲሰጠኝ አልያም ብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሺህ) ካሳ እንዲከፈለኝ የሚል ነው፡፡2ኛ ተጠሪም በሰጡት መልስ በንዑስ ተቋራጭነት የዋናው ስራ ተቋራጭ ከሆነው አመልካች በተሰጠን ዲዛይን መሠረት የሠራን ሲሆን ከተሰጠን ዲዛይን ውጭ የሠራነው ነገር የሌለ በመሆኑ አመልካች ወደ ክርክሩ እንዲገባልን ሚል ነው፡፡አመልካችም ወደ ክርክሩ እንዲገባ ተደርጎ ክሱ በይርጋ የሚቋረጥ ነው በሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በፍሬ ነገር ላይም በሰጡት መልስ የሠራነውን የባቡር ድልድይ ዲዛይን 3ኛ ተጠሪ ምንም አይነት ችግር የሌለበት መሆኑን አረጋግጦ ያፀደቀው ነው፣ጉድለት ካለበትም ሰሪው ተከሳሽ ስለሆነ ኃላፊነት ያለባቸው ተከሳሽ እና 3ኛ ተጠሪ ናቸው፣ጉዳቱ የደረሰው ተፈጥሮአዊ በሆነ ጎርፍ ምክንያት ነው እንጂ ድልድዩ በመሰራቱ ምክንያት አይደለም፡፡መሬቱ ካሳ የተከፈለበት ነው በሚል 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ወደ ክርክሩ እንዲገቡ ትዕዛዝ እንዲሰጥ የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡3ኛ ተጠሪም ይርጋን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት በማንሳት የተከራከሩ ሲሆን በፍሬ ነገር ክርክራቸውም መሬቱ ካሳ የተከፈለበት ነው፣ ከተከሳሽ ጋር ምንም አይነት ውል የለንም፣ውላችን ከአመልካች ጋር ሲሆን በውላችን አግባብ ማንኛውንም ኃላፊነት የሚወስደው ራሱ ተቋራጩ ነው ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ፍ/ቤቱም በዲዛይኑ ውስጥ የፍሳሽ ማስወገጃው ከድልድዩ የሚወጣውን ጎርፍ ተከትሎ ቋሚ ስራ ያልተሰራለት ስለመሆኑ በቀረቡት ምስክሮች ተረጋግጧል፣የፍሳሽ ማስወገጃ በዲዛይን ውስጥ ስራውም ተካቶ አልተሰራም፣የባቡር መስመር ስራውን ዲዛይን የሚሰራው አመልካች ሲሆን የሚያፀድቀው ደግሞ 3ኛ ተጠሪ በመሆኑ ያልተነጣጠለ ኃላፊነት አለባቸው፣ለከሳሽ የሚከፈለውን የጉዳት ካሳ በተመለከተ የ2008 እና የ2009 አላባ በ2 ዓመት ይርጋ የተቋረጠ ሲሆን የ2010 ለ2011 እና የ2011 ለ2012 ያለው የሰሜን ወሎ ዞን ገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም በላከው ውጤት አግባብ እና የቀሪው የ10 ዓመት ዘላቂ የመፈናቀል ካሳ የአመቱ በ10 ዓመት ተባዝቶ በመጣው ውጤት ሊወሰን ይገባል በማለት በአጠቃላይ 375‚060 ባልተነጣጠለ ኃላፊነት እንዲከፍሉ በሚል ወስኗል፡፡መልካም ንባብ…
ወ/ሮ አያልነሽ ሚሻል እና የሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ሃዋሳ ጽ/ቤት የሰበር መ/ቁ 257607 ወ/ሮ አያልነሽ ሚሻል እና የሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ሃዋሳ ጽ/ቤት የሰበር መ/ቁ 257607 አመልካች ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ባቀረቡት አቤቱታ ኮሚሽኑ የግዥና አስዳደር ባለሙያ ለመቅጠር ባወጣዉ ማስታወቅያ ተመዝግቤ ለፁሁፍ ፈተና በቀረብኩበት ወቅት አብረዉኝ ከሚፈተኑት መካከል ቆንጂት በዛብህ የተባሉ ተፈታኝ ወደ ፈተና አዳራሽ ወረቀት ይዘዉ በመግባት ከወረቀቱ ላይ መልስ ሲሰሩ የነበር በመሆኑ በወቅቱ ፈተኝ ለነበሩት ለአቶ ቤዛዩ ከበደ በሌላዋ ተፈተኝ መቅደስ ካህሳይ አማካኝነት የተነገራቸዉ ቢሆንም ፈታኙ ወረቁቱን ወደ ቦርሳ እንድታስገባ ብቻ በማድረግ ትኩረት ሳይሰጡ አልፈዉታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በቃል ፈተና ወቅት እኔን ለመጉዳ አግባብነት የሌላቸዉ ጥያቄዎች ሲያቀርቡ የነበር በመሆኑ የዉድድሩ ዉጤት አድሏዊ እና አግባብነት የሌለዉ በመሆኑ ዉድቅ ሊደረግ ይገባል በሚል ቅሬታቸውን ዘርዝረው አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…
