እነ ወ-ሮ ጀማነሽ ቀነኒ፣አቶ አሰፋ ሸቡ እና ወ-ሮ ብርቱካን ሸቡ የሰ-መ-ቁጥር 177205 እነ ወ-ሮ ጀማነሽ ቀነኒ፣አቶ አሰፋ ሸቡ እና ወ-ሮ ብርቱካን ሸቡ የሰ-መ-ቁጥር 177205 ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች ግንቦት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የደቡብ ብ/ብ/ህ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 11920 የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ እና የደቡብ ብ/ብ/ህ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 12667 ግንቦት 5 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልን በማለት ቅሬታቸውን በማቅረባቸው ነው፡፡ ቅሬታቸውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካቾች የሚቃወሙባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልን ይገባል የሚሉትን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የስር ፍ/ቤት የከተማ ማዘጋጃ ቤቱ አጣርቶ ገልጾ እያለ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ከቀበሌ ጠይቆ በዚሁ ተመስርቶ የሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም፡፡ የውርስ አጣሪው ከሳሽ 12,000 ብር የተቀበለች መሆኑን ጭምር ከሪፖርቱ ጋር ሰነዱን አቅርቦ እያለ እና ድርሻዋን መውሰዷ ተረጋግጦ እያለ በድካሚ ትካፈል ተብሎ መወሰኑ ተገቢ ባለመሆኑና የተጠሪ ክስም በይርጋ ውድቅ መሆን ስገባ መታለፉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚልነው፡፡..........
አቶ ረዲ አህመድ እና ወ-ሮ መኪያ ሀሰን የሰ-መ-ቁ 175719 አቶ ረዲ አህመድ እና ወ-ሮ መኪያ ሀሰን የሰ-መ-ቁ 175719 ይህ የባልና ሚስት የንብረት ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.223910 በ10/8/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ። የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረዉ ጋብቻ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍ/ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ ጋብቻችን በፍቺ እንዲፈርስ ወስኗል። ስለሆነም አመልካች እና ተጠሪ በጋራ የፈራነዉ በሱሉልታ ከተማ ልዩ ስሙ ድሬ ጀርባ የሚገኘዉ የቤት ቁጥር 632 SUL 2.1 የሆነዉ በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት እንዲንካፈል እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል። የአሁን ተጠሪ በዚህ ክስ ላይ ባቀረቡት መልስ ይህን ቤት ተጠሪ ከአመልካች ጋር የነበረን ጋብቻ ከተቋረጠ በኋላ ተጠሪ ከግለሰብ ገንዘብ ተበድሬ የተሰራ ስለሆነ የጋራ ንብረት ሳይሆን የግል ንብረቴ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል።………
እነ ወ/ሮ አያልነሽ ፈንቴ እና ወ/ሮ ብርሃኔ ተካ የሰ-መ-ቁ182110 እነ ወ/ሮ አያልነሽ ፈንቴ እና ወ/ሮ ብርሃኔ ተካ የሰ-መ-ቁ182110 አመልካች ለዚህ ችሎት ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ/ም ባቀረቡት አቤቱታ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 62378 መጋቢት 11 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችሎት ማስረጃ ሳይሰማ አመልካች የሟች ሚስት አይደሉም በማለት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍርድ ቤቱም በመዝገብ ቁጥር 194677 መጋቢት 11 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችሎት ያቀረቡትን አቤቱታ በመሰረዙ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅሬታ አቅርበው ችሎቱም በመዝገብ ቁጥር 148513 የሰበር አቤቱታቸውን የሰረዘው ሆኖ እያለ እና የአሁን ተጠሪ በሰበር መዝገብ ቁጥር 152523 ባቀረቡት ቅሬታ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በፊት የተሰጠን ውሳኔን ጠቅሶ ግራ ቀኙ የሟች ሚስቶች አይደሉም በማለት የሰጠውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ በመሻር በማስረጃ ተጣሪቶ እንዲወሰን ወደ ሥር ፍርድ ቤት መልሶት እያለ ፤ ይህ ውሳኔ ለአመልካችም ተፈፃሚነት ሊኖረው ሲገባ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ስላላቀረብሽ ውሳኔውን እንደተቀበልሽ ይቆጠራል በማለት ከክርክሩ እንዲወጡ በማድረግ ተጠሪ ብቻ ሚስትነታቸውን እንዲያረጋግጡ መደረጉ የእኩልነት መርህን የሚጥስ ነው በማለት ብይኑ ተሽሮ ሚስት መሆናቸውን በማስረጃ ማረጋገጥ እንዲችሉ እንዲወሰንላቸው ጠይቋል።………….
