በደሴ ከተማ የሆጤ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እና የወ/ሮ ማሚቴ ሁሴን ወራሾች እነ አያል አብርሃ የሰ/መ/ቁ፡-204074

በደሴ ከተማ የሆጤ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እና የወ/ሮ ማሚቴ ሁሴን ወራሾች እነ አያል አብርሃ የሰ/መ/ቁ፡-204074

ክርክሩ የመንግስት የንግድ ቤትን የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ በተጀመረበት የደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ፣ አመልካች ተከሳሽ እንዲሁም 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ክርክሩ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡…………

ኦዲት ሰርቪስ ኮርፖሬሽን እና ፀጋ ረታ አስመጪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የሰ/መ/ቁ፡-197008

ኦዲት ሰርቪስ ኮርፖሬሽን እና ፀጋ ረታ አስመጪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የሰ/መ/ቁ፡-197008

ክርክሩ የሽያጭ ውልን መነሻ ያደረገ ሲሆን ጉዳዩ በተጀመረበት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካች የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ባቀረበው ክስ አመልካች የኮምፒዩተር እቃዎችን ለመግዛት ባወጣው ጨረታ ተጠሪ አሸንፎ እቃዎቹን አቅርቦ ክፍያ የተቀበለ ቢሆንም እቃዎቹን ከሰርቨሩ ጋር የሚያገናኙ ኬብሎችን ባለማቅረቡ ምክንያት እቃዎቹ የተፈለገውን አገልግሎት መስጠት አልቻሉም፡፡በመሆኑም ኬብሎቹን እንዲያቀርብ ወይም በወቅቱ የገበያ ዋጋ የእቃዎቹን ግምት ብር 182,900 ወጪና ኪሳራን ጨምሮ እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ተጠሪ የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች እቃዎቹ ጉድለት ያለባቸው መሆኑን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በ1 አመት ውስጥ ክስ ስላላቀረበ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል እንደሚከተለው ቀርቧል…………

ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር እና እነ አቶ ታምሩ ደብሩ ሰ/መ/ቁ፡-191430

ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር እና እነ አቶ ታምሩ ደብሩ ሰ/መ/ቁ፡-191430

ክርክሩ የአክሲዮን ድርሻ ትርፍ እንዲከፈል የቀረበ ክስን መሰረት ያደረገ ሲሆን ጉዳዩ በተጀመረበት የምእራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተጠሪ ከሳሽና 1ኛ የከሳሽ ተከሳሽ፣ አመልካች ተከሳሽና የተከሳሽ ከሳሽ እንዲሁም 2ኛ ተጠሪ 2ኛ የተከሳሽ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

1ኛ ተጠሪ ጥቅምት 23 ቀን 2009 ዓ.ም ፅፎ ባቀረበው ክስ በአመልካች ኩባንያ ውስጥ በልዩ ቁጥር 1457 የተመዘገበ የአክሲዮን ድርሻ ያለኝ ሲሆን በዓመቱ መጨረሻ ሒሳብ ተሰርቶ ሊከፈለኝ ሲገባ ከ2006 እስከ 2008 ያልተከፈለኝ የአክሲዮን ትርፍን ፍርድ ቤቱ ሂሳቡን በማስመርመር በግምት ብር 30,000 እንዲከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡…….   

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ-ክርስቲያን ኮሚሽን እና አቶ መስፍን አዱኛ የሰ/መ/ቁ. 211260

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ-ክርስቲያን ኮሚሽን እና አቶ መስፍን አዱኛ የሰ/መ/ቁ. 211260

ጉዳዩ የግል የስራ ቅጥር ዉልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በጀመረበት በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ በቀን 30/06/2013 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከጥር 23 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ በፕሮጀክት ኦፊሰርነት በወር ብር 10,095.00 እየተከፈለኝ ሳገለግል የቆየሁ ቢሆንም አመልካች ምንም አይነት ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠኝ፣ በማላውቀው እና በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም የስራ ውሌን ያቋረጠው በመሆኑ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ተብሎ ወደ ስራዬ እንድመለስ፤ ወደ ስራ የማልመለስ ከሆነ ደግሞ ያልተጠቀምኩበት የ58 ቀን የዓመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ፣ ካሳ፣ የሶስት ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ ክፍያ ለዘገየበት የሶስት ወር ደመወዝ ቅጣት እንዲከፍል እና የስራ ልምድ እንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቀዉን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ እንደሚከተለው ቀርቧል…………

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል ገቢዎች ቢሮ እና አቶ አዕምሮ ዘሪሁን የሰ/መ/ቁ.210727

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል ገቢዎች ቢሮ እና አቶ አዕምሮ ዘሪሁን የሰ/መ/ቁ.210727

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው ተጠሪ በባሕር ዳር ከተማ ገቢዎች መምሪያ የታክስ ኦዲትና የሕግ ማስከበር የሥራ ሂደት አስተባባሪነት ከነበሩበት ኃላፊነት ተነስተው ከደረጃ 9 ወደ ደረጀ 8 ዝቅ ብለው በሽያጭ መመዝገቢያ ኤክስፐርት ሆነው እንዲሰሩ በመመደባቸው ቅሬታ አቅርበው ተቀባይት በማጣቱ ለአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የአስተዳደር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ ጥፋት ሳይኖረብኝና የዲሲፕሊን ክስ ሳይቀርበብኝ ከሥራ መደቡ መነሳቴ ሆነ ከደረጃና ደመወዝ ዝቅ መደረጌ አግባብ አይደለም የሚል ሲሆን አመልካች ባቀረበው መልስ በደንብ ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 9(4) መሠረት ማንኛውም የሥራ ሂደት አስተባባሪ በአሳማኝ ምክንያት ከኃላፊነት ሲነሳ ከያዘው መደብ ዝቅ ብሎ እንደሚመደብ ስለሚገልጽ በዚህ አግባብ የተከናወነ ነው ብሏል፡፡…………

First131132133134136138139140Last