ተድላ ክፍሌ ኦሻ እና ከኦሮሚያ ጠቅላይ ዐ/ሕግ ዳኘ አማረ የሰ/መ/ቁጥር 219862 ተድላ ክፍሌ ኦሻ እና ከኦሮሚያ ጠቅላይ ዐ/ሕግ ዳኘ አማረ የሰ/መ/ቁጥር 219862 ጉዳዩ በሰው አካል ላይ ከባድ ጉዳት ማድረስ ወንጀልን በሚመለከት የቀረበ ክርክር ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አርሲ ዞን የዲገሉና ጢጆ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡ የአሁን ተጠሪ ሐምሌ 6ቀን 2011ዓ/ም በተፃፈ ክሱ የአሁን አመልካችን አንደኛ ተከሣሽ በማድረግ እንዲሁም አቶ ደጀኔ ከበደን ሁለተኛ ተከሣሽ በማድረግ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና 555(ለ) የሚደነግገውን በመተላለፍ በጋራ ሆነው በሰው አካል ላይ ጉዳት ለማደረስ አስበው ሚያዚ 19ቀን 2013ዓ/ም ከምሽቱ 2፡00 አረቢ ቀበሌ ልዩ ቦታው ቱሉ ገሬ ከሚባለው ስፍራ የግል ተበዳይ ሐብታሙ ሙላቱን አመልካች በከዘራ የግራ ጭንቅላቱ ላይ መቶ በመፈንከት ጥድ ላይ ሲጥለው የቀኝ ዓይኑ አካባቢ አጥንት ወደ ውስጥ በመስበር ጉዳት መድረሱን ሁለተኛው ተከሣሽ በበኩሉ በወደቀበት በዱላ ቀኝ ትክሻውን በመምታት ከበድ የአካል ጉዳት መድረስ ወንጀል ፈጽሟል የሚል ክስ አቅርበዋል፡፡ መልካም ንባብ……….
ወ/ሮ ፅዱ ታዬ እና አቶ ፋሲል ስለሺ የሰ/መ/ቁጥር 219484 ወ/ሮ ፅዱ ታዬ እና አቶ ፋሲል ስለሺ የሰ/መ/ቁጥር 219484 የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ እንደተረዳነው ተጠሪ በአመልካች የጥብቅና አገልግሎት ክፍያ እንዲከፈላቸው ክስ አቅርበው አመልካች በሌሉበት ክርክሩ ቀጥሎ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ አመልካች እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡ ከውሳኔ በኋላ አመልካች በሌሉበት የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ የክርክሩ ተካፋይ ለመሆን አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የአመልካችን አቤቱታ መርምሮ አመልካች ቀርበው እንዲከራከሩ መጥሪያ እንዲደርሳቸው በጋዜጣ ጭምር ጥሪ ሲደረግ ነበር፡፡ አመልካች ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ ሆኖ እያለ ሰፊ ሽፋን ባለው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው አልሰማሁም ያሉ ቢሆንም እንዳይሰሙ ያደረጋቸውን ምክንያት ስላልገለጹ አቤቱታቸው ተቀባይነት የለውም በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ አመልካች በዚህ ትእዛዝ ላይ የይግባኝ ቅሬታ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡መልካም ንባብ…….
ኮማንደር ደጃሹ ደሳለኝ እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዓቃቤሕግ የሰ.መ.ቁ. 218348 ኮማንደር ደጃሹ ደሳለኝ እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዓቃቤሕግ የሰ.መ.ቁ. 218348 ጉዳዩ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች 14ኛ ተከሳሽ ሲሆን፤ የአሁን ተጠሪም በአመልካች እና ሌሎች ተከሳሾች ላይ ያቀረባቸው 7 ክሶች ሲሆኑ አመልካችን የሚመለከቱት ክሶች ሶስት ናቸው፡፡ መልካም ንባብ…….