አቶ ደጋረገ ሙሉ እና ወ-ሮ ውብናት ላቀ የሰ-መ-ቁ 181649 አቶ ደጋረገ ሙሉ እና ወ-ሮ ውብናት ላቀ የሰ-መ-ቁ 181649 ይህ የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክር የተጀመረዉ በአማራ ክልል በሜጫ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ተጠሪ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር አመልካች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.74190 ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ። የአሁን ተጠሪ በሥር በወረዳዉ ፍ/ቤት ባቀረበችዉ ክስ ከአሁን አመልካች ጋር ያለን ጋብቻ እንዲፈርስ፣ በጋራ የፈረናቸዉ ንብረቶች እንዲንካፈል በማለት ዘርዝራ በማቅረብ እንዲወሰንላት ዳኝነት ጠይቃለች።የአሁን አመልካች በዚህ ክስ ባቀረቡት መልስ ተጠሪዋ ባቀረበችዉ የንብረት ጥያቄ ላይ ተገቢ ነዉ ያለዉን ክርክር ያቀረበ ሲሆን፤ በራሱ በኩል ባቀረበዉ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ከተጠሪ ጋር ሊንካፈል ይገባል የሚላቸዉን ንብረቶች በመዘርዘር በመጠየቅ፤ የሰራተኛ እዳ አራት ኩንታል በቆሎ አንድ ኩንታል ዳጉሳ፣ አንድ ኩንታል ጓያ አለብን ልንከፍል ይገባል በማለት ጠይቋል። የአሁን ተጠሪ በዚህ በተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ላይ መልስ ያቀረበች ሲሆን፣ የሰራተኛ የጋራ እዳ አለብን በማለት የቀረበዉም ሐሰት ነዉ፣ ይህ ተቀጠረ የተባለዉ ልጅ የአሁን አመልካች የግል ልጅ ነዉ የእኔም ሶስት ልጆች የግል ነበረኝ የግል ከብቶች ነበራቸዉ እነዚህ ልጆች አብራዉ ከእኛ ጋር ያደጉ ሲሆን ለሰሩበት ልንከፍላቸዉ አልተስማማንም አልቀጠርናቸዉም፣የአሁን አመልካች ልጅ እንደልጅ ከቤት ነበረ እንጂ የተቀጠረ አይደለም።ከዚህ በኋላ የወረዳዉ ፍ/ቤት የሰዉ ምስክሮች በመስማት በሰጠዉ ዉሳኔ የአሁን አመልካች በተከሳሽ ከሳሽነት የጋራ ዕዳ በማለት ያቀረበዉ የሰራተኛ እዳ 6 [ስድስት] ማዳበሪያ እህል በጋራ ሊከፍሉ ይገባል፤ የባልና ሚስት ንብረቶች ላይ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ ሰጥቷል። የአሁን ተጠሪ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለባህር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበችዉ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ የባልና ሚሰት ንብረት በተመለከተ በተወሰኑ ንብረቶች ላይ የሥር ፍ/ቤት ጉዳዩን ድጋሚ አጣርቶ እንዲወስን የመለሰ ሲሆን፣ የሰራተኛ ዕዳ የተባለዉን የሥር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።.........
