ፌደራል ስነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና ወ/ሮ ፍሬህይወት ተረፈ የሰ/መ/ቁ፡- 209987 ፌደራል ስነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና ወ/ሮ ፍሬህይወት ተረፈ የሰ/መ/ቁ፡- 209987 ጉዳዩ ተጠሪ በአመልካች ኮሚሽን አለአግባብ ከደረጃና ከደመወዝ ዝቅ ተደርጌያለሁ በማለት ለፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ መነሻ የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ተብሎ የቀረበዉን የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ ተጠሪ በአመልካች ላይ በአስተዳደር ፍርድ ቤት ዘንድ ባቀረቡት ይግባኝ ከንብረት አወጋገድ፣ከሂሳብ አዘጋግ፣ በኦዲት ግኝት ለይ የተሰጠዉን ምክረ ሀሳብ ተግባራዊ ከማድረግ እና ሥራዎቼን በወቅቱ ከመፈጸም አንጻር የፈጸምኩት ጥፋት ሳይኖር አለአግባብ ከነበርኩበት ሥራ መደብ አንድ ደረጃ ዝቅ አድርጎ መድቦኛል፡፡ በመሆኑም አመልካች የሰጠኝ የዲሲፕሊን ውሳኔ አግባብ አይደለም ተብሎ ወደ ቀድሞ የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ደረጃ -15 ስራ መደብ ላይ እንዲመልሰኝ እንዲሁም በእግድ ምክንያት ያልተከፈለኝን የሐምሌ እና የነሐሴ ወር 2012 ዓ/ም ደመወዝ ብር 20,300.00 አመልካች እንዲከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡………..
እነ አቶ ከበደ ደሴ እና ወ/ሮ እልፍነሽ አብደላ የሰ/መ/ቁ.209757 እነ አቶ ከበደ ደሴ እና ወ/ሮ እልፍነሽ አብደላ የሰ/መ/ቁ.209757 ጉዳዩ የሽያጭ ውል የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪዎች ከሳሽ በመሆን በአመልካቾች ላይ በሁለት የተለያዩ መዝገቦች ላይ ባቀረቡት ክስ አመልካቾች በደራጀማ ሆቴል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ውስጥ ስድስት አክሲዮኖችን ከአንድ ሱቅ ጋር እንሸጥላችኋለን በማለት በ2004 ዓ.ም በተደረገው ውል ለ1ኛ ተጠሪ በብር 450,000.00 እንዲሁም ለ2ኛ ተጠሪ በብር 480,000.00 የሸጡልን ቢሆንም ውሉ ከህግ ውጪ የተደረገ በመሆኑ አመልካቾች በሽያጭ ውሉ መሰረት የወሰዱት ገንዘብ እንዲመልሱልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡አመልካቾች በበኩላቸዉ ውሉ የተደረገው በቃል መሆኑንና አንደኛው ተዋዋይ በውሉ ጥቅም አለማግኘቱ የውል ማፍረሻ ምክንያት አይሆንም፣የተሸጠው በሱቅ የመጠቀም መብት እንጂ የሱቅ ባለሀብት እንዲሁም የአክሲዮን ድርሻ ላይ አይደለም፣ተጠሪዎች ሱቁን በመረከብ ሲጠቀሙበት ቆይቷል፤ይህም በሱቁ ላይ ጥቅም ሲያገኙ እንደነበር የሚያሳይ ነው፣ተጠሪዎች የከፈሉት ገንዘብ የሚመለስበት የህግ አግባብ የለም፣ማህበሩ የሚሰራበት ቤት ከቤቶች ኮርፖሬሽን በመከራየት ነዉ፤በመሆኑም ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ ውድቅ እንዲደረግ በማለት ተከራክረዋል፡፡………………..