አቶ ሰሎሞን ጥበቡ እና የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሰ/መ/ቁጥር 218343 አቶ ሰሎሞን ጥበቡ እና የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሰ/መ/ቁጥር 218343 የአሁን ተጠሪ በስር በባህርዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአመልካችና በስር 1ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ላይ ባቀረበው ክስ 1ኛ አኳኬም የውሀ ማከሚያ ኬሚካል እና ማጣሪያ ኃ/የተ/የግል ማሀበር በውሃ ማከሚያ ኬሚካልና በውሃ ማጣሪያ ሽያጭ ንግድ ላይ ተሰማርቶ ሲሰራ አመልካች የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ፤የስር 3ኛ ተከሳሽ ደግሞ መስራች አባል ሆነው ባሉበት ጊዜ ከግንቦት 2004 እስከ ሰኔ 2008 ባለው የግብር ዘመን ውስጥ የተርን አቨር ታክስ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኞች አራት ጥራዝ ያለ ግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ፈቃድ በድጋሚ አሳትመው ከቁጥር 0050-0110 እና ከቁጥር 0151-0200 ያሉትን በመጠቀም የግብርና ታክስ ሰብሳቢውን መስሪያ ቤት ስራ የማሰናከል ወንጀል ፈፅመዋል በማለት የወ/ህ/አ.32(1)(ሀ)፤34(1)፤የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀፅ 98(1)(ለ)፤102(1) የደረሰኝ አጠቃቀም እና አያያዝ መመሪያ ቁጥር 28(1) እና 6(3) ን በመጥቀስ የመጀመሪያ ክሱን በሶስቱም ተከሳሾች ላይ ያቀረበ ሲሆን በ1ኛ ተከሳሽና በአመልካች ላይ ባቀረበው ሁለተኛ ክሱም የወ/ህ/አ.32(1)(ሀ)፤34(1)፤የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀፅ 96 እና 102(1) ን በመተላለፍ ከግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ፈቃድ ውጪ በታተመው ደረሰኝ ከፈፀሙት ሽያጭ የተሰበሰበውን ብር 948,448.00 ገቢ ባለማሳወቅ ብር 284,534.40 የንግድ ትርፍ ግብርና እና ሽያጭ ባለማሳወቅ ብር 3,396.34 በድምሩ 287,937.74 የንግድ ትርፍ ግብር አሳጥተዋል በዚህም ህግን በመጣስ ገቢን አለማሳወቅ ወንጀል ፈፅመዋል በማለት የከሰሰ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ በአመልካችና የስር 1ኛ ተከሳሽ ላይ ባቀረበው 3ኛ ክስም የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያው አገልግሎት ላይ በነበረበት ወቅት በህገ ወጥ መንገድ ባሳተማቸው የእጅ በእጅ ሽጭ ደረሰኞች በመጠቀም የወ/ህ/አ.32(1)(ሀ)፤34(1)፤የገቢ ግብር መሻሻያ አዋጅ ቁጥር 608/2001 አንቀፅ 97(ሀ)(2) እና የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀፅ 102(1) ተላልፈው የወንጀል ድርጊት ፈፅማዋል በማለት ከሷል፡፡መልካም ንባብ….
እነ አቶ ሥልጣን ወ/ሚካኤል እና እነ አቶ ኦሜጋ ተረዳ የሰ.መ.ቁ. 217855 እነ አቶ ሥልጣን ወ/ሚካኤል እና እነ አቶ ኦሜጋ ተረዳ የሰ.መ.ቁ. 217855 ጉዳዩ ይዞታ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካቾች ከሳሾች፤ የአሁን ተጠሪዎች በቅደም ተከተል 1ኛ ፣2ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች፤ በዚህ የሰበር ክርክር የሌሉት ወ/ሪት ሙሉ ወርቅ ኦሜጋ እና ወ/ሮ ሸዋዬ ሰይድ በቅደም ተከተል ደግሞ 3ኛ እና 5ኛ ተከሻሶች በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ስሙ አስኮ ተብሎ ለሚጠራው ሰፈር የተጠሪዎች እና የስር ተከሳሾች ይዞታ የሚያሳየው 275 ካ.ሜ ሲሆን የአመልካቾች ደግሞ 152 ካ.ሜ የሆነ ይዞታ ነው፤ ተጠሪዎች እና የስር ተከሳሾች በቤት ቁጥር 378 ካርታ ላይ ካለው 275 ካ.ሜ ይዞታ ተጨማሪ ከአመልካቾች ይዞታ ስር የሚገኝ 35 ካ.ሜ አላግባብ የያዙ መሆኑን በመግለጽ ተጠሪዎች እና የስር ተከሳሾች ከካርታቸው ውጪ የያዙትን ቦታ በመሃንዲስ ተለክቶ አለግባብ የወሰዱት ተረጋግግጦ እንዲለቁ ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡መልከም ንባብ…….