ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማሕበር እና አቶ ነገራ ለታ የሰ/መ/ቁ፡-204021 ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማሕበር እና አቶ ነገራ ለታ የሰ/መ/ቁ፡-204021 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪዎች ከሳሾች ነበሩ፡፡ ተጠሪዎች የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ/ም ባቀረቡት የተሻሻለ ክስ ከአመልካች ጋር በጥበቃ ሥራ ውል በኮንትራት ጊዜያዊ ውል አድርገናል፤ እስከ ነሀሴ 25 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ ውላችን ተራዝሟል፡፡ የ15 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት የሥራ ቅጥር ውል ጊዜ ሳይጠናቀቅ ከሐምሌ 30 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ አላግባብ በሕገ-ወጥ መንገድ ከሥራ አሰናበቶናል የሚል ነው መልካም ንባብ…………………
እነ ወ/ሮ የብርጓል በላይነህ እና እነ ወ/ሮ እቴነሽ መብራት የሰ/መ/ቁ፡-203809 እነ ወ/ሮ የብርጓል በላይነህ እና እነ ወ/ሮ እቴነሽ መብራት የሰ/መ/ቁ፡-203809 ጉዳዩ የይግባኝ ማስፈቃጃ አቤቱታን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካቾች የአዊ ብሔረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 01-18421 ሕዳር 11 ቀን 2012 ዓ/ም በሠጠው ውሳኔ ይግባኙን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የ60 ቀናት ጊዜው ያለፈባቸው በመሆኑ ጥር 20 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ የይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታ በማቅረብ ጊዘው ያለፈው የኮሮና ወረሽኝ በሽታ በመኖሩ፣ በሚኖሩበት አካባቢ የጸጥታ ችግርና የትራንስፖርት ችግር ያጋጠማቸው መሆኑን በመጥቀስ ከአቅም በላይ የሆኑ ምክንያቶች መሆናቸውን በማንሳት ይግባኙን ማቅረብ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል፡፡…………..
የጉምሩክ ኮሚሽን ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት እና አቶ ኤልያስ ዩሱፍ የሰ/መ/ቁ፡-203260 የጉምሩክ ኮሚሽን ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት እና አቶ ኤልያስ ዩሱፍ የሰ/መ/ቁ፡-203260 ጉዳዩ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ያለፈበትን ይግባኝ ማቅረብ እንዲቻል ለማስፈቀድ የቀረበ ማመልከቻ ዉድቅ በማድረግ በተሰጠ ዉሳኔ ላይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ተብሎ የቀረበ አቤቱታ የሚመለከት ሲሆን እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡………………….
ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ እና ወ/ሮ ሰብለ ሙሉነህ ሰ/መ/ቁ፡-202872 ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ እና ወ/ሮ ሰብለ ሙሉነህ ሰ/መ/ቁ፡-202872 ጉዳዩ የስራ ዉል መቋረጥ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ፤ የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ከመዝገቡ እንደሚታየዉ የተጠሪ ክስ የሚለዉ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከፍተኛ የህዝብ አገልግሎት ሀላፊ ሆኜ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በወር ብር 15,304 እየተከፈለኝ እየሰራሁ እያለ በህገ ወጥ መንገድ በቀን 15/11/2011 ዓ.ም ከስራ ያሰናበተኝ ስለሆነ ወደ ስራዬን እንዲመልሰኝ ወይም በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት ክፍያዎች እንዲከፍለኝ በማለት ዳኝነት የጠየቀች ሲሆን አመልካች በበኩሉ ተጠሪ ደንበኞች ያላመጡትን ሂሳብ እንዳመጡ በማድረግ የሌላቸውን የሂሳብ ሚዛን ወይም ቀሪ ሂሳብ በመፃፍ የማይገባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ አድርጋለች፣እንዲሁም ይህንን የድርጅት ሰነድ አስመስላ በመስራት የወንጀል ድርጊት ፈጽማለች፣በአጠቃላይ ወደ ባንኩ የመጣ ገንዘብ እና ከባንኩ የወጣ ገንዘብ በሌለበት በአየር ላይ የገቢና የወጪ ገንዘብ እንዳላቸው በማስመሰል ጽፋላቸዋለች፡፡ስለዚህ ባንኩ ማግኘት ያለበት ጥቅም ለሶስተኛ ወገን ጥቅም እንዲውል አድርጋለች፣ይህ ደግሞ በአዋጅ ቁ/1156/2011 አንቀጽ 27/1/መ መሰረት ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል እንዲቋረጥ የሚያደርግ ጥፋት በመሆኑ ተጠሪ የተሰናበተችዉ በህጋዊ መንገድ በመሆኑ የካሳ፣የአገልግሎት፣የማስጠንቀቂያ እና ሌሎች ክፍያዎች አይከፈላትም፣ሌሎች በአንቀጽ 36 እና 38 የተጠየቀው ክፍያ ክሊራንስ ካጠናቀቀች በኋላ የሚከፈል ክፍያ ነው በማለት ተከራክረዋል፡፡…………………
አቶ ታደሰ ንጉሴ እና አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ሻሸመኔ ቅርንጫፍ የሠ/መ/ቁጥር 201974 አቶ ታደሰ ንጉሴ እና አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ሻሸመኔ ቅርንጫፍ የሠ/መ/ቁጥር 201974 ጉዳዩ የሥራ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን አመልካች በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ ከተጠሪ ጋር በ1989 ዓ/ም በፈፀሙት የስራ ውል በባላንስ ሠራተኛነት የስራ መደብ ላይ በወር 13,034.00 እየተከፈላቸዉ እንዲሰሩ ተቀጥረዉ ሲሰሩ መቆየታቸዉን፤ነገር ግን ያለምንም ምክንያት በቀን 07/09/2011ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ የትራንዛክሽን ሥራ በመስራት በማሳለፍ ብድር በመዝጋት ባንኩ ማግኘት ያለበትን በማሳጣት ጥፋት ፈጽመሀል በማለት ሥራዬ ትራንዛክሽን ማሳለፍ ባለመሆኑ የሰራሁት ጥፋት ሳይኖር ከሕግ-ዉጭ ከሥራ አሰናብቶኛል፡፡ስለሆነም ወደ ሥራ እንዲመልሰኝ እንዲወሰንልኝ፡፡ይህ የሚታለፍ ከሆነ የስንብት ክፍያ ብር 95,582.67 ፣የ15 ቀን ደመወዝ ብር 6,517.00 ፣ክፍያ ለዘገየበት የሶስት ወር ደመወዝ ብር 39,102.00 ፣ካሳ የ6 ወር ደመወዝ ብር 78,204.00፣የፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያ ብር 63,550.29፣ተጠሪ ባንክ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ከ20 ዓመት በላይ ላገለገለ ሰራተኛ 21 ካራት ወርቅ ስለሚሰጥ የዚህ ዋጋ የአንድ ካራት ዋጋ ብር 1,700.00 ብር 35,700.00፣የቦነስ ክፍያ የ2011 ዓ/ም ብር 39,102.00፣ከ2009-2011ዓ/ም ድረስ ያልተጠቀምኩበትን የሶስት ዓመት የአመት እረፍት ወደገንዘብ ቀይሮ እንዲከፍለኝ በአቃላይ ብር 370,991.29 (ሶስት መቶ ሰባ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አንድ ብር ከሃያ ዘጠኝ ሳንቲም) እንዲከፈላቸዉ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡…………….