ወ/ሮ መሠረት ኃይሉ እና ወ/ሮ ቢቂልቱ በየነ የሰ/መ/ቁ. 201128 ወ/ሮ መሠረት ኃይሉ እና ወ/ሮ ቢቂልቱ በየነ የሰ/መ/ቁ. 201128 ጉዳዩ የፍርድ አፈፃፀምን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በቡራዩ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ተጠሪ የፍርድ ባለመብት በመሆን የፍርድ ባለዕዳ በሆኑት በአመልካች እና ሌሎች ሁለት ግለሰቦች ላይ ባቀረቡት አቤቱታ የቡራዩ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 64593 ላይ በቀን 10/08/2009 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በሰጠዉ ውሳኔ መሠረት እንዲፈፀምላቸው የጠየቁትን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡………………
አቶ ሙሉጌታ ኃ/ማርያም እና አቶ ነጋሽ ያደቴ አባይነህ ነጋሽ ሰ.መ.ቁ.200968 አቶ ሙሉጌታ ኃ/ማርያም እና አቶ ነጋሽ ያደቴ አባይነህ ነጋሽ ሰ.መ.ቁ.200968 ይህ የእርሻ መሬት የተጀመረዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.251106 ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ በሥር ፍ/ቤት ባቀረበዉ ክስ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ክልል ዉስጥ ግብር እየገበርኩበት ያለዉን ሁለት ቀርጥ (አዋሳኝ በመጥቀስ) የእርሻ መሬት ይዞታዬን የካቲት ወር 1989 ዓ.ም ባደረግነዉ ዉል ለጊዜያዊ ችግሬ መዋያ ብር 7000 (ሰባት ሺህ) ከተከሳሽ ተቀብዬ መሬቱን ለተከሳሽ የሰጠሁ፣ ገንዘቡን ስመልስለት ደግሞ መሬቱን ሊመልስልኝ የተስማመን ሲሆን፣ ተከሳሽ ገንዘቡን ተቀብሎኝ መሬቱን እንዲያስረክበኝ ፈቃደኛ ስላልሆነ፣ ተከሳሽ ገንዘቡን ተቀብሎኝ የእርሻ መሬቱን እንዲያስረክበኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡……………..
አቶ አክሉሉ ካሕሳይ እና አኪር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር የሰ/መ/ቁ፡-198891 አቶ አክሉሉ ካሕሳይ እና አኪር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር የሰ/መ/ቁ፡-198891 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ተከሳሽ ነበር፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ ከተጠሪ ጋር ጥር 25 ቀን 2005 ዓ/ም በተደረገ የመኪና ኪራይ ውል ስምምነት መሠረት የሠሌዳ ቁጥር 3-83597 አ.አ. የሆነ ተሽከርካሪ ለ10 ወራት ከ15 ቀናት ለሰራው ብር 346,500.00 ተጠሪ መክፈል ሲገባው ብር 100,000.00 ብቻ ከፍሎ ቀሪ ገንዘብ ስላልከፈለ ብር 246,500.00 ከሕጋዊ ወለድ ጋር እንዲከፈላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡……………..
አቶ ወርቁ ኃይለመስቀል እና አቶ ከበደ ደስታየሰ/መ/ቁ፡-198805 አቶ ወርቁ ኃይለመስቀል እና አቶ ከበደ ደስታየሰ/መ/ቁ፡-198805 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ከሟች አባታቸው አቶ ደስታ አድማሱ በውርስ የሚተላለፍ የሚንቀሳቀስ እና በዚህ ችሎት ደረጃ አከራከሪ ሆነ የቀረበውን የገጠር እርሻ መሬት አመልካች ለቀው እንዲያስረክቧቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ አመልካች ስለመሬቱ ያቀረቡት መልስ ይዞታው የሟች ደስታ አድማሱና የባለቤቱና የአመልካች አያት የሆኑት የወ/ሮ እህተጊዮርጊስ ኃይለጊዮርጊስ ሲሆን አያቴ ወራሽ ስለሆን የሟች ደስታ አድማሱን ድርሻ በኑዛዜና በሥጦታ አስተላፈውልኛል፡፡ በድጋሜ ከልጆቹ ጋር መሬቱን አውርሰውኛል፡፡ የሟች ደስታ ድርሻ ሊተላፍልህ አይችልም ቢባል እንኳን የአያቴ የቤተሰብ አባል ስለሆንኩ ግማሽ ድርሻውን ተጠሪ ሊጠይቁኝ አይገባም ብለዋል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የወረዳ ፍርድ ቤት ጉዳዩን መርምሮ…………….
እነ አቶ መርጋ ከበደ፣ አቶ አበራ ከበደ እና ጠ/ዮሴፍ አመንቴ የሰ-መ-ቁ-189155 እነ አቶ መርጋ ከበደ፣ አቶ አበራ ከበደ እና ጠ/ዮሴፍ አመንቴ የሰ-መ-ቁ-189155 የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካቾች የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 48351 በቀን 01/09/2011 ዓ.ም የዳዎ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ 30573 በቀን 06/07/2011 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የሰጠውን ውሳኔ፤ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ 313390 በቀን 29/01/2012 ዓ.ም እንዲሁም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 319820 በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በመሻራቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ የተጀመረው በስር የዳዎ ወረዳ ፍ/ቤት የአሁን አመልካቾች ባቀረቡት ክስ ሲሆን ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡……..