አቶ ጀማል ሹራቤ እና አቶ ጀማል አቤ የሰ/መ/ቁ፡-205675

አቶ ጀማል ሹራቤ እና አቶ ጀማል አቤ የሰ/መ/ቁ፡-205675

ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ አመልካች DLA መከስከሻ ማሽን ባለ 32 ምጣድ የሆነ ለተጠሪ ሊሸጥለት ከተስማማ በኋላ እና ብሩን ከተቀበለ በኋላ ተጠሪን በሀሰተኛ ክስ በመክሰስ ማሽኑን መልሶ በመውሰድ ቢያንስ የ90 ቀናት ጥቅም በቀን በብር 4,000.00 ሒሳብ የክስክሶ ስራ እና ዘርን አፈር ማልበስ ሰርቶ የሚያስገኘውንና በአጠቃላይ ብር 360,000.00 ያሰጣኝ ስለሆነ ወጪ እና ኪሳራን ጨምሮ እንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረበውን ክስ መነሻ ያደረገ ሲሆን አመልካች በአዳማ ልዪ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የነበረ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበር፡፡………

ወ/ሮ ሀለዊያ አብዱጀባር እና እነ ሂላል አበዱጀባር የሰ/መ/ቁ፡-206828

ወ/ሮ ሀለዊያ አብዱጀባር እና እነ ሂላል አበዱጀባር የሰ/መ/ቁ፡-206828

ጉዳዩ እንዲህ ነው፡፡ የአሁን አመልካች ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የአፈፃፀም አቤቱታ ቀደም ሲል ከአሁን ተጠሪዎች ጋር በዚያው ፍርድ ቤት በነበራቸው ክርክር ለክሱ ምክንያት ከሆነው ቤትና ይዞታ ላይ ለአሁን ተጠሪዎች እናት በፍርድ ቤቱ በፀደቀው ስምምነት ላይ ከተጠቀሰው ውጭ ባለው ቤት እና ይዞታ ላይ በስማቸው ካርታ እና ፕላን እንዲሰራላቸው ለክፍሉ ይዞታ አስተዳደር ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ይጠይቃሉ፡፡ ይህንኑ የአፈፃፀም አቤቱታ አስመልክቶ በአሁን ተጠሪዎች በኩል ምን መከራከሪያ እንደቀረበ የስር ፍርድ ቤት መዝገብ አያሳይም፡፡ በሌላ በኩል በዚህ የሰበር ሰሚ ችሎት ክርክር ተካፋይ ያልሆኑት አቶ አህመድ መሃመድ የተባሉት ግለሰብ የአፈፃፀም አቤቱታ የቀረበበት ቤት እና ይዞታ የአሁን ተጠሪዎች እና የራሳቸው አውራሽ የጋራ የውርስ ሀብት መሆኑን ጠቅሰው የአፈፃፀም አቤቱታው ውድቅ እንዲደረግ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ህግ ቁጥር 418 መሰረት አፈፃፀሙን በመቃወም ይቀርባሉ፡፡……….

ወ/ሮ ዱሬቲ ረያድ እና አቶ መሐመድ ቱኬ የሰ/መ/ቁ፡-206988

ወ/ሮ ዱሬቲ ረያድ እና አቶ መሐመድ ቱኬ የሰ/መ/ቁ፡-206988

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 335988 መጋቢት 6ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችሎት ጉዳዩን በየደረጃው የተመረመሩት የክልሉ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔና ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈፀመበትም ሲል የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብሎ እንዲታረምላቸው አመልካች በመጠየቃቸው ነው፡፡ በምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጀመረው የአፈፃፀም ክርክር የአሁን አመልካች የወ/ሮ ትግስት ግርማ ወራሾች ሞግዚት ሆነው የአፈፃፀም ክርክር ጣልቃ ገብ፣ የአሁን ተጠሪ የፍርድ ባለመብት፣ አቶ ሪያድ መሐመድ (የአመልካች አባት) የፍርድ ባለዕዳ፣ ሀዋስ ሀጅ ሁሴን(የአቶ ሪያድ መሀመድ ባለቤት) ደግሞ ሁለተኛ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

የፍርድ ባለመብት የሆኑት ተጠሪ የፍርድ ባለዕዳው 1,785,000.00ብር እንዲከፍለው የተወሰነበትን ፍርድ ለማስፈፀም በሻሸመኔ ከተማ የሚገኙ ሁለት ቤቶች የፍርድ ባለዕዳው ንብረት ናቸው ተብለው ቤቶችን ለመሸጥ ጨረታ ሲወጣ ከእነዚህ ቤቶች መካከል በ350 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ቤት የሟች እናታቸው የወ/ሮ ትዕግስት ግርማ ድርሻ ያለበት እና የፍርድ ባለዕዳ የሆኑት አባታቸው ድርሻቸውን ለእነሱ ያስተላለፈላቸው መሆኑን በመዘርዘር ጨረታው እንዲሰረዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 418 መሰረት አመልካች መቃወሚያ አቅርበዋል፡፡ ሁለተኛ ጣልቃ ገብ ደግሞ በዚሁ ከተማ በ180 ካሬ ሜትር ላይ የተሰራው ቤት ለፍርድ ማስፈፀሚያነት እንዲውል ለመሸጥ ጨረታ መውጣቱን በመቃወም አቤቱታ አቅርበዋል፡፡……..

አቶ አብደላ ከሊል እና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁ፡209319

አቶ አብደላ ከሊል እና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁ፡209319

ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ የአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 56(1) እና አዋጅ ቁጥር 609/2001 አንቀፅ 2(10) ፤22(10) እና 50(ለ)(1) ን በመጥቀስ ባቀረበው ክስ ጥር 05 ቀን 2013 ዓም ከቀኑ 3፡00 በሰበታ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 08 ውስጥ በሚገኘው ለተጨማሪ እሴት ታክስ በተመሰገበው የህንፃ መሳሪያ መሸጫ ድርጅት ባለቤትና አስተናጋጅ ሆነው ሲሰሩ ብረት የሚታሰርበት ፒንሳ በብር 130.00 ለዐቃቤ ህግ ምስክሮች ሲሸጡ ወዲያውኑ ደረሰኝ ሊሰጡ ሲገባ ያለደረሰኝ ግብይት ፈፅመዋል በማለት ከሷል፡፡……….

ወ/ሮ ትዕግስት ታደሰ እና ፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሰመ/ቁ፡-210020

ወ/ሮ ትዕግስት ታደሰ እና ፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሰመ/ቁ፡-210020

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የከባድ አካል ጉዳት ማድረስ የወንጀል ክስን የሚመለከት ነው፡፡የሰበር አቤቱታ የቀረበው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአመልካች ላይ የሰጠው የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ጉዳዩን በይግባኝ በተመለከተው ፌ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት መፅናቱ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ስለሆነ ይህ ውሳኔ እንዲታረምልኝ በማለት አመልካች ስላመለከቱ ነው፡፡

ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ የወንጀል ህግ አንቀፅ 555(ለ) ን በመጥቀስ ባቀረበው ክስ በክሱ ላይ በተመለከተው ጊዜና ቦታ የግል ተበዳይ አስቴር ደገፉን በቦክስ ሰንዝራ ፊቷ ላይ በመምታት የላይኛው የፊት ለፊት በቀኝ በኩል ያለው አንድ ጥርስ እና የፊት ለፊት በግራ በኩል ያለው ጥርሶቿ በከፍተኛ ደረጃ እንዲነቃነቁ አድርጋለች በዚህም ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ፈፅማለች በማለት ከሷል፡፡………..

First125126127128130132133134Last