አቶ ቀኖ ኩታሳ እና ወ-ሮ መሳይ ገመቹ የሰ-መ-ቁ 180936 አቶ ቀኖ ኩታሳ እና ወ-ሮ መሳይ ገመቹ የሰ-መ-ቁ 180936 ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 303340 በ11/10/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት በ11/11/11ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡ የጉዳዩ አመጣጥ የአሁን ተጠሪ በስር በጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የኖኖ ቤንጃ ወረዳ ፍ/ቤት በአሁን አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በክሱ 1ኛ እና 2ኛ ተራ ቁጥር ላይ የተጠቀሰው ስፋቱ እና አዋሳኙ የተጠቀሰው አንድ ባር ሳር ቤት ግምቱ ብር 4000(አራት ሺህ ብር) የሚያወጣ አለን፤ በክሱ ከተራ ቁጥር 3 እስከ 47 የተጠቀሱትን ንብረቶች አመልካች ድርሻዬን እንዲያካፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው አመልካች ባቀረቡት መልስ ከተጠሪ ጋር የኖርነው አስር ወር ብቻ ነው፤ ክስ የቀረበባቸውን ንብረቶች ከቀድሞ ሚስቴ ወ/ሮ ያደሺ ያንካ ጋር ከ1990ዓ.ም ጀምረን ያፈራናቸው ንብረቶች ተጠሪን አይመለከትም፤ ተጠሪ ያላት ንብረት የቤት ውስጥ እቃ ብቻ ሲሆን እነሱም በተራ ቁጥር 12፤13፤14፤15፤19፤20፤23፤24፤26፤27 ሲሆኑ ያልተመዘገቡ ንብረቶች ደግሞ በተራ ቁጥር 3፤4፤5፤6፤16፤18፤21፤22፤25፤28፤29፤30፤31፤35፤36፤46 ሲሆኑ በተራ ቁጥር 46 ላይ የተጠቀሰው ኑግ የለም፤ በተራ ቁጥር 6 ላይ የተጠቀሰው በሬ የቀድሞ ሚስቴ ንብረት ነው፤ በተራ ቁጥር 45 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ተጠሪን ሳላገባት በፊት በ2007ዓ.ም ውስጥ ከቀድሞ ሚስቴ ጋር የገዛነው ነው፤ በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሰውን ንብረት አመልካችን ሳላገባት በፊት በ2007ዓ.ም ከቀድሞ ሚስቴ ጋር አፍርተን የባለቤትነት ማስረጃ ስላለን ተጠሪን አይመለከትም፤ በተራ ቁጥር 47 ላይ ተጠሪ የገለጸችውን ቤት በ2007ዓ.ም ከቀድሞ ሚስቴ ጋር ያፈራነው ስለሆነ ተጠሪን አይመለከትም፤ በ27/1/10ዓ.ም የተፈጸመው ውል ደግሞ ተጠሪ የገጠሩ ኑሮ አቅቶኛል ወደ ከተማ አስገባኝ ብላ በሽማግሌ ስለጠየቀችኝ ያደረኩት ውል እንጂ የሰጠኋት ስጦታ የለም፤ ስጦታ አልተሰጠም እንጂ ተሰጥቷል ቢባል እንኳን በመካከላችን የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት የተፈጸመ ውል ስለሆነ ውሉ እንዲፈርስልኝ ፤ በ29/8/09ዓ.ም የተፈጸመውን ውል ደግሞ የቀድሞ ሚስቴን ሳላማክራት የፈጸምኩት ውል ስለሆነ ከቤተሰብ ህጉ የሚቃረን ውል ስለሆነ ውድቅ እንዲደረግልኝ በማለት የተከራከሩ ሲሆን፤ በስር ጣልቃ ገብ የሆኑት ወ/ሮ ያደሺ አንካ (አሁን በሰበር አቤቱታው ላይ የሌሉ) በጣልቃገብነት ገብተው እንዲከራከሩ ተፈቅዶላቸው ባቀረቡት አቤቱታ ከአመልካች ጋር በ1990ዓ.ም ጋብቻ መስርተን አንድ ልጅ እና ንብረት አፍርተን እያለ አመልካች እና ተጠሪ ጋብቻ ፈጽመው ጋብቻቸውን አፍርሰው ወደ ንብረት ክርክር ሲሸጋገሩ ተጠሪ ከአመልካች ጋር ለአስር ወራት ብቻ የኖረች ሲሆን በተራ ቁጥር 1፤2፤6፤7፤8፤9፤10፤11፤31፤32፤33፤34፤37፤38፤39፤40፤41፤42፤43፤44፤45፤47 ላይ ተጠሪ የጠቀሰችው ንብረት እኔ ያፈራሁት ንብረት ስለሆነ ከክርክሩ ይውጣልኝ፤ በ29/8/10ዓ.ም የተደረገውን የስጦታ ውል በተመለከተ አመልካች ከጣልቃገብ ፍላጎት ውጪ የጋራ ንብረታችን የሆነውን ለ3ኛ ወገን ለማስተላለፍ መብት የሌለው በመሆኑ ውሉ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡.............