እነ አቶ ዮሴፍ ኃይሌ እና ፎራንክ ቢዝነስ ግሩፕ አክሲዮን ማህበር የሰ/መ/ቁ. 209266 እነ አቶ ዮሴፍ ኃይሌ እና ፎራንክ ቢዝነስ ግሩፕ አክሲዮን ማህበር የሰ/መ/ቁ. 209266 ጉዳዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሳሽ፣ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካቾች በተጠሪ ላይ በቀን 22/10/2012 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ በተለያየ የቅጥር ዘመን በሽያጭ ባለሞያ የስራ መደብ ላይ ተቀጥረን ስንሰራ ብንቆይም ተጠሪ ከህግ ውጪ ከቀን 26/08/2012 ዓ.ም ጀምሮ አሰናብቶናል፡፡ ስለሆነም ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ተብሎ ተጠሪው ካሳ፣ የአገልግሎት፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ ቅጣት፣ ከግንቦት ወር ጀምሮ የኮሮና ወረርሺኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እስከሚበቃበት ጊዜ ድረስ ያለው የወር ደመወዛችን እና የዓመት እረፍት በገንዘብ ተቀይሮ እንዲከፈለን ይወሰንልን በማለት የጠየቁትን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡እንደሚከተልው ቀርቧል…………….
እነ አቶ ግርማ ገብራይ እና ወ/ሮ ወሰኔ ገብራይ የሰ/መ/ቁ፡-207081 እነ አቶ ግርማ ገብራይ እና ወ/ሮ ወሰኔ ገብራይ የሰ/መ/ቁ፡-207081 ጉዳዩ ከገጠር መሬት ጋር የተያያዘ የውርስ ክርክርን የሚመለከት ነዉ፡፡ አመልካቾች በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ወረዳ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ ተጠሪ የእናታችንን እና የአባታችንን የውርስ ይዞታ አዋሳኞቾቻቸዉ በክሱ ይዘት የተጠቀሱትን በአራት ቦታ የሚገኙ የእርሻ መሬቶችን እንዲሁም በሻሸመኔ ከተማ ዉስጥ በ2000 ካሬ ሜትር ላይ የሚገኝ አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰ መኖሪያ ቤት በጋራ እያስተዳደሩ ቆይተዉ ተጠሪ ድርሻችንን ሊያካፍሏቸዉ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ በመግለጽ ድርሻቸዉ አንዲያካፍሏቸዉ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስ አመልካቾች የዉርስ ሀብት ነዉ የሚሉት መሬቶች ከ1980 ዓ/ም ጀምሮ በግላቸዉ ይዘዉ የሚጠቀሙበት እንደሆነ መኖሪያ ቤቱንም በግላቸዉ የሰሩት እንደሆነ በመግለጽ ክሱ ዉድቅ እንዲደረግላቸዉ በመጠየቅ ተከራክረዋል፡፡እንዲሁም የዉርስ ንብረት በአመልካቾች እጅ እንደሚገኝ በመግለጽ አመልካቾች እንዲያካፍሏቸዉ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በማቅረብ ተከራክረዋል፡፡…….
ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ስራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እነ ገልገሎ ቀጀላ የሰ/መ/ቁ፡-206765 ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ስራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እነ ገልገሎ ቀጀላ የሰ/መ/ቁ፡-206765 ጉዳዩ የሰራተኛ ጥቅማ ጥቅም ክፍያ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪዎች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩበት ነዉ፡፡ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ አመልካች ከአዋሽ- ኮምቦልቻ- ሃራ ገበያ ድረስ በሚያከናውነው የባቡር መንገድ ስራ ጊራና ሳይት ላይ ተቀጥረን ሲንሰራ የቆየን ሲሆን ያልተከፈለን የትርፍ ሰዓት፣ የሳምንት እረፍት፣ የህዝብ በዓላት ቀን ክፍያ እና የአልጋ አበል እንዲከፈለን ይወሰንልን የሚል ሲሆን አመልካች በበኩሉ የክፍያ ጥያቄ በይርጋ ይታገዳል፣ተጠሪዎች እነዚህ ክፍያዎች የሚገባቸው መሆኑን በማስረጃ አላረጋገጡም፣ትርፍ ሰዓት ስራ እንዲሰሩ አሰሪው ግልፅ ትዕዛዝ አልሰጠም፣የትርፍ ሰዓት መስራታቸዉ አልተመዘገበም፣ 9ኛው ተጠሪ የድርጅቱ ሰራተኛ አይደለም፣ የአልጋ አበል ለመክፈል አመልካች የገባው የውል ግዴታ የለም፣ለመክፈል አይገደድም በማለት ክሱ ውድቅ እንዲደረግ መከራከሩን መዝገቡ ያሣያል እንደሚከተልው ቀርቧል…………….