እነ አቶ ሐይሌ ንማኒ፣አቶ ነስሩ አህመድ፣ጀማል ዋበላ እና ወ/ሪት ምንዳዬ ለገሰ የሰ-መ-ቁ-188293

እነ አቶ ሐይሌ ንማኒ፣አቶ ነስሩ አህመድ፣ጀማል ዋበላ እና ወ/ሪት ምንዳዬ ለገሰ የሰ-መ-ቁ-188293

ጉዳዩ የንግድ መደብር ሽያጭ ውልን መነሻ ያደረገ ክርክር የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ በተጀመረበት በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ አመልካች 2ኛ ተከሳሽ እና 2ኛ አመልካች ጣልቃ ገብ በመሆን እንዲሁም 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ 2ኛ ተጠሪ ደግሞ 1ኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ከክርክሩ እንደተረዳነዉ 1ኛ ተጠሪ በአሁን 1ኛ አመልካች እና በ2ኛ ተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር 222 የሆነ በንግድ ምዝገባ ቁጥር AA/AK/08/2/1/000075/2006 በቀን 20/08/2002 የተመዘገበ እና በቀን 11/07/2006 ዓ/ም በቁጥር 14/671/710375/2006 የንግድ ፍቃድ የወጣበት የትራንስፖርት ፣የመጋዘንና የኮሚኒኬሽን ስራዎች ንግድ የሚካሄድበት የንግድ መደብር 1ኛ ተጠሪ በቀን 13/07/2006 ዓ/ም በብር 400,000.00 ለመግዛት ተስማምተው ቅድመ ክፍያ ብር 50‚000.00 ለ2ኛ ተጠሪ ከፍለዉ ቀሪውን ክፍያ 2ኛ ተጠሪ የንግድ መደብሩን ከተለያዩ ግዴታዎች አፅድተው ከነሰነዱ ሲያስረክቡ ለመቀበል ተስማምተዋል፡፡ሆኖም 2ኛ ተጠሪ እንደ ውሉ ግዴታቸውን ያልተወጡ በመሆኑ የንግድ መደብሩ በአሁን 1ኛ አመልካች እጅ የሚገኝ በመሆኑ የንግድ መደብሩን ለአሁን 1ኛ ተጠሪ እንዲያስረክቡ እና የአሁን 2ኛ ተጠሪ እንደ ውሉ ባለመፈፀማቸው ብር 50‚000.00  እንዲከፍሉ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡………..

ወ-ሮ አበባዬ ጌቶ እና ወ-ሮ ወርቅዬ ጌቶ የሰ-መ-ቁ 187253

ወ-ሮ አበባዬ ጌቶ እና ወ-ሮ ወርቅዬ ጌቶ የሰ-መ-ቁ 187253

ጉዳዩ የገጠር መሬት ክርክር የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ክልል በሳይንት ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ ላይ ያቀረበችዉ ክስ የወላጅ እናቴ አበቡ ወርቁ ወራሽ መሆኔን በ14/09/2010 ዓ.ም አረጋግጫለሁ፡፡ስለዚህ ተጠሪ አራት ቦታ የሚገኝ የውርስ መሬት እንዲታካፍለኝ እንዲወሰንልኝ የሚል ሲሆን ተጠሪ በበኩሏ ያቀረበችዉ መልስ እናታችን እንደሞተች በ2004ዓ.ም በፍርድ ቤት ስናሳውጅ የአሁኗ አመልካች መሬት ስላላት መሬት አትወርስም ተብላ ተከልክላለች፣አዲሱ አዋጅ ስለሚፈቅድላት አሁን ሊትጠይቅ አይገባም፣በይዞታዉ ላይ የማረጋገጫ ደብተር አውጥቼበት የራሴ መሬት ነው በማለት ክሱ ተቀባይነት እንደሌለዉ  ተከራክራለች፡፡

ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክር እና የቀረበውን ማስረጃ መርምሮ እናታቸው ከሞተች ከኋላ እስከ 2009 ዓ.ም ተጠሪ እያረሰች ለሌሎች ወራሾች ስታካፍላቸው የኖረች እና በጽሁፍ የተደረገ የንብረት ክፍፍል ስምምነት ባይኖርም መሬቶቹ የእናታቸው መሆኑ ስለተረጋገጠ ተጠሪ እና አመልካች የማረጋገጫ ደብተር ይዘዉ አላባ ሲጠቀሙ ነበር አመልካች ወራሽ መሆኗ ስለተረጋገጠ ከተጠቀሱት መሬቶች ላይ አመልካች የድርሻዋን ልትካፈል ይገባል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡……………..

የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ከ ኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ

የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ከ ኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ

የሀረሪ ሕዝብ ክልል መንግሥት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ከክልሉ ውጭ የሚኖር የሐረሪ ሕዝብ ከዚህ ቀደም እንደነበሩት አምስት አገራዊ ምርጫዎች በ6ኛው አገራዊ ምርጫም ከክልሉ ዉጭ ያሉ የብሔረሰቡ አባላት ለሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ሊመርጡ ይገባል በሚል ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን ማስተናገድ እንደማይቻል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

የሀረሪ ሕዝብ ክልል መንግሥት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ምርጫ ቦርዱ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም የይግባኝ ቅሬታውን ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቧል፡፡ የፍርድ ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 205809 ሚያዚያ 19 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ የሰጠውን ውሳኔ ውድቅ በማድረግ ቦርዱ ከክልሉ ውጪ ያሉ ሐረሪዎች የመምረጥ መብትን አስቀድሞ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ተግባራዊ እንዲያደርግ ወስኗል፡፡

በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኘው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይግባኝ ችሎቱ የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ጉዳዩን ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበ ቢሆንም የሰበር አቤቱታውን የተመለከተው የፍርድ ቤቱ ሰበር ችሎት በሰ/መ/ቁ 207036 ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም ጉዳዩን በጥልቀት ከመረመረ በኋላ በሰጠው ውሳኔ የይግባኝ ሰሚ ችሎቱ የሰጠውን ወሳኔ አጽንቷል፡፡

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከ ኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከ ኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ

ጉዳዩ ለ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ አመልካች (ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክረሲ ፓርቲ) ያቀረባቸው እጩ ተወዳዳሪዎች  ምዝገባ መከልከላቸውን በመቃወም አመልካች ያቀረበውን አቤቱታ  የምርጫ ጉዳዮቸን ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተመልክተው ሰጡትን ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በሚል በሰበር እንዲታረም በመዝገብ ቁጥር 207000 ግንቦት 13 ቀን 2013 ዓ.ም የቀረበ ነው፡፡ 

እነ አቶ ግርማ ግያ እና አቶ አማረ ፍቅሩ የሰ-መ-ቁ. 186016

እነ አቶ ግርማ ግያ እና አቶ አማረ ፍቅሩ የሰ-መ-ቁ. 186016

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር 1ኛ ተከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ በአፈጻጸም ከሳሽ አቶ አበራ አላሮና በስር 2ኛና 3ኛ ተከሳሾች መካከል በሶዶ ከተማ መሀል ክፍለ ከተማ በ200 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ቤት እንዲሸጥ ሲታዘዝ የሥር 3ኛ ተከሳሽ የሆነው የሶዶ ከተማ መሀል ክፍለ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የሠጠውን መግለጫ በመቀየር ቤት የለውም ባዶ ቦታ ነው በማለቱ የአፈጻጸም ችሎቱ በንብረቱ ላይ የሠጠውን እግድ አንስቷል፡፡ በዚህ መካከል ንብረቱን ከአፈጻጸም ለማሸሽ በአመልካች ወኪልነት ቤቱን በብር 165,000.00 ሽጠውልኝ ቤቱን አፍርሼ ግንባታ የጀመርኩ ሲሆን ስመ-ሀብቱም ተዛውሮልኛል፡፡ አፈጻጸም ክርክሩ በይግባኝ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀጥሎ ቦታው ላይ ቤት እያለው ተገቢ ባልሆነ መንገድ ከአፈጻጸም ውጭ መደረጉ ተገቢ አይደለም በማለት ቤቱ በሀራጅ ተሽጦ ለፍርድ ባለመብት አቶ አበራ አላሮ ዕዳ መክፈያ እንዲውል ወስኗል፡፡ ክፍለከተማው የተሰጠኝን ማስረጃ አመክኗል፡፡ ስለዚህ አመልካችን ጨምሮ የሥር ተከሳሾች ቤቱ በአፈጻጸም ክርክር ሂደት ላይ እንዳለ እያወቁ ከቅን ልቦና ውጭ አላግባብ ለመበልጸግ በማሰብና መብቴ ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉ በመሆኑ ለሽያጭ የከፈልኩትን ገንዘብ ብር 165,000.00 እና ለግንባታና ለሠነድ የወጣውን በድምሩ ብር 321,222.00 በአንድነትና በነጠላ ኃላፊነት እንዲከፍሉኝ የሚል ነው፡፡ አመልካች ያቀረቡት መልስ ከሥር 2ኛ ተከሳሽ አቶ አብርሃም ዘውጋ በተሰጠኝ የውክልና ሥልጣን መሠረት ሕጋዊ ቤት በብር 65,000.00 ለተጠሪ ሽጫለሁ፡፡ የተሸጠው በብር 165,000.00 ነው የተባለው ሀሰት ነው፡፡ የተጭበረበረ ሽያጭ ሆነ አላግባብ የተገኘ ብልጽግና የለም፡፡ ጥፋት አልፈጸምኩም፤ ለክሱ ኃላፊነት የለብኝም ብለዋል፡፡ የሥር 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች የነበሩት ጉዳያቸው በሌሉበት ታይቷል፡፡……………

First141142143144146148149150Last