አቶ ሀበን ግዑሽ እና ሊቢያ ኦይል ኢትዮጵያ ሊሚትድ የሰ-መ-ቁ. 188331 አቶ ሀበን ግዑሽ እና ሊቢያ ኦይል ኢትዮጵያ ሊሚትድ የሰ-መ-ቁ. 188331 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች ተከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ከሳሽ ነበር፡፡ ተጠሪ ያቀረበው ክስ ከአመልካች ጋር ጥቅምት 25 ቀን 2002 ዓ/ም፣ መጋቢት 10 ቀን 2002 ዓ/ም፣ ሕዳር 12 ቀን 2004 ዓ/ም፣ ሀምሌ 30 ቀን 2004 ዓ/ም፣ ሕዳር 21 ቀን 2005 ዓ/ም እና ሕዳር 21 ቀን 2005 ዓ/ም የነዳጅ ማደያ ጣቢያ ኦፕሬተር/ዲለር ሥምምነቶች ተደርጓል፡፡ አመልካች የነዳጅ ውጤቶችን በጅምላ እየገዙ በሽሬ ከተማ፣ ሞጆ ከተማ፣ ዳንሻ ከተማ፣ ሁመራ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ሁለት ቦታ ላይ ባሉ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ለመቸርቸርና የማደያ ጣቢያ አገልግሎት ለመስጠት ግዴታ ገብተዋል፡፡ አመልካች የተረከቧቸውን የነዳጅ ውጤት ምርቶችን ባለመክፈላቸው በተለያዩ ጊዜያት ዕዳ ተሳስበን የሚከፍሉበት ጊዜ ተወስኗል፡፡ ክፍያ በማቋረጣቸውም ጥር 23 ቀን 2008 ዓ/ም በተደረገ 3ኛ የውል ማሻሻያ ሥምምነት በ2ኛው የውል ማሻሻያ ከተመለከተው ያልተከፈለው ብር 24,275,805.86 በየወሩ ብር 1,391,255.80 ሊከፍሉና ተጨማሪ አመልካች በዱቤ ሽያጭ የተረከቧቸውን ምርቶች ዋጋ ብር 8,816,151.10 በየወሩ ብር 367,339.63 ከፍለው ሊያጠናቅቁ የተስማማን ሲሆን ጎን ለጎን ሥራውን እንዲሰሩ፣ ወርሃዊ ዕዳ አከፋፈል የጊዜ ሠሌዳ ባያከብሩ በ3ኛው የውል ማሻሻያ ሥምምነት አንቀጽ 6 እና 2.13 እንዲሁም በስድስቱ የኦፕሬተር/ዲለር ውሎች አንቀጽ 5.3፣ 12፣ 13 እና 14 መሠረት ውሎችን የማቋረጥና ዕዳውን አጠቃሎ የማስመለስ መብት እንዳለን ተመልክቷል፡፡ አመልካች ለሠባት ተከታታይ ወራት ምንም ክፍያ አልከፈሉም፡፡ አራት ቼኮች ዋጋቸው ብር 27,902,795.60 የሆኑ የሠጡ ቢሆንም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቂ ስንቅ ስለሌላቸው ክፍያ ሊፈጸም አለመቻሉን ገልጾ ቼኮቹን መልሷል፡፡ ለአመልካች ክፍያውን እንዲፈጽሙ ግንቦት 01 ቀን 2008 ዓ/ም ማስጠንቀቂያ የተሠጣቸው ቢሆንም አልከፈሉም፤ የውል ግዴታቸው ጥሰው ከስድስት ወራት በላይ ማደያዎች አገልግሎት ሳይሰጡ ያለስራ እንዲቆዩ አድርገዋል፡፡ ስለዚህ በ3ኛው የውል ማሻሻያ ሥምምነት መሠረት ብር 33,091,956.96 ከሕጋዊ ወለድ ጋር አመልካች ለተጠሪ እንዲከፍሉ እንዲወሰን ዳኝነት ጠይቋል፡፡………..
