በአማጋ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጮራ የጋዝና ኬሚካል ውጤቶች ፋብሪካ፣ሂክማ የፈሳሽ ሳሙና ማምረቻ ኃ/የተ/የቡድን ኢንተርፐራይዝ እና ሌሎች የሰ-መ-ቁ 175155 በአማጋ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጮራ የጋዝና ኬሚካል ውጤቶች ፋብሪካ፣ሂክማ የፈሳሽ ሳሙና ማምረቻ ኃ/የተ/የቡድን ኢንተርፐራይዝ እና ሌሎች የሰ-መ-ቁ 175155 ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ139054 በ29/5/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ፤ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 172510 በ26/7/11ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት በ7/8/11ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረበ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የፌ/ከ/ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረበው የተሻሻለ ክስ ለከሳሽ በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/98 መሰረት ለሁለት አይነት የበረኪና ምርቶች ማለትም ለትልቁ ባለ 800 ሚሊ ሊትር SEDEX እንዲሁም ለትንሹ ባለ 300 ሚሊ ሊትር SEDEX በምዝገባ ቁ.LTM/0189/2005 እና LTOW 0186/2005 በቅደም ተከተል የተመዘገበ እና እስከ 28/10/12ዓ.ም ድረስ ጸንቶ የሚቆይ የንግድ ምልክት ምዝገባ ሰርተፍኬት ከኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት በ2005ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን የንግድ ምልክቶቹ የተመዘገቡት እና ፈቃድ የተሰጠው በቃል እና በስእል(በቅርጽ) (በምስል) ከመሆኑም ባሻገር የቀለም አይነቱ በአዋጁ አንቀጽ 5(2) መሰረት ጥቁር እና ነጭ ነው፡፡ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ አላማው የተለያዩ እቃዎችን በማምረትና በማከፋፈል ወይም አገልግሎት በመስጠት የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መልካም ስም እና ዝና ለመጠበቅ እንዲሁም በተመሳሳይ ስራዎች እና አገልግለቶች መካከል ማሳከርን ለማስወገድ እና አንድን ምርት/እቃ ወይም አገልግሎት በቀላሉ ለመለየትና የንግድ ምልክቱ በአገልግሎት ተጠቃሚው (ኮንሲዩመሩ) ላይ ግርታ እንዳይፈጥር ለማድረግ ነው፡፡…………
ሲስተር ኮከብ በቀለ ከ እነ ሰላም እስኮዳቮልፕ ሲስተር ኮከብ በቀለ ከ እነ ሰላም እስኮዳቮልፕ እግድ እና የመያዣ ወይም የቅድሚያ መብት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 173079 ከፍርድ በፊት የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ የሚሰጥ የእግድ ወይም ንብረት የማስከበር ትዕዛዝ የመያዣ መብትን የማያቋቁም በመሆኑ የቅድሚያ መብትን ሊፈጥር እንደማይችል አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ ይህ የህግ ትርጉም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር ሰሚ ችሎት ከዚህ በፊት በሰ/መ/ቁጥር 97206 እና በሰ/መ/ቁጥር 29269 በዚሁ ጉዳይ ላይ ሰጥቶት የነበረውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም አሻሽሏል ወይም ለውጧል፡፡
አቶ አህመድ አብዱራህማን ከ ኢልይስ ዲተርጀንት ኢንዱስትሪ ኩባንያ የሰ-መ-ቁ 193292 አቶ አህመድ አብዱራህማን ከ ኢልይስ ዲተርጀንት ኢንዱስትሪ ኩባንያ የሰ-መ-ቁ 193292 በዚህ መዝገብ የተያዘው ክርክር የውጪ ሀገር ሰው (ኩባንያ) በንግድ ምልክት ምዝገባ ላይ ያቀረበውን የተቃዉሞ አቤቱታ መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩም ጆብ (Job) እና ሂላክ (Hilaac) የተባሉ የሳሙና ንግድ ምልክቶችን ይመለከታል፡፡ የሰበር አቤቱታው በአመልካች የቀረበውም በንግድ ምልክት የተቃውሞ አቤቱታው ላይ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት በመ/ቁ 0036 በቀን 21/06/2011 ዓ.ም እንዲሁም ይግባኙ የቀረበለት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 235010 በቀን 27/06/2012 ዓ.ም ያሳለፉት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው። ..................
አቶ ቃሲም አብዶ እና ወ/ሮ ዙበይዳ ሳፊ የሰ/መ/ቁ 192830 አቶ ቃሲም አብዶ እና ወ/ሮ ዙበይዳ ሳፊ የሰ/መ/ቁ 192830 የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚው ችሎት በመዝገብ ቁጥር 320970 መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተጠሪ በግራቀኙ መካከል የነበረው ጋብቻ የባህል መሆኑን በወረዳ ፍርድ ቤት አረጋግጣ ካቀረበችው ክስ ውጭ እንዲሁም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምሥራቅ ምድብ ችሎት ተከራካሪዎቹ ጥር 23 ቀን 2007 ዓ/ም ባህላዊ ጋብቻ ፈፅመው ከዚያን ጊዜ አንስቶ አብረው የሚኖሩ መሆኑን በማስረጃ አረጋግጦ የሰጠውን ፍርድ ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ሳይኖረው በመሻር በግራቀኙ መካከል ሐይማኖታዊ ጋብቻ በ2003 ዓ/ም ተፈፅሟል በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ስህተቱ ታርሞ ፤ በአመልካች እና ተጠሪ መካከል የነበረው ባህላዊ ጋብቻ ጥር 23 ቀን 2007 ዓ/ም የተደረገ በመሆኑ ፣ ከዚያ በፊት የተፈራው በአዳማ ከተማ ጠደቻ አራራ ቀበሌ በ200 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያለፈው ቤት እና የሰሌዳ ቁጥሩ አ.አ 43134 የሆነው መኪና ከጋብቻ በፊት የተፈራ የአመልካች የግል ንብረት ነው ተብሎ እንዲወሰን አመልካች ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ/ም ያቀረቡት የሰበር ቅሬታ ያስቀርባል ተብሎ መዝገቡ ለችሎት ቀርቧል፡፡ ጉዳዩ የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍልን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ እንደሚከተለው ቀርቧል……………….
አቶ ደምሴ ኦዳ ከ አቶ አሰፋ ወርቁ አቶ ደምሴ ኦዳ ከ አቶ አሰፋ ወርቁ ከፍርድ ቤት ውጪ በአማራጭ የሙግት መፍቻ መንገዶች እልባት የተሰጠ አንድ የፍትሐብሔት ጉዳይ በፍርድ ቤት ቀርቦ በቀጥታ ለአፈጻጸም ሊቀርብ የሚችልበትን ሁኔታ በተመለከተ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 196228 ግንቦት 25 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