አቶ ኢሳያስ አድማሱ አለማየሁ እና ወ-ሮ አልማዝ ተድላ ደስታ የ-ሰ-መ-ቁ 183547

አቶ ኢሳያስ አድማሱ አለማየሁ እና ወ-ሮ አልማዝ ተድላ ደስታ የ-ሰ-መ-ቁ 183547

ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መናገሻ ምድብ 2ኛ ፍ/ብሄር ችሎት በኮ.መ.ቁ 62214 በ13/3/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ፤ የፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ 230102 በ28/10/11ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት በ7/1/12ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ ሟች አባቴ አቶ አድማሱ አለማየሁ በ29/10/03ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ አመልካችን ከወራሽነት የነቀለ እና የወራሽነት ድርሻ የሌለኝ ያደረገ ስለሆነ ይህ ኑዛዜ ተሰርዞ በፍ/ብ/ህ/ቁ 842(1) መሰረት ከሌሎች ወራሾች እኩል ድርሻ ያለኝ መሆኑ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሟች ህጋዊ ሚስት ስሆን ወራሽ ባልሆን ከሚስት እና ከባለቤቴ ንብረት ድርሻ ግማሹ(50%) የኔ መሆኑ እስከታወቀ ከሌሎች ወራሾች ጋር መከሰስ የሌለብኝ በመሆኑ፤ አመልካችም ከ1ኛ ተጠሪ የሚፈልገው መብት እና ጥቅም ስለሌለ ክሱ በ1ኛ ተጠሪ ላይ መቅረቡ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 33 መሰረት ተቀባይነት የለውም የሚል ሲሆን፤ ተጠሪዎች በጋራ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሟች አቶ አድማሱ አለማየሁ ግንቦት 29 ቀን 2003ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ በአርባ ቀን መታሰቢያው የካቲት 5 ቀን 2009ዓ.ም ሲነበብ አመልካችም በአካል ተገኝቶ የሰማ በመሆኑ ይህን ደግሞ መቃወም የሚችለው በፍ/ብ/ህ/ቁ 973(2) በ15 ቀን ውስጥ ብቻ ሲሆን አመልካችም ለሽምግልና ዳኞች ይህን ያላደረገ በመሆኑ፤ በአንቀጽ 973(2)(3) መሰረትም እስከ 3 ወር ግዜ ውስጥ ያላቀረበ በመሆኑ ክሱ በፍ/ብ/ህጉ እና በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 244(2)(ለ) መሰረት በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የተከራከሩ ሲሆን፤ ፍ/ቤቱም በመቃወሚያዎቹ ላይ ክሱን ከሰማ እና የግራቀኙን ምስክሮች ቃል ከሰማ በኋላ አመልካች ኑዛዜው ሲነበብ ሰምተዋል ወይስ አልሰሙም? ያልሰሙ ከሆነ የአመልካች ክስ በይርጋ የሚታገድ ነው ወይስ አይደለም? የሚሉትን ጭብጦች በመያዝ ጉዳዩን መርምሮ የአመልካች ምስክሮች በሰጡት ቃል አመልካች ኑዛዜው ሲነበብ በቦታው እንዳልነበሩ እና በእለቱም አብረው መዋላቸውን ገልጸዋል ይሁን እንጂ የአመልካች እናት አመልካች የ40 ቀን መታሰቢያው ቦታ እንዲሄድ በምስክሮች በኩል ያደረጉ ቢሆንም አመልካች ግን ሳይሄድ እንደቀረ መስክረዋል፤ የተጠሪዎች ምስክሮች በበኩላቸው አመልካች የሟች አባቱ የ40 ቀን መታሰቢያ ቀን የካቲት 5 2009ዓ.ም እዛ እንደነበር ፤ የኑዛዜው ኮፒ ለአመልካች እንደተሰጠ እና ስሙም በሄኖክ አድማሱ በሚባል ተራ ቁጥር 13 ላይ የሰፈረ ነው፤ የአመልካች ስም በሄኖክ አድማሱ ስም እንደሚታወቅ ለዚህም ማሳያ የአመልካች እናት የአመልካች ስም ሄኖክ ነው ማለታቸውን 1ኛ ምስክር መስክረዋል፤ አመልካች ጠዋት 1 ሰአት ጀምሮ እዛ እንደነበር እና የኑዛዜው ድርሻ አንሶኛል ያለውም ከ1 ወር በኋላ ነው በማለት በመመስከራቸው ከግራቀኙ ምስክሮች ቃል አመልካች ኑዛዜው በሚነበብበት ወቅት ቦታው የነበረ መሆኑን የተጠሪዎች ምስክሮች ከአመልካች ምስክሮች በበለጠ እና በአሳማኝ መልኩ በመግለጻቸው የፍ/ብሄር ህግ አንቀጽ 973(2) (3) ከደነገገው አንጻር ኑዛዜው የተነበበው የካቲት 5 ቀን 2009ዓ.ም ሲሆን የአመልካች ክስ የቀረበው በ22/12/09ዓ.ም በመሆኑ ይህም ሲቆጠር ከ15(አስራ አምስት) ቀናት በኋላ ብሎም ከ3(ሶስት) ወር በኋላ በመሆኑ ፤ አመልካችም በኑዛዜው ላይ ስማቸው እስከሰፈረ ድረስ የፍ/ብ/ህ/ቁ 939 ከደነገገው እና የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 36604 እና 53223(ቅጽ 8 እና 12) ከሰጣቸው አስገዳጅ ውሳኔዎች አንጻር ከኑዛዜው ተነቅያለሁ የሚባልበት አግባብ የለም ስለሆነም ክሱ በፍ/ብ/ህ/ቁ 973(1) እና 244(2) (ረ) መሰረት በይርጋ ይታገዳል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፌ/ከ/ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም በሰጠው ትእዛዝ ይግባኙን ሰርዞታል፡፡……….