የወ/ሮ በላይነሽ ወንድማገኘሁ ወራሾች አቶ በሻዳ ወርቁ ደፈሩአቶ ደበበ ወርቁ ደፈሩ እና አቶ ደበበ ቱሉ (3ሰዎች)ሰ.መ.ቁ:- 257723 የወ/ሮ በላይነሽ ወንድማገኘሁ ወራሾች አቶ በሻዳ ወርቁ ደፈሩአቶ ደበበ ወርቁ ደፈሩ እና አቶ ደበበ ቱሉ (3ሰዎች)ሰ.መ.ቁ:- 257723 የይዞታ ክርክር የሚመለከት ሲሆን ተጠሪዎች በአመልካቾች አውራሽ ላይ ክርክሩ በጀመረበት የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘቱ ሲታይ፡- አመልካቾች በአዲስአበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ሰርቲ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ከነበራቸው ቦታ በምስራቅ መንገድ፣ በምእራብ የአቶ ደቻሳ መኖሪያ ቤት በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ ኤሌክስቴራዞና እምነበረድ ፋብሪካ የሚያዋስኑት ስፋቱ 5057 ካሬ ሜትር ህዳር 1 ቀን 1984 ዓ.ም በተፃፈ የስጦታ ውል ለተጠሪዎች ያስተላለፉ መሆኑን፤ ተጠሪዎችም ለ30 ዓመት በ3ኛ ተጠሪ ስም ግብር በመገበር በእጃችን አድርገን አትክልቶችን በመትከልና በመዝራት የምናስተዳድረውን ይዞታ የአመልካቾች አውራሽ የሆኑት (ወ/ሮ በላይነሽ ወንድማገኝ)(ስር ተከሳሽ) መብትና ጥቅም ሳይኖራቸው ህጋዊ ይዞታችንን በጉልበት ነጥቀው የያዙ በመሆኑ ለቀው እንዲወጡ እንዲወሰንልን የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…
አማኑኤል ያዘዉ ተፈሪ እና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 265504 አማኑኤል ያዘዉ ተፈሪ እና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 265504 አመልካች በቀን 26/09/2016 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ ከላይ በተመለከተዉ መሠረት በተሰጠ የጥፋተኝነትና የቅጣት ዉሳኔ ላይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን ይዘቱም በአጭሩ ጫማዎቹን ለሕዝብ ግልጽ ከሆነ ገበያ ቦታ ላይ ገዝቼ ለቤተሰቦቼና ለጎረቤት ልጆች ለመለገስ የገዛሁት እንደሆነና ከዉጭ አገር እንዳላስገባሁ በመከላከያ ማስረጃዎቼ አስረድቼ እያለሁ ጥፈተኛ መባሌ ሕጉን ያልተከተለና የማስረጃ ምዘና ስህተት የተፈጸመበት ነዉ፡፡ባቀረብኩት ሦስት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች መሠረት መቀጣት የሚገባኝ በእርከን 11 ስር በአንድ ዓመት ከስምንት ወር መሆን ሲገባ ሁለት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ከተያዙለት ከስር 2ኛ ተከሳሽ ጋር እኩል በ2(ሁለት) ዓመት ጽኑ እስራት እንድቀጣ መወሰኑ ስህተት ነዉ፡፡እንዲሁም ለአባይ ግድብ 3 ጊዜ ቦንድ መግዛቴ፣ሁለት ጊዜ ደም በመለገስ በጎ አድራጎት ሥራ መፈጸሜ እና ለአረንጋዴ አሻራ ልማት የሚሰማሩ ሰዎችን በራሴ መኪና በማመላለስ ላበረከትኩት አስተዋጽኦ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 86 መሠረት የቅጣት ማቅለያ ተደርጎ እንዲያዝልኝ የጠየቅሁት ሳይያዝልኝ መታለፉ ስህተት ስለሆነ እንደልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ተይዞ ተሻሽሎ ይወሰንልኝ በማለት አመልክቷል፡፡መልካም ንባብ…