አቶ ፍቃዱ አዱኛ እና የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የጠበቆች የዲስፕሊን ጉባኤ የሰ-መ-ቁ-195138 አቶ ፍቃዱ አዱኛ እና የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የጠበቆች የዲስፕሊን ጉባኤ የሰ-መ-ቁ-195138 አቶ ፍቃዱ አዱኛ እና የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የጠበቆች የዲስፕሊን ጉባኤ የሰ-መ-ቁ-195138 ጉዳዩ የጠበቃ ዲስፕሊን ክስ ጋር በተያያዘ የተሰጠ የጥፋተኝነትና የቅጣት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ተብሎ የቀረበ አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ በመጀመሪያ በታየበት በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የጠበቆች የዲስፕሊን ጉባኤ በአመልካች ላይ በቀረበዉ የዲስፕሊን ክስ አቶ እሸቱ ገበየሁ እና በባለቤታቸዉ ወ/ሮ አዲስአለም ገብረእግዚአብሔር መካከል የነበረዉ ጋብቻ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በመ/ቁጥር 70064 ላይ ያደረጉትን ክርክር በፍቺ ፈርሶ የንብረት ክፍፍል ዉሳኔ በቀን 19/02/2008ዓ/ም ከተወሰነ በኋላ አመልካች የአቶ እሸቱ ገበየሁ ባለቤት ከነበሩት ወ/ሮ አዲስአለም ገብረእግዚአብሔር ጋር በመመሳጠር የአመልካች ባለቤት ወ/ሮ አዲስአለም ደሳለኝ በእላዩ ላይ ቀን 11/06/2001 ዓ/ም ተብሎ ተጽፎበት በተፈረመ ዉል ለወ/ሮ አዲስአለም ገብረእግዚአብሔር ብር 600,000.00 እንዳበደሩ በማስመሰል የሐሰት የብድር ዉል በመፈራረም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 177766 ላይ ባለቤታቸዉን ወ/ሮ አዲስአለም ደሳለኝን ወክለዉ በአቶ እሸቱ ገበየሁ ባለቤት በወ/ሮ አዲስአለም ገብረእግዚአብሔር ላይ ሀሰተኛ ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ክስ በመመስርት አስወስነዋል፤በይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ፊት ቀርበዉ ተከራክረዋል በሚል በአቶ እሸቱ ገበየሁ የዲስፕሊን ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡…..
እነ ማስተዋል ታዘበው እና ወ-ሮ አቻም ሙጬ የሰ-መ-ቁ 180761 እነ ማስተዋል ታዘበው እና ወ-ሮ አቻም ሙጬ የሰ-መ-ቁ 180761 ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 86614 ግንቦት 21 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ፣ የባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 0318665 የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ እና የባህርዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 54250 ጥር 17 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታቸውን በማቅረበቀቸው ነው፡፡ ቅሬታቸውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካቾች የሚቃወሙባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልን ይገባል የሚሉትን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የስር ፍ/ቤት አባታችን በህይወት እያለ በ300 ብር ቦታ ገዝቶ ቤት ሰርቶበት እየኖረበት የሞተ መሆኑ ምስክሮቻችን መስክረውልን እያለ የ2ኛ ተጠሪ ምስክሮች ከኛ ምስክሮች ባልተሻለ ሁኔታ የሰጡትን ምስክርነት ወስዶ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን የሚል ነው፡፡……..
እነ መቶ አለቃ ኩምሳ ጨመዳ፣ወ-ሮ ኡርጌ መርጋ እና አቶ ካሳሁን አድነው የሰ-መ-ቁ 188071 እነ መቶ አለቃ ኩምሳ ጨመዳ፣ወ-ሮ ኡርጌ መርጋ እና አቶ ካሳሁን አድነው የሰ-መ-ቁ 188071 የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ጋር የሽያጭ ውል ያላቸው መሆኑና ውሉም የተፈፀመው ከጋብቻ በፊት መሆኑ በ2ኛ ተጠሪ ታምኖ እያለ ፤ 250 ካ.ሜ በሆነ ይዞታ ላይ ስድስት ክፍል ቤት ሰርቶ ከፊሉን መኖሪያቸው ቀሪውን የሚያከራዩት በአጥር ተከልሎ ለብቻው ያለ ቤት መሆኑ በምስክሮችም ሆነ በክፍለ ከተማ ተረጋግጦ እያለ ፤ እንዲሁም የአመልካች ይዞታ ከተጠሪ የተለየ መሆኑ እየታወቀ ተጠሪዎች የስድስት ክፍል ቤት ባለመብት አድርጎ እኩል እንዲካፈሉ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መወሰኑ እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህን ውሳኔ ማጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው በማለት በሰበር ለማሳረም ነው።...........