አቶ ወንድማገኝ መንግስቱ ማሞ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ-መ-ቁ 191629

አቶ ወንድማገኝ መንግስቱ ማሞ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ-መ-ቁ 191629

አቶ ወንድማገኝ መንግስቱ ማሞ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ-መ-ቁ 191629

ይህ የሰበር ጉዳይ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለው ተጠሪ በአመልካች ላይ 3 የወንጀል ህግ ድንጋጌዎችን በመጥቀስ ተደራራቢ  ወንጀል ፈፅሟል በማለት ያቀረበው ክስ በደቡብ ክልል ኮንታ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን መርምሮ በ 2 ድንጋጌ ጥፋተኛ በማድረግ በ 11 ዓመት ፅኑ እስራት እና በብር 5,000.00  እንዲቀጣ የሰጠው ውሣኔ በይግባኝ ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመቅረቡ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ቅጣቱን በማሻሻል በ 7 ዓመት ከ 8 ወር ፅኑ እስራት እና በብር 2,500.00  እንዲቀጣ ሲወሰን ለክልሉ ከ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ሁለቱን ድንጋጌ በመተው በወንጀል ህግ አንቀፅ 543/3 ስር ብቻ ጥፋተኛ በማድረግ 5 ዓመት ፅኑ እስራት እና በብር 1,000.00 የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የፈፀመ በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ ሲል አመልካች የሰበር አቤቱታ በማቅረቡ መነሻነት ነው፡፡የጉዳዩን አመጣጥ እንዲህ ነው፡፡…….

እነ አቶ አንበሳው አፈወርቅ እና አቶ አበበ ተገኝ የሠ-መ-ቁጥር 185708

እነ አቶ አንበሳው አፈወርቅ እና አቶ አበበ ተገኝ የሠ-መ-ቁጥር 185708

ጉዳዩ የቤት ሽያጭ ውል አፈጻጸምን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በመጀመሪያ በታየበት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካች በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የቤት ቁጥሩ አዲስ የሆነውን በ360 ካሬ ሜትር የሰፈረ ቤት በብር 650,000.00 ከተጠሪ ገዝቻለሁ፡፡ በውሉ ላይ ተጠሪ ቤቱን እንዳስረከቡ የተገለጸ ቢሆንም ቤቱን በምረከብበት ወቅት እናቴ ከዚህ አለም በሞት የተለየች በመሆኑ ችግር ስለገጠመኝ ሳልረከብ የቀረሁ ስለሆነ ሀዘኔን ጨርሼ ተጠሪ ቤቱን እንዲያስረክቡኝ ብጠይቅም ቤቱን ሊያስረክቡኝ ፈቃደኛ ስላልሆኑ ቤቱን እንዲያስረክቡኝ እና በዉሉ የተመለከተዉን መቀጫ ብር 100,000.00 እንዲከፍለኙ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ተጠሪ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም ፍሬ ነገሩን በተመለከተ በሰጡት መልስ አመልካች ከተጠሪ ጋር ፈጸምኩኝ ያሉትን ወል አልፈጸምኩም፡፡ምንም ገንዘብ አልተቀበልኩም፡፡አመልካች ፈጸምኩኝ ያሉት ዉል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 መሰረት ያልተፈጸመና ሕጋዊ መሰረት የሌለዉና በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1720/1 መሰረት ረቂቅ ነዉ፡፡ ከአመልካች ጋር ቤተሰባዊ ግንኙነት ስለነበረኝ ጉዳይ እንዲያስፈጽሙልኝ የዉክልና ሥልጣና በርካታ ሕጋዊ ሰነዶችን ሰጥቻቸዉ በእጃቸዉ የሚገኝ ቢሆንም አመልካች ዉል አለኝ የሚሉት ዉል ሳይኖርና የተቀበልኩት ገንዘብ ሳይኖር በሀሰት የቀረበ ስለሆነ ክሱ ዉድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል፡፡……..

ወ/ሮ ገነት ገሠሰ ቸኮል ፣ የአ/አ ከተማ የየካ ክ/ከተማ አስ/ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ሌሎች የሰ/መ/ቁ 180001

ወ/ሮ ገነት ገሠሰ ቸኮል ፣ የአ/አ ከተማ የየካ ክ/ከተማ አስ/ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ሌሎች የሰ/መ/ቁ 180001

ጉዳዩ ከሚመለከተው የመንግስት አካል የግንባታ ፈቃድ ተሰጥቶ ግንባታው ከተጀመረ በኋላ ፈቃዱ የተሰጠው በተጠቀሰው ትምህርት ቤት የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር በጥናት በተለዬ ይዞታ ላይ ነው በሚል የተሰጠውን የግንባታ ፈቃድ አግዶ የተጀመረው ግንባታ እንዲቆም መደረጉ የሁከት ተግባር ነው በሚል የቀረበውን ክስ የመረመረው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በአመልካች መብት ላይ የፈጠሩት ሁከት የለም ሲል በሰጠው ውሣኔና ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የአመልካችን ይግባኝ በመሰረዙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈፅመዋል ተብሎ እንዲታረም የቀረበን  ክርክር የሚመለከት ነው፡፡………….

ወ/ሮ ትዕግስት ዓለሙ ቢ/አ/ኤ/ካ ኃ/የተ/የግል ማሕበር የጉባ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት፣የጉባ ወረዳ አካባቢ ጥበቃ፣መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ. 161449

ወ/ሮ ትዕግስት ዓለሙ ቢ/አ/ኤ/ካ ኃ/የተ/የግል ማሕበር የጉባ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት፣የጉባ ወረዳ አካባቢ ጥበቃ፣መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ. 161449

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪዎች ተከሳሾች ነበሩ፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ በጉባ ወረዳ ማንኩሽ ቀበሌ 10 ሄክታር የእርሻ መሬት በ1987 ዓ/ም ተመርቼ በሕጋዊ መንገድ የያዝኩትን 1ኛ ተጠሪ ፈቃድ ሳያወጣ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ትክና ካሣ ሳይከፍሉኝ ያላግባብ የይዞታ መሬቴን ለ1ኛ ተጠሪ በ2008 ዓ/ም ስለሰጡብኝ የ2008/2009 ዓ/ም የምርት ዘመን ያጣሁት የሰሊጥ ምርት ብር 115,000.00፣ ማሳ ለማዘጋጀት ያወጣሁት ብር 40,000.00፣ የማፈናቀያ ካሣ ብር 115,000.00 እና 10 ሄክታር ትክ የእርሻ መሬት እንዲሰጡኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ ያቀረበው መልስ ካሣና ትክ አስተዳደሩ የሚሰጠው እንጂ 1ኛ ተጠሪን አይመለክትም፡፡ በኢንቨስትመንት በሕጋዊ ፈቃድ የተሰጠኝ ስለሆነ ልጠየቅ አይገባም ብሏል፡፡ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በበኩላቸው መሬቱን የሠጠው የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ እንጂ እኛ አይደለንም፡፡ ካሣው የተጋነነ ነው፡፡ ብር 40,000.00 መሬቱን ለማጽዳት ስለመውጣቱ ማስረጃ አልቀረበም፡፡ ለ21 ዓመት መሬቱ ስለታረሰ የሚጸዳ ነገር የለውም፡፡ መሬቱን የሠጠው ቢሮ በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር ይታዘዝልን ብለዋል፡፡ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ  በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር ታዞ ባለመቅረቡ ጉዳዩ በሌለበት ታይቷል፡፡..........

First139140141142144146147148Last