እነ አቶ ጁሀር ያህያ እና ወ/ሮ መሬም አህመድ የሰ.መ.ቁ 179607 እነ አቶ ጁሀር ያህያ እና ወ/ሮ መሬም አህመድ የሰ.መ.ቁ 179607 ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካቾች የአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 03-76478 በ15/8/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት በ16/12/11ዓ.ም በተጻፈ የተሻሻለ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ የአሁን 1ኛ ተጠሪ በስር የአብክመ ጎንደር ዞን አስተዳደር የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በአሁን 2ኛ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በ1960ዓ.ም ተጋብተን 4 ልጆች ወልደን ንብረት አፍርተን ስንኖር ባለመግባባታችን ጋብቻው ሳይፈርስ ተለያይተን ኖረናል፡፡ ስለሆነም አሁን ጋብቻው ፈርሶ 2ኛ ተጠሪ ሌላም ሚስት ስላለው የዘረዘርኩትን ንብረት ለሶስት እንድንካፈል በማለት ዳኝነት ጠይቀው 2ኛ ተጠሪም ባቀረቡት መልስ 1ኛ ተጠሪ ልጅ ወልዳልኛለች እንጂ ጋብቻ የለንም በማለት ተከራክረው ፍ/ቤቱም ጋብቻ አለ የለም? የሚለውን በምስክር እና በሰነድ በማረጋገጥ ጋብቻ እንዳለ በማረጋገጥ ብይን ሰጥቶ 1ኛ ተጠሪ የዘረዘሩትን ንብረቶች ባልና ሚስት የሆኑት 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች እንዲሁም በስር 1ኛ ጣልቃገቦች የነበሩት የአሁን አመልካቾች እንዲካፈሉ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ጉዳዩ በይግባኝ ወደ ክልሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሄዶ ፍ/ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪ መካከል ጋብቻ ያለ መሆኑን አረጋግጦ የአሁን 3ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብተው ባለመከራከራቸው የተነሳ የስር የወረዳ ፍ/ቤቱን ውሳኔ በመሻር የአሁን 3ኛ ተጠሪ ጣልቃገብተው እንዲከራከሩ ውሳኔ በመስጠት ጉዳዩን ለስር የወረዳው ፍ/ቤት በመለሰው መሰረት 3ኛ ተጠሪ በስር የወረዳው ፍ/ቤት 2ኛ ጣልቃገብ ሆነው ባቀረቡት የጽሁፍ ክርክር የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበው በፍሬጉዳዩ ላይ ባቀረቡት መልስ 1ኛ ተጠሪ ዘርዝራ ያቀረበችው ንብረት እንዲፈራ ያደረገችው አስተዋጽኦ የለም፤ በ2ኛ ተጠሪ እና በ3ኛ ተጠሪ ጥረት የተፈሩ ንብረቶች ናቸው፤ በ1ኛ ተጠሪ ክስ በተራ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰው እና አሁን አመልካቾች በዚህ ፍ/ቤት ላቀረቡት የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው አከራካሪው በመሀል አራዳ የሚገኘው ባለሁለት ፎቅ ቤት ከአሁን አመልካቾች ልጆቻችን(በስር ከ1ኛ ጣልቃገቦች) ጋር በሽርክና ስራ ከመጀመራችን በፊት በንጉሱ ዘመን ከቀበሌ የተቀበልነው እኔ እና 2ኛ ተጠሪ ስንሆን እስከ 1983ዓ.ም በመኖሪያ ቤት የምንጠቀምበት 2ኛ ተጠሪ እና እኔ ባለቤቱ 3ኛ ተጠሪ ስንሆን 2ኛ ተጠሪ በእርጅና ምክንያት ስራ ሲያቆም ለገቢ ምንጭ እንዲሆነን ከጋራ ልጆቻችን ጋር የሽርክና ውል ወስደንበታል፡፡ ፎቁም የተሰራው በልጆቻችን ጥረት በመሆኑ የልጆቻችን የ60% ድርሻ መኖሩን ስለማውቅ በነሱ በኩል የቀረበውን የጣልቃገብነት አቤቱታ አልቃወምም፤ ነገር ግን ፍ/ቤቱ በ2ኛ ተጠሪ እና በአሁን አመልካቾች(በስር 1ኛ ጣልቃገቦች) መካከል የተደረገው የሽርክና ውል ፈራሽ ነው የሚልበት ምክንያት ካለው ክፍፍልን በተመለከተ የቤቱ እና ቦታው ግማሽ ሀብት የ3ኛ ተጠሪ በመሆኑ ግማሽ ባለሀብት ናት ይባልልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡
እነ ወ-ሮ የሺወርቅ ፈንታዉ እና ወ-ሮ ፀሀይነሽ ፈንታዉ የሠ-መ-ቁጥር 190450 እነ ወ-ሮ የሺወርቅ ፈንታዉ እና ወ-ሮ ፀሀይነሽ ፈንታዉ የሠ-መ-ቁጥር 190450 ጉዳዩ የፍርድ አፈጻጸምን የሚመለከት ሲሆን ከክርክሩ እንደተረዳነዉ ጉዳዩ የተጀመረዉ በአማራ ክልል ሀብሩ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን ፍርድ ቤቱ በመ/ቁጥር 0101191 ላይ በቀን 13/07/2011ዓ/ም በተሰጠ ዉሳኔ ላይ ክስ የቀረበበትን ቤትና ቦታ በአይነት እንዲካፈሉ ያልተጨረሰ ግንባታ ካለ ከተካፈሉ በኋላ የየድርሻቸዉን ግንባታ እንዲጨርሱና ቤት ያልተሰራበትን ትርፍ ቦታ ግራ ቀኝ እኩል እንዲካፈሉ በሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት እንዲፈጸምላቸዉ የአሁን ተጠሪ የፍርድ አፈጻጸም መዝገብ አስከፍተዉ ፍርድ ቤቱም በመ/ቁጥር 0101101 ላይ ግራ ቀኝ እኩል እንዲካፈሉ ዉሳኔ የተሰጠበት ቤትና ቦታ ለሁለት ተካፍሎ በየግላቸዉ ካርታና ፕላን ለማሰራት የሚቻል ከሆነ በየግላቸዉ ካርታና ፕላን እንዲሰራላቸዉ ይህ የማይቻል ከሆነም እነ በሚል ካርታና ፕላን ሰርቶላቸዉ ዉጤቱን እንዲያሳዉቅ በሚል በቀን 03/10/2011 ዓ/ም ቤቱ ለሚገኝበት ለዉርጌሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ትእዛዝ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡……..
እነ ወ-ሮ ሰሚራ ጀማል እና አቶ ናስር ሐጎስ የሠ-መ-ቁጥር 188406 እነ ወ-ሮ ሰሚራ ጀማል እና አቶ ናስር ሐጎስ የሠ-መ-ቁጥር 188406 ጉዳዩ ዳኝነት ሳይከፈል መዝገብ በነጻ ስለማስከፈት የሚመለከት ሆኖ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች አቤቱታዉን በማቅረብ የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረቡት አቤቱታ እየተከራከሩበት ካለው ንብረት ውጭ ሌላ እንደሌላቸውና በጋብቻ ወቅት የተፈራው ንብረትም በፍርድ ስለታገደ መጠቀም እንደማይችሉ በመግለፅ በተጠሪ ላይ ለሚመሰርቱት የ32‚750‚000.00 ብር ክስ ለዳኝኘት የሚከፍሉት ገንዘብ እንደሌላቸዉ በመግለጽ መዝገቡ በነጻ እንዲከፈትላቸው የጠየቁ ሲሆን ተጠሪ በሰጡት መልስ አመልካች በጋብቻ ላይ እያሉ የሰሩት በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቤት ቁጥር 297 የሆነ መኖሪያ ቤት ፣ በመቐለ ከተማ መኖሪያ ቤት እንዲሁም በፒስ ደልውን ቴክኖሎጂ ሲስተም ሶልሽን ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ውስጥ አክሲዮን ያላቸው ስለሆነ ድሃ ስላልሆኑ የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፍሉ መዝገብ ሊከፈትላቸዉ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡…….
እነ አቶ ኪሮስ መኮንን፣አቶ ዳዊት አማረ እና አቶ ኪሮስ ዳኘው የሰ-መ-ቁ- 188807 እነ አቶ ኪሮስ መኮንን፣አቶ ዳዊት አማረ እና አቶ ኪሮስ ዳኘው የሰ-መ-ቁ- 188807 ጉዳዩ የእግድ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሠሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የሥር ከሳሽ፣ 2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ ሲሆኑ 1ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ ነበሩ፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ 2ኛ ተጠሪ ቤት እንዲገዛልኝ ገንዘብ ልኬለት የንብረቱን ሥመ-ሀብት በስሙ ስላደረገ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥሩ TH-14-B-4 የሆነ ቤት ያስረክበኝ ወይም ግምቱን ይክፈለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው ከ2ኛ ተጠሪ ጋር እየተከራከሩ ባለበት ሁኔታ ክርክር ያስነሳው ንብረት ላይ ፍርድ ቤቱ እግድ ሠጠ፡፡ 1ኛ ተጠሪ ጣልቃ በመግባት ንብረቱን ከ2ኛ ተጠሪ በውል ስለገዛሁ ሊከራከሩበት አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ በክርክሩ መካከል አመልካችና 2ኛ ተጠሪ ሠኔ 29 ቀን 2009 ዓ/ም ባደረጉት የእርቅ ሥምምነት የገንዘብ ዕዳውን 2ኛ ተጠሪ ለአመልካች ሊከፍሉና ተከፍሎ እስከሚያልቅ ድረስ ንብረቱ ላይ የተሠጠው እግድ ሳይነሳ እንዲቆይ የተስማሙ ሲሆን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 190764 ጥቅምት 06 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የእርቅ ሥምምነቱን ተቀብሎ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 277 መሠረት አጽድቋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ በበኩላቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገብ ቁጥር 191057 ክርክር ያስነሳውን ንብረት 1ኛ ተጠሪ ስለገዙት 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ እንዲያስረክቡ ሕዳር 20 ቀን 2011 ዓ/ም የተሠጠውን ፍርድ በማያያዝ ንብረቱን በፍርድ ስላገኘሁት በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ ክርክር ምክንያት የተሠጠው እግድ እንዲነሳ በማለት አመልክተዋል፡፡ አመልካች ለእግድ ይነሳልኝ ማመልከቻው ያቀረቡት መልስ በእርቅ ስምምነቱ የተመለከተውን ገንዘብ 2ኛ ተጠሪ እስኪከፍሉ ድረስ እግዱ ጸንቶ እንዲቆይ ተስማምተን እርቁ በፍርድ ቤት የጸደቀና ይህንንም 1ኛ ተጠሪ እያወቁ ያልተቃወሙና በይግባኝ ያላስለወጡ በመሆኑ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡…………
አቶ ጉዕሽ ሃይሉ ደሞዝ እና ወ-ሮ ፅጌ ገ-ሂወት የሰ-መ-ቁ 180326 አቶ ጉዕሽ ሃይሉ ደሞዝ እና ወ-ሮ ፅጌ ገ-ሂወት የሰ-መ-ቁ 180326 ይህ የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክር የተጀመረዉ በመቐለ ከተማ በ02 ቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ተከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.115041 በ12/09/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።የአሁን ተጠሪ በቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤት ባቀረበችዉ ክስ ከአመልካች ጋር ያለን ጋብቻ እንዲፈርስ፣ ትዳር ሲንመሰርት በባንክ ወደ አመልካች የሂሳብ ቁጥር ገቢ ያደረኩኝ ገንዘብ እንዲከፍለኝ፣ ለጥሎሽ ከሚገዛ ወርቅ ቀንሶ የወሰደዉ ብር 8190 እንዲከፍለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቃለች፣ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ዘርዝራለች። የአሁን አመልካች በዚህ ክስ ላይ ባቀረበዉ መልስ ተጠሪ ይህን ገንዘብ ለመጠየቅ መብት የለትም፣ ትዳር ሲንፈጽም ባደረግነዉ ዉል እኔም ገንዘብ በመግጠም በመቐለ ከተማ 16 ቀበሌ ዉስጥ የአልኮል ማከፋፈያ ከፍተን ኪራይ ብር 6000 ስንከፍል ቆይተን ስምምነት ስናጣ አሁን ለዋርድያ ብር 500 እየከፈልን እየተጠበቀ ስለሆነ ለትዳር መግጠሚያ ያቀረበችዉን ገንዘብ መጠየቋ ተገቢ አይደለም፣ በትዳር ዉስጥ ትርፍም ኪሳራም የጋራ ነዉ፣ ይህ ንብረት ተቆጥሮ በገንዘብም ሆነ በዓይነት እንዲንካፈል በማለት ተከራክሯል፣ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ጠቅሷል።…………