እነ ወ-ሮ መሰረት ገብሬ እና ወ-ሮ ወርቋሃ ገብሬ የሰ-መ-ቁ 182459 እነ ወ-ሮ መሰረት ገብሬ እና ወ-ሮ ወርቋሃ ገብሬ የሰ-መ-ቁ 182459 የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 123889 በቀን 15/12/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 222328 በቀን 15/09/2011 ዓ.ም ያሳለፈው ብይን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው። ለውሳኔው ምክንያት የሆነው ክርክር በስር የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተጀመረው የአሁን ተጠሪዎች ባቀረቡት የመቃወሚያ አቤቱታ ሲሆን የአሁን አመልካች የመቃወም ተጠሪ ነበሩ፡፡ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው ተጠሪዎች በቀን 08/12/2009 ዓ.ም ባቀረቡት የመቃወም አቤቱታ የአሁን አመልካች የአቶ ገብሬ ደስታ ልጅ ሳትሆን ልጅ ነኝ በማለት አመልክታ ፍ/ቤቱ ልጅ ነሽ በማለት የሰጠው ውሳኔ እንዲሰረዝልን በማለት ጠይቀዋል፡፡አመልካች በሰጡት መልስ በጋብቻ ውስጥ ስለተወለድኩ እና በህጉ ላይ የተመለከተውን የህግ ግምት ስላላስተባበሉ፤ ሟች እናትና አባቴ በ1965 ተጋብተው በ1969 ዓ.ም የተወለድኩ በመሆኑ፤ እንዲሁም ሟች አባቴ ልጅ መሆኔን አምኖ እንደ ልጅ ሲያስተምረኝ እና ሲንከባከበኝ ስለነበር አቤቱታቸው ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የመቃወም ተከሳሽ የሟች አቶ ገብሬ ደስታ ልጅ ናቸው በማለት የተሰጠው ውሳኔ ሊሰረዝ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ክርክርና ማስረጃውን መርምሮ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በሰጠው ውሳኔ አቶ ገብሬ ደስታ እና ወ/ሮ ዳዊ ገመቹ ጋብቻ መስርተው የነበረ መሆኑና የመቃወም ተከሳሽን ያሳደጓቸው መሆኑ በግራ ቀኙ የታመኑ ፍሬ ነገሮች ናቸው፡፡ የመቃወም ተከሳሽ አቶ ገብሬ ደስታ እና ወ/ሮ ዳዊ ገመቹ በ1965 ዓ.ም ተጋብተው በ1969 ዓ.ም ተወለድኩ በማለት ቢከራከሩም ምስክሮቻቸው ግን አቶ ገብሬ ደስታ እና ወ/ሮ ዳዊ ገመቹ መቼ እንደተጋቡ አላስረዱም፡፡ በተጨማሪም የመቃወም ተከሳሽ የልደት ምስክር ወረቀት ቢያወጡም የመቃወም ከሳሾች ምስክሮች በተመሳሳይ ቃል የመቃወም ተከሳሽ እናትና አቶ ገብሬ ደስታ ከመጋባታቸው በፊት የመቃወም ተከሳሽ ተወልደው የመጡ መሆኑን መስክረዋል፡፡ ሟች የመቃወም ተከሳሽን ያሳደጓቸው፣ ያስተማሯቸው እና በስማቸው የሚጠሩ መሆኑ በመቃወም ተከሳሽ ማስረጃዎች ቢረጋገጥም ይህን ያደረጉት ግን የሚስታቸው ልጅ በመሆናቸው ምክንያት እንጂ ልጃቸው በመሆናቸው አይደለም፡፡ በመቃወም ከሳሾች እና ተከሳሽ መካከል ዝምድና እንደሌለም በምርመራ ተጣርቷል፡፡ በመሆኑም የመቃወም ተከሳሽ የሟች አቶ ገብሬ ደስታ ልጅ ናቸው በማለት በቀን 09/10/2009 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 360(2) መሰረት ተሰርዟል